ትግሉ ባስቸኳይ ይቀየር

ደራሲ - አሚጎ ዞሮመጣ


የሰው ልጅ ጠላቱን ማወቅ ከተሳነው

ተማረ አልተማረ ሁሉም ፋይዳ የለው

እያየ እየሰማ ሚስጥሩ ካልገባው

አሽከርና ጊታ መለየት ካቃተው

ወሳኝ ትግል ማድረግ እንዲት ነው ሚቻለው?


መለስ መሪ አይደለ እንደራሲ ነው

እምዪን ለማጥፋት መድሀኒት ነው ብሎ ፈረንጅ የሰራው


ቂሙን የማይረሳው ፈረንጅ መሰሪው

እኛን ሳያማክር በአገራችን ላይ ወያኒን ሾመው

ከዚያም እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጠው

በዘር በሀይማኖት ከፋፍለህ ግዛው

ያለ ርሕራሂም ከፍ ዝቅ አድርገህ ሕዝቡን አዋርደው

ታሪኩን በሙሉ እንዳልነበረ አርገህ በደንብ በክለው

ይህንን ካደረክ - የኛ ድጋፍ ላንተ አስከዘላለሙ የሚቀጥል ነው


እሱም አልቦዘነ ለብዙ አመታት

አገሪን ክፉኛ በሽብር መታት

ሕዝቡም ተጋለጠ ለማይሆን ስደት

አገር ቢት ያለውም ሱባኢ ቢገባ ጠሎትም ቢያደርግ

ምንም አልጠቀመው ታረደ እንደ በግ


CIA በክንፉ Mossad በክናፉ እየጠበቀው

ያልተመረመረ ያልታወቀ ምግብ ሕዝቡን ሲያበላው

መቃወም ሲገባን ዝም ብለን አለፍነው

ይዘገያል እንጂ የሗላ የሗላ የሚያስጠይቀን ነው

እረ ለመሆኑ አማካሪ አድርጎ ማነው የሾመው

ባገራችን ጉዳይ ማንም ሳይጠይቀው እጁን ያስገባው

ተው አርፈህ ተቀመጥ ብለን ካላልነው

እንዲሁ ቁጭ ብለን ማለቃችን ነው


አበው እንደሚሉት ቆማጣን ቆማጣ ብለው ካላሉት

ደስ ይለዋል አሉ ገብቶ መፈትፈት


እሰከ ዛሪ ድረስ ትግል ብለን ያልነው

ለማንም አልበጀ ጊዚ ማባከን ነው


ፈረሱን ከጋሪው ማስቀደም አለብን

የተገላቢጦሽ የትም አያደርሰን


እኒ እንደሚመስለኝ መድሀኒት የምለው

የትግል ታክቲኩን ቶሎ መቀየር ነው


ባዶውን ከቀረው ካገልጋዩ ጋሪ ከምንታገል


ሳንውል ሳናድር ትግሉን ወደ ጊታው ማዞር ይገባናል


ግፈኛውን ፈረንጅ እኛ ስናቀው

ዛሩ ደንገጥ ብሎ የሚያዳምጠው

ስታከብረው ሳይሆን ስትገርፈው ነው


የትም ይሁን የት ተዝናንቶ መኖር ነው የሱ ፍላጎት

ምንም ደንታ የለው እኛ ብንሰደድ ወይም ብንሞት


ሰለዚህ ወገኒ ዶክተር ፕሮፊሰር ምሁራኑ ሁሉ

ታክቲክህን ቀይር እስከመጨረሻው እንዲሰምር ትግሉ


መልፈስፈስ እናቁም እንሁን ኮስታራ

ባንዲራው ይሰቀል በቋራ ተራራ


እንቢልታው ይነፋ ከበሮው ይደለቅ

የታጋዮች መንደር ይበል ደመቅ ደመቅ


ከተማ ቁጭ ብለን በራብ ከሚፈጀን

ወይም እንደ ፍየል ጢማችንን ይዞ ከሚጎትተን

እንጠቀምበት ጋራ ሸንተረሩን እንዳባቶቻችን

በኩራት እንድትኖር እስከ ዘላለሙ ኢትዮጵያ አገራችን!!!Chapter-1 ..... Next24-07-2012