ምእራፍ - 5

ጉድ ነው


እኔን የሰለቸኝ ከዜናዎች ሁሉ ሞተ የሚሉት

በሱ የተነሳ ሳሰላስል ማደር የወገን እሮሮ ቀንና ሌሊት


ዜናው ከብዙ በጥቂቱ አንዲህ ብሎ የጀምራል -


ቤይሩት - ሊባነን


አረብ አገር ሄዳ አንድ ሀበሻ ሞተች ቢደበድባት

ዳኛውም ሳቅ ብለው ምንም እንዳልሆነ ፍርድ ሳይሰጡት

ገዳይ መሀመድን በል ደህና ሁን ብለው አሰናበቱት


ኮለኝ - ጀርመኒ


ትምርቱን ጨርሶ ሊሄድ ወደ ቤት

አቶቡስ ሲጠብቅ ቁጭ ባለበት

እስኪን ሄዶች መጥተው በጬቤ ወጉት


ዋሸንግተን ዲ ሲ -- ዩ . ኤስ . ኤ


ወደ መዝናኛ ቤት አላስገባም ቢሉት

መስኮቱን ሰበረው በውድቅተ ሌሊት

ከጭካኔም ብዛት አምስት ስድስት ሆነው ጨፍጭፈው ገደሉት


እናንት ጋዜጠኞች ይኸ ነው እንግዲህ ስለኛ የሚወራው ?

እረ ለመሆኑ አበሻው ገደለ የሚለውን መዝሙር መች ነው የምንሰማው -


Author - አሚጎ

Chapter-6 ..... Next© 2016 Ethiocartoons.net