ምእራፍ - 4

ዋ ! ስንቱ ጀግና ተኮላሸ


የሰው ልጆች ሁሉ ሀይማኖት አላቸው

በድንጋይ ይመኑ ወይም ባምላካቸው

ፈጣሪን እንደሆን አንድም ሰው አላየው

ሀይማኖትም ቢሆን ሳይንስ እንዳልሆነ ልቦና እያወቀው

ያባት የናት እምነት አልፈልግም ማለት ጥበቡ ምን ላይ ነው

መጥደቅ የፈለገ በወረስው እምነት ጠንቶ መቆየት ነው


ጰንጤዎችን ብንወስድ አዲሱን ሀይማኖት

በቅዱስ መጵሀፍ ነው አሉ የሚያምኑት

ከጥንቱ ሀይማኖት ከዚያ ከኦርቶዶክስ ...

ከጥንቱ ሀይማኖት ከዚያ ከካተሊክ ...

ለምን አስፈለገ አጉል መለያየት

ግባችን ከሆነ ሞቶ መነሳት


አንበሳውን ጀግና ሞት የማይፈራውን

ዘፋኙን እንዲሁ ሕዝብ ያፈቀረውን

ይህ አጉል ሀይማኖት አደረገው ብኩን

ምሁራኑ ሁሉ ፈላስፋ ለመሆን ትንሽ ሲቀራቸው

የጰንጤው ሰባኪ በመዳፉ ብቻ ዘጭ አደረጋቸው

እንደዛ ሲሆኑ አትኩሮ ላየ ሰው አይ ማሳዘናቸው

ዘፋኝ ምሁራኑ አምላክን ለማግኘት አልባሌ ቦታ እንዲህ ሲዋትቱ

ነገሩ ምንድነው ሕዝቡ እኮ ፈዘዘ እረ መላ ምቱ

ግራም ነፈስ ቀኝ ውነት ለመናገር በንጡህ አንደበት

እኔ የምፈራው እኔ የማከብረው አዲሱን ሀይማኖት

እነ አሊ ቢራ - መሀሙድ አህመድ ጰንጤ የሆኑ ለት -


ቅር ያለው ስው ካለ ይቅርታ ብያለሁ -


Author - Amigo Zorometa


Chapter-5 ..... Next© 2016 Ethiocartoons.net