ምእራፍ - 3

ፍርድ ወይስ ፍርጃ


ዳኛ


እዚህ ያመጣችሁ ዋናው ቁም ነገሩ

ምንድነው ጉዳዩ እስኪ ተናገሩ


አቃቤ ሕግ


አመስግናለሁ ጉዳዩን ለመስማት ስለፈቀዱልን

አንድ ኢትዮጵያዊ ነጮች ደብድበውት ሞተ ነው የሚሉን

ጌታዬ ይመኑኝ በፍጡም አልሆነም እነሱ እንደሚሉት

መርማሪውም ዶክተር ለኛ አሳውቆናል እንደሆነ ውሸት

የመንግሥት ጠበቃ ሆኜ ሳገለግል ለብዙ ዘመናት

አጋጥሞኝ አይውቅም እንዲህ የተንዛዛ አይን ያወጣ ተረት

በእኩለ ሌሊት ሰክሮ እየወደቁ ስው ገደለኝ ማለት -

ይሄን ነው እንግዲህ ለጊዜው የምለው

አስፈላጊ ቲሆን ብዙ ነገር አለ የምጨማምረው -


ዳኛ


እስኪ አንተ ደሞ የነጩ ጠበቃ ትንሽ አክልበት

ነገሩን በቶሎ ወጪ ሳናበዛ ፍርድ እንድንሰጥበት -


የተከሳሽ ጠበቃ


ውነት ነው ጌታዬ በዚህ ኢኮኖሚ በቀውጢ ዘመን

መች የሚያዋጣነው በሆነ ባልሆነው ጊዜ ማባከን

ከሳምንታት በፊት ሞተ የተባለው ወጣት አህመድ

ስውነቱ ዝሎ አዳለጠውና ሲወድቅ ከምንገድ

ትንሽም አልቆዩ ፖሊሶቹ ምጥተው ብድግ ሲያረጉት

ሕይወቱ አለፈች ያሞሞቱን ሚስጥር ምንድነው ሳይሉት -

በጣም የሚገርመው በያደባባዩ ገደለ የሚሉት የኔን ክልያንት

ትክክል አይደሉም ሳያረጋግጡ ወሬ ማናፋት -

ክቡርነትዎ ፊትዎ ቆሜአለሁ ጠብ የማይለውን ፍርዶን ለመስማት -


ዳኛ


የከሳሽ ጠብቃ አንተስ ምን ትላለህ

አስኪ ወዲህ እምጣ መርጃ እንዳለህ


የከሳሽ ጠበቃ


የኔ መረጃዬ ምስክሮች ናቸው

አምስት ስድስት ሆነው እጁን ጠፍረው

ያለ ርህራሄ ሲገሉት ጨፍጭፈው

ለኔ ነግረውኛል ምስክሮች መጥተው

ይሄ ነው ማስርጃው እኔ አንደማውቀው

ከዚህ በተረፈ የፖሊስ አለቃ ካቲ የተባለች

በዚያች ቀን ሌሊት ስለተስራው ግፍ ለአለም በሙሉ መግልጫ ስታለች -

በህጉ መሰረት የአይን ምስክር የፖሊስ ሪፖርት እስካለን ድረስ -

በቂ ይመስለኛል የያዝነውን ጉዳይ ከዳር ለማድረስ -

ውነት ቻምፒዮን ነች የትም ሆነ የት

እተማመናለሁ ፍርድዎ እንደሚደርግ ሀቅን መሰረት -


የመጨረሻ ፍርድ


ከቀኝም ከግራ ሁሉንም ሰማነው

እነዚህ እስላሞች እኛ ስናቃቸው

እራስን በመግደል የታወቁ ናቸው

ፍርድ ይሰጠን ባዮች ይህ ላለመሆኑ ምን ማስረጃ አላችው

የከሳሽ ጠበቃ በቂ ማስረጃዎች ባለማቅረባቸው

በሕጉ መሰረት ፋይሉን ብንዘጋው በመተማመን ነው ቅር እንደማይላቸው -

ከንግዲህ በኅላ ነጣ ስለሆኑ ተከሳሾች ሁሉ

ያላንዳች ዋስትና ወደሚሄዱበት መሄድ ይችላሉ !


Author - Amigo ZorometaChapter-4 ..... Next
© 2016 Ethiocartoons.net