ልጁ
አባቱን አይመስልም
ደራሲ - አሚጎ ዞሮመጣ
አንድ ሚስጥር አልኝ ስሙኝ በጥሞና
ለብዙ ዘመናት በሆዴ የያዝኩት አስገራሚ ዜና
ከጭንቀት ለመዳን ይህን ሳሰማችሁ
በፈጠረን አምላክ በአላህ ብላችሁ
አዳምጡኝ እላለሁ በሙሉ ልባችሁ
ኢ-ሜል አድርጉልኝ ምክርም ካላችሁ
ሚስቴን ካገባሓት ሶስት አመት ሆነኝ
ከስዋም የወለድኩት አንድ ወንድ ልጅ አለኝ
አንደሚታወቀው ወንድ ልጅ ሲወለድ አባት ደስ ይለዋል
ግን ከሰውነቱ አንዱ እሱን ካልመሰለ ያጠራጥረዋል
አንደ ጠላ ቂጣ አሁንም አሁንም አካላቱን ሁሉ ባገላብጠው
ፈጣሪ ይመስክር እኔን የሚመስል አንድም ነገር የለው
ይሄ ነው እንግዲህ የጭንቀቴ ሁሉ ዋናው መንስዔው
ግራ ተጋባሁኝ አስኪ አንድ በሉ ስለ መፍትሄው
እንዲሁ አንደቀልድ ማን ይመስላል ብዬ ሚስቴን ስጠይቃት
ሁሌ የምትነግረኝ የማላቃቸውን የአባትዋን አባት
እኔም ውነት መስሎኝ ፎቶ እንድታሳይኝ ዓጥብቄ ጠይኳት
ግና ምን ይሆናል የምትስጠኝ መልስ አጉል ተረት ተረት
ካገሬ ስወጣ ይዤ የወጣሁት እጅና እግሬን ነው
እኔ እዚህ ቁጭ ብዬ የሳቸውን ፎቶ ከየት ነው
ማመጣው
ብላ ስትጮህብኝ ከመቸውም በላይ ጥርጣሬ ያዘኝ
ከዚያ በኋላ ግን የህይወት ታሪኳን መመርመር ጀመርኩኝ
ሲያወሩ ስምቼ ችላ ያልኩትንም የአሉባልታ ወሬ
ውሳኔ ላይ ደረስኩ ጊዜዬን ስውቼ ላጤነው ከምሬ
የድካሜም ዋጋ እንዲህ አንድ ዋዛ አልቀረም በከንቱ
በጥቂት ቀናት ውስጥ ሚስጥሩ ታወቀ ከስር መሰረቱ
የሚስቴ ጉድ ወጣ ወደ አደባባይ
የኔም ልብ ፈካአለ እንደ እንጉዳይ
ታሪኩ እንደዚህ ነው ስሙኝ ቶሎ ቶሎ
ካለችበት ሰፈር ትንሽ ወጣ ብሎ
ያበሻ አስቤዛ አንጀራ በርበሬ ቆሎ ዶቦ ቆሎ
ልትገዛ ስትሔድ ወከክ ያደጋታል አንድ የህንድ መለሎ
በፍቅር ተሳስረው ለጥቂት አመታት ከቆዩ በሗላ
መፈልግ ጀመረች ለትዳር የሚሆን ሌላ ያልተበላ
ከሱ ከተጣላች ገና በሳምንቱ መጥታ ከኔ ቤት
እንዝርት ሆነችብኝ አስከ ዘላለሙ አንዳስታውሳት
ነገሩም ሆነና እሷ እዳሰበችው
ላገባት ወስንኩኝ ሳይቀማኝ ሌላ ሰው
ይህ በዚህ አንዳለ ቀናቶች ያልፉና ወራቶች ሲተኩ
በሆድዋ መወጠር ማርገዝዋን አወኩ
አንደማይሆን የለም በኔ አቆጣጠር ዘጠኝ ወር ሳይሞላ
ጥቁር ጠጉር ያለው ጠይም ልጅ ዱብ አላ
ማርያም ያጥናሽ ብሎ የሚገባውና የሚወጣው ሁሉ
ልጁን ከኔ ጋራ ያመሳስሉና ይንሾካሾካሉ
እሱ አጭር ቀጭን አራስ መላጣ
አንዲህ ያለ ጠጉራም ከየት ነው የመጣ
ግን እኮ ይች ልጅ ትወጣ ነበረ ካንድ ህንዲ ጋራ
ብለው ሲቦጭቁኝ ሁሉም በየተራ
እስኪ በናታችሁ ከሃሚታ በፊት ጉዳዩ ይጣራ
ብላ ስትቆጣ የሷ ታናሽ እህት ስው ይሰማትና
አንዱ ሹክ ይለኛል እንደ ስበር ዜና
ከያማ በኋላ ምኑን ልንገራችሁ የጭንቀቴን ክብደት
ይሄው እስከ ስዛሬ ተሸክሜዋለሁ ለሶስት አመታት
የኔ አይደለም ብዬ ልጁን እንዳልክደው
ዳዲ ሲለኝ ቤቢ ብዬ አቅፌ ስሜ አሳድጌው
በየሜዳው በየአስፋልቱ እጁን ይዤ አዝናንቸው
ደስ እንዲለው በመኪና በያለበት አሽከርክሬው
አበሻ ሬስቶራንት ወስጄ ከወንድ ከሴቱ አስተዋውቄው
ከዚያም በተረፈ ዘመዶቼ ሁሉ ወንድ ልጅ ወለደ ብለው ተደስተው
ከንግዲህ በኋላ የኔ አይደለም ማለት የማይሆን ነገር ነው
በሌላ አንጻር ደሞ የኔ ያልሆነውን የኔ ነው ማለቱ
እንኳን አይምሮዬ አለም ይታዘባል አንደሆንኩኝ ከንቱ
እረ ምን ይሻላል ከዚህ ጉድ ያውጣችሁ
እስኪ መላ በሉ ምንድን ነው ምክራችሁ
ኋላ ልብ አድርጉ የዚህ አይነት ችግር በናንተም ይመጣል
እንደምንም ብለን መፍትሄውን አሁን መፈለግ ይሻላል
እንግዲህ ሃሳቤን በናንት ጥያለሁ
እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ እላለሁ
----------------------- The End ------------------------

www.ethiocartoons.net
© 2005 Amigo Zorometa