የቀድሞ ጦር ሐይሎች አጭር ታሪክ

ደራሲ - አያ ሙሄ

አቀናባሪ - አሚጎ

 

ባለሁበት አገር መለዮ ለባሽ ለመኖሬ የታወቀ በመሆኑ አንድ አዲስ የመጣ የቀድሞ የጦሩ አባል ሰዎች አስተዋወቁኝ አጋጣሚም የማዕረግ አቻዬና የነበርንበት ክፍልም ተቃራራቢ ስለነበር አንድ አንድ ጫወታዎችን ስንጀምር ግንዛቤያችን ግን ለየቅል ሆነብኝ :: ያወራነው ፖለቲካ ሳይሆን የጦርሜዳ ውሎ ነበርና እኔ የተገነዝብኩት ሁኔታና እሱ የተረከልኝ ታሪክ ተቃራኒ ስለሆነብኝ ግራ ተጋባሁ :: ጭውውታችን አንዱ ከአንዱ የሚያበላልጥ ሳይሆን ለነበሩት ስህተቶችና ድሎች ተጠያቂና ባለቤት ማነው የሚለው ግን ሁለታችንም የተለያየ ስለነበር እስኪ በየአገሩ ያሉ አባሎቻችን ጋር እንድንወያይበት ይህን አርዕስት ከፈትኩ ::

1. በቀይ ኮከብ ዘመቻ ጊዜ በመብረቅ ዕዝ ግንባር 21ኛ ክ /ጦር 44ኛና 45ኛ ብርጌድ በጠላት ኃይል በመመታቱ የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ውብሸት አፍአበት ላይ ሲረሸኑ የ 44ኛ ብርጌድ አዛዥ የነበሩት ሌ /ኮ ስለሺ ገ /ፃዲቅ ደግሞ ማዕረጋቸው ተገፈው በ 10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ሲደረግ የመብረቅ ዕዝ አዛዥ የነበሩት የዛኔ ብ /ጄ ቁምላቸው ደጀኔ (በኃላ ሜ /ጄ ) ከሰራዊቱ ወደ ኤርትራ ክ /ሃገር ኮሚሳሪያት እንዲዛወሩ ተደርጎ ነበር :: በዚህም ጊዜ በብዙዎቻችን ዘንድ የኮሎኔል ውብሸት መረሸን ልክ እንዳልነበረና ሊረሸኑ የቻሉት ብ /ጄ ቁምላቸው ራሳቸውን ከሃላፊነት ለማዳን ባቀረቡት ሪፖርትና በሜ /ጄ ኃይለጊዮርጊስ ሃብተማርያም ግብታዊ የተዳላ ምርመራ እንደሆነ አስታውሳለሁ :: በቅርብ የነበሩ አለቆቻችንም በዚህ ተቆጭተው ሲናገሩ እሰማ ነበር ::

2. በናቅፋ ግንባር የነበሩት የ 3ኛ ክ /ጦር 4 ብርጌዶች ናቅፋን ሊቆጣጠሩ በ 400 እና 500 ሜትር ርቀት ላይ እንዳሉ የ 17ኛ ክ /ጦር አካል የነበሩ 2ኛ ፓራ ኮማንዶና 19ኛ ነበልባል ብርጌድ የውጊያ ቀጠናውን እንዲረከቡ መደረጋቸው ስህተትና ቀደም ሲል በነበሩት ውጊያዎች በሰው ኃይል የተመናመኑት 2 ብርጌዶች የአራት ብርጌድ ቀጠና በመያዛቸው ጠላት መከላከያውን ለመስበር እንደቻለ ብዙዎች ገምግመን ጨርሰነዋል :: እኔም እዛ ነበርኩ ::

3. በ 1978 እ .ኢ .አ ባህረ -ነጋሽ ዘመቻ ሲካሄድ የ 7ኛው አየር ወለድ ከሰማይ ላይ እየወረደ "አምበርበር " የተባለውን የሻዕቢያ ዋና የወታደራዊና ፖሊትቢሮ ፅ /ቤት ለተወሰነ ሰአታት እንዳርበረበደና ብዙም ሰው እንደተጎዳብን አስታውሳለሁ :: በውጊያውም የሻዕቢያ ወታደራዊ ዋና አዛዥ የነበረው ዒብራሂም ዓፋ እንደሞተ ሻዕቢያ በኃላ ራሱ እምኗል :: ታድያ ውስን አባላት ዕቅዱ ስህተትና ጀብደኛ የሆነ ; በአሰላለፉም ሆነ በውጤቱ የማፈግፈጊያ ወረዳ ያልነበረው ነው በለን አምነናል ::

4. 604 ኮር ሽሬ ላይ ሲደመሰስ የነበረው ትልቁ የለገሠ አስፋው ስህተት የነበሩትን ክ /ጦሮች አንድ ላይ በማጎር ያለምንም የመከላከያ ወይም የማጥቃት ትዕዛዝ እንዲቀመጡ ማድረግና የአዛዦችን ሃሳብ አልቀበል ማለቱ ነው ::

እንግዲህ በነዚህ ግንዛቤዎቼ ይህ ወንድሜ የነገረኝ ታሪክ ግን በጭራሽ እኔ ስህተቶች ያልኩዋቸው በወቅቱ እርምጃው ተገቢ ነበር ነው ያለኝ :: ምናልባት አያውቅ እንደሆን ብዬ እንዳልገምት የነበረው ኃላፊነት ከኔ ያልተናነሰና ብዙውን ጊዜም እኔ አብሬአቸው ከነበርኩት ከፍተኛ መኮንኖች የሰራና ባለሙያ ነው ::

በሉ እስኪ እናንተም የምትሉትን በሉኝ ::

Terrible

ሰላም የቀድሞ ወገን አያ ሙሄ ! እንዴት ነህ ? በዉነቱ በጣም ደስ የሚል ነገር ነዉ የጻፍከዉ :: እኔ እንኩዋ ወደበሁዋላ ላይ ነዉ ወደ ጦሩ የተቀላቀልኩት :: ምንም የጦር ሜዳ ተሞክሮ ስለሌለኝ ላግዝህ ባለመቻሌ በጣም አዝናለሁ :: ነገር ግን ይህሽን ኮት ያደረግሁዋትን ነገር እስኪ ተመልከታት ::

አያ ሙሄ እንደጻፈ(ች)ው:

3. የ 7ኛው አየር ወለድ

እንደዛ የሚባል ጦር ነበረ እንዴ ? እኔ የማዉቀዉ 102ኛ አየር ወለድ ክ /ጦርን ብቻ ሲሆን በርግጥ በሁዋላ 201ኛ የሚባል በደርግ ዉድቀት አካባቢ ማለትም በ 1982 ተቁዋቁሞ እንደነበረ አስታዉሳለሁ ::

በል እስኪ ተሳታፊ ባይኖርም ታሪክ ነዉና አዉጋን ::

 

ላሊበላ 4

አሁን የቀይ ኮከቡንም ሆነ የአልካቸውን የጦር ክፍሎች አላውቃቸውም :: የማስታውሰው ግን የጃንሆይ ጠባቂ የነበረው የ 3ኛን ብርጌድ ጦር አንድ ሻለቃ ጦር ናቅፋ ከተማዋ ላይ የጥበቃ ወረዳ በተሰጡበት ጊዜ አዲስ አበባ መጥቼ ነበር :: ሻቢያም ናቅፋን መቆጣጠር አይችልም ነበር ::

ደርጉ ባጠቃላይ ኢትዮጵያ ነች ብሎ ያመናት ወይም የተቀበላት አዲስ አበባን ብቻ ነበር ማለት ይቻላል :: አዲስ አበባ ሠላም ነች በዚያን ጊዜ ግን ጀማምሮታል :: ሕዝባዊ መንግሥት አሁኑኑ እያሉ ጥያቄ የሚያፋጥኑ ወጣቶቹ ትውልድ የኔ እኩዮች በብዛት ነበሩ ::

ደርጉ ግን ከሲቪሉ ጀምሮ እስከ ወታደራዊ ካምፕ ድረስ መፈራቱን ብቻ ነበር አግኖ የያዘው :: በዚያም የተነሳ ያንን

3ኛ : ብርጌድ ክብር ዘበኛ ጦር እዚያ አፋበትና ናቅፋ ላይ ወስዶ ማስፈር ወታደሮቹን ከነ መሪዎቻቸው መዓበል ጀኃነብ ውስጥ ማስገባት ነው ::

እስኪለማመዱ እንኳን ከረን ወይም የባሕር ኃይልን አምባ ጥበቃን ቢያደርጉ ኖሮ ሻቢያም ወደ ናቅፋ ባልቀረበ ነበር :: ከዚያስደርጉ አልሰማ ብሎ ናቅፋ የተፈረደበት ቶር በሻቢያ ተዋጊዎች ተከቦ ከብዙ ወራቶች በላይ ሲሰቃይ ደራሽ ወገን በማጣቱ በጀርመን ራዲዮ አማካኝነት (ጩኸቴን ብጸሙኝ ) የምትለዋን የጥላሁን ገሠሠን ተወዳጁዋን ዘፈን እንዳለ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መርጠው ነበር ::

ከዚያም ኮሎኔሉ ራሳቸውን ሲገሉ ሠራዊትቱም ተዋግቶ በመጨረሻ አለቀ :: ናቅፋም ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተያዘች :: አሁንም ስህተቱ የማነው ? ስህተቱ አገርና ፖለቲካ ወታደርነት አብረው አይሄዱም :: ወታደር ወታደር እንጂ የፖለቲካ መሪ በጭራሽ ሊሆን አይገባውም :: ባፍሪቃ ውስጥ ግን ገዳቢ ሕግና ወሳኝ ህዝብን ሳይፈሩ ጀበጀነራሎች የሚስተዳደሩ ብዙዎቹ ናቸው :: ግብጽና ናይጄሪያ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎቹም ሱዳንን ዩጋንዳንም ጭምር ይዞ የሚጓዝ ነው ::

ያባይሆን ኖሮ አገራቺን በሰላማዊ ሕዝቡና ምሁሮቹዋ ብትመራና ሥልጣኑ የህዝብ ቢሆን ኖሮ ህዝቡ አስቦ ማንኛውንም በላዩ ላይ የሚሸርቡበትን ጠላቶቹ ሊያጠፋቸው ታግሎም ሊጥላቸው ይችል ነበር :: ለነበሩት አዳዲስ የኮሚኒስት መንፈስ በልባቸው ገብቶ የረበሻቸው አገራችንን ወደ 1917 ሮቮሎሺን ወስደው ወጣቱን ሲጨሩሱት የሰውን ሃብት በግፍ ሲወርሱት ያንና ሌላው ተጨምሮ ለኢትዮጵያ ጠላቶቹዋ ወያኔና ሻቢያ ሳይሆን ሕዝቡዋም ጭምር ነበረ ያደመባት ያሰኛል ::

ታዲያ ያጠፉት ያሁሉ ጦርና መሣሪያ ማጋዙ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱንም ከጅ ወደ አፍ ብቻ የሆነን ኤኮኖሚ ድቅቅ እንዲል አድርጎአል :: ታዲያ ከለገሃር የነበረን ጦር ናቅፋ ሄዶ ይቀመጥ ማለት ጦሩን መጥላትና ተጋልጦም እንዲሞት ብቻ ሳይሆን ለዚያ ጦር ከፋኖዎች ጋራ ለመዋጋት ሲባል ስልጠና ተሰጥቶት ነበር ወይ ነው ? አልተሰጠውም የተሰጠው የነበረው ልብስን አሳምሮ ጫማቸውን ወልውለው ጽዳታቸውንም ጠብቀው ጃንሆይን ማጀብና ብሎም የጃንሆይን ቤተ መንግሥት ማስከበር መጠበቅ ብቻ ነው :: ያን ጦር ነው የተፋፋመ ውጊያ ያለበትና ከፍተኛ ኃላፊነት ቦታ በዚያ ቀውጢ ወቅት የላኳቸው ::

ያስህተት አሁን ያመጣህልኝን የጦር ክፍሎች በብዛት እንዲጎርፉ ሆነውው ያለውጤትም አዛዦቻቸው መረሸናቸው የሚያስገርም ነው :: ጉድና ጅራት ከወደ ኌላ ነው ይባላል :: የወያኔውም ሚስጢር ለወደፊት ወያኔ በሚወድቅበት ጊዜ ጥሩ ሆኖ ይገለጻል በሚል እምነት ይኖረኛል ::

ከረን ስትያዝ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ጦር ስለቀረበት አዛዡ ኮሎኔል ይልማ በሽጉጥ ራሱን ከመምታቱ በፊት የከረን አዲስ ባንክና ንግድ ባንክ በውጣቸው ያለውን ገንዘብ አቃጥሎት ማንኛውንም የሠራዊቱንም ንብረት አቃጥሎ አበላሽቶ በመጨረሻ ራሱን መግደሉ ምንኛ ኢትዮጵያን እንደሚወዳት ያመለክተናል ::

በምትኩ ግን አዲስ አበባ ተቀምጠው ሲቪል ጀነራሎቹ ና ኮሚሣር የሚባሉት አንድ አዛዥ አዛዥነቱን ከማክበር በሱም እንደመመራት ፋንታ ፖለቲካ ጠዋት ማታ ለወታደሩ በማስተማር አዛዥና ታዛዥ መከባበር ቀርቶ መናናቅና ልክ እንዳልከው እንደሽሬ እንዳስላሴው ትዛዝ ሰሚና የጥበቃ የመረጃ የንቃት ሁኔታዎች በመበላሸታቸው ወያኔ ያንን የሚመስል ወንጀሎችን ሊሰራ ቺሏል :: የሚያሳዝን ሁኔታና ፋሽስቶች እንኳን የገደሉዋቸውን ወታደሮች በቶሎ ይቀብሩዋቸዋል :: ወያኔዎች ግን ጀነራል መኮንኖቹ ሳይቀሩ 3 ቀን ሙሉ በሞቱበት መሬት ላይ ቆይተው ሬሳቸው ሊፈርስ ሲል የፎቶ ካሜራ ይዘው ያንንም አንስተው ለዓለም ረዳቶቻቸው መዝናኛ እንዲሆን አቅርበው ነበር ::

ይህ አሳዛኝ ሥራ መቸስ የማይታመን ይመስላል ግን ተፈጽሟል :: ፈጻሚዎቹ እስካሁንም ድረስ ኢትዮጵያን እየዘረፉ ኢትዮጵያንም እያፈረሱ ይገኛሉ :: ግድያቸው ደግግሞ ከቀድሞው ብሶባቸዋል እንጂ ምንም አልተሻሻሉም ::

አያሙሔ እርግጥ ነው አሁን ላለው ትግል ያንን የመሰለ ማንሳትህ ባንድ ፊት ይጠቅማል :: በልሌላው አቅጣጫ ግን ያሳዝን ይመስለኛል :: ታዲያ ከንግዲህስ ስላለው የመስክ ትግል ወገኖቻቺን አርበኞቹ እንዴት ምን የመሰለ የማጥቃትም ሆነ የመከላከል እርምጃ መውሰድ ይገባቸዋል ትላለህ :: እርግጥ ነው ሃሳብ ነው እኛ የምንነጋገረው የአርበኞቹን ስልቶች ሳንነካ የነሱ የነሱ ነው በዚያው ልክ አሁን እየተነጋገርን የምንገኝውን እነሱም ያነባሉ :: ታዲያ የስልት አይነቶች ብዙ ናቸውና እነኛም ሁሉ በማምጣት ካለፈው ስህተትም በመማር ለወደፊትም ያእንዳይደርስ መደረግ ይኖርበታል ነው የኔ ሃሣባዊ አቀራረብ ::

ወታደር አገርና ዳር ድንበር የህዝብንም ነጻነት ለመጠበቅ የሚያበቃ ወታደራዊ ትምህርት ብቻ መማሩ እርግጥ ነው :: ከዚያ አልፎ ፖለቲከኛና በካድ Rኤዎች በኮሚሳሮች የሚነቃ ከሆነ ያወታደራዊ ይዘት እንዳለ ፖለቲከኛ ሆኗል እንጂ ወታደር አይባልም :: በዚያም ምክንያት ይመስለኛል ያሁሉ ሽንፈት በየወቅቱ የደረሰው :: ፖለቲከኞች እኮ አይጣል ነው ሕይወታቸውን ሲወዱዋት ? ሕይወትን የሚያፈቅር ከፖለቲከኞች የበለጠ በምድር ላይ አይገኝም :: ለዚህም ነው አገራቺን አሁን ያለቺበት አጣብቂኝ ውስጥ እንድትኖር የሆነቺው ::

አክባሪህ

ላሊበላ 4

አያ ሙሄ

ውድ ወንድሞቼ ላሊበላ 4 እና Terrible, አሁንም ሸንቀጥ ያለ ሰላምታ !!!

ወገኔ Terrible 102ኛ አየር ወለድ ክ /ጦር ሲሆን በስሩ 5ኛ 6ኛ 7ኛና 8ኛ አየር ወለድ ብርጌዶች ነበሩት :: 5ኛ አየር ወለድ ብርጌድ ብቻውን በ 1973 ተመልምሎ እስከ 1974 በደንብ ሰልጥኖ የተመረቀ ሲሆን በ 1976 ዓ .ም 6ኛ 7ኛና 8ኛ አየር ወለድ ብርጌዶች ተመልምለው እንደነገሩ ስልጠና ከተሰጣቸው በኃላ 102ኛ አየር ወለድ በክ /ጦር ደረጃ ተዋቀረ :: ሶስቱም ብርጌዶች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁት ማሰልጠኛ ጣብያ ብቻ ሳይሆን በየቀጠናው ጭምርም ነው :: የመጀመርያው የክ /ጦር አዛዥ ወደር የሌለው የጀግና ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆኑት ብ /ጄ ተስፋዬ ሲሆኑ ም /አዛዡ ኮሎኔል በኃይሉ ክንዴ ነበሩ :: በኃላም ብ /ጄ ተመስገን ገመቹ የክ /ጦሩ አዛዥ ነበሩ :: የክ /ጦሩ ዘመቻ መኮንን ካስታውስክ ደግሞ ብዙ ጨዋታ ይኖረናል ::

ወገኔ ላሊበላ በነገራችን ላይ በናንተ ጊዜ ናቅፋ የነበረው ሰራዊት መሉ በመሉ አልተደመሰሰም :: ከላይ ወደር የሌለው ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆኑት ብ /ጄ ተስፋዬና ሌሎች ጓዶቻቸው የናቅፋን ከበባ ሰንጥቀው ወጥተዋል :; ሜዳሊያውንም የተሸለሙት ያን ጊዜ ነው ::

ወገኔ ላሊበላ 4 የገለፅከውን ከሞላ ጎደል የምስማማበትና የሆነ ነገር ነው ::

አሁንም አገራችን ውስጥ ስላለው ፖለቲካ ለፖለቲከኞች ልተወውና ስለወታደራዊ ጉዳዮች የመሰለኝን ትንሽ ኃሳብ ላስቀምጥ :: ወታደራዊ ታክቲክ ራሱን የቻለ ሚስጥር ነውና ዌብ ላይ ከመተንተን የሙያው ህግጋት ያግደኛል :: አስፈላጊ ከሆነ ሰው ጋር ግን መነጋገር ይቻላል :: ጠቅለል ባለመልኩ ግን ወንበዴዎችን እናውቃቸዋለን ያውቁናል :: የተፈታነው በራሳችን መሪዎች ቁንፅል የፖለቲካ ጉዞ እና በውጭ መንግስታት መሰሪ ዕቅድ ነው :: በ 1974 እና 1975 ዓ .ም የሻዕቢያን አከርካሪ አጥንት ለመበጠስና ወያኔን አስሶ ለማስተማር ያደርግናቸው ዘመቻዎች ወንበዴዎችን አደናግጦ "የብረት አጥር " የሚል ስም አስከመስጠት ደርሰው ነበር :: እንዳልከው በፖለቲካ መምሪያውና በአዛዦች እንዲሁም በአዛዦችና በ 01 ጓዶች (ሩስኪ አማካሪዎች ) የነበረው የታክቲክና ስትራቴጂ ንትርክ የማይስፈልጉ መስዋዕትነቶች ተከፍለዋል :: ያም ሳይቀር ሰራዊቱ ወደፊት እንግስግስ ለምንድነው ምሽግ ውስጥ ቁጭ በለን የምንሰቃየው ብሎ ሲጠይቅ ፀረ -ሕዝብና አናርኪ እየተባለ ተረሽኗል :: በኃላም ወታደራዊ ደህንነት ሲታከልበት በአመራሩ ላይ መረበሽና በራስ ያለመተማመን ሁኔታዎች ተፈጠሩ :: እኛም ሃገርን ለመጠበቅ ወገንን ለማገልገል አስተምሮ እዚህ ያደረሰንን ህዝብ አደራ ለመወጣት አለመቻላችን ሲታወቀን ግማሾቻችን በትምህርት ስም ከአገር ወጣን ሌላውም እንደየዘመዱ ወደ መሃል አገር ነጎደ :: ምስኪኑና ቀሪው ግን የማይቀርለትን ፅዋ ተጎነጨ ! ሊተካ የማይችል ትውልድ ከሰመ ! በወታደራዊ ችሎታቸው እንኳንስ ከአፍሪካ ከኃያላን መንግስታት የጦር መኮንኖች ጋር ትምህርታቸውን ተከታትለው ባገኙት ታላቅ ውጤት የወርቅ ሜዳሊያ ያገኙት (ምሳሌ ብ /ጄ ተስፋዬ ትርፌ ) ተረሸኑ ; ተገደሉ መንገድ ላይ ቆመው ለመኑ ! አይ መኖር እኛም እየኖርን ነው .... ለዛሬ እዚህ ይብቃኝ እምባዬ ኪቦርዴን አራሰው ሞት በክብር የት ይገኛል ?

ኤግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክልን !!!

የትምጌታ

ውድ ወንድሞቼ ሀያ ሙሄ , terrible, ላሊበላ 4, እንዲሁም ቢሌ - ጤና ይሰጥልኝ !

እኔ እንኳን የኢትዮጵያ ሰራዊት ውስጥ ተሰልፌ አላገለገልኩም :: ነገር ግን ወንድሜ ሀያ ሙሄ ያነሳው የውይይት መድረክ ስቦኝ ነው የመጣሁት :: የስከአሁኑንም ውይይት በጥሞናና በሙሉ ለብ ተከታትዬዋለሁ :: መቼም ወታደሩ ብቻ ሳይሆን አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ምትክ የማይገኝላቸው የጦር መሪዎች ኢትዮጵያ እንደነበራት እንመሰክራለን :: እንኳንስ እዚህ ግባ የማይባል የወንበዴ ክምችት ቀርቶ መላዋን አፍሪካችንን ለመከላከል በቂ ችሎታ የነበረው ነበር (በወታደራዊ ብቃትም በመሳሪያ ሀይልም ):: እንዲያውም (አንድ ግዜ አንድ እህት እንደጠቀሰችው ) ለወያኔ እና ሻአቢያ መደበኛ ወታደር ሳይሆን መመደብ የነበረበት , እንደነሱ ከዋሻ ዋሻ እየዘመተ የሚገርፋቸው የሽምቅ ሀይል መመደብ እንጂ ::

ምትክ የሌላትን ነብሳቸውን ለሀገር አንድነት ሰጥተው ላለፉ ወገኖች ሁሉ የኢትዮጵያ አምላክ ነብሳቸውን ይባርካት !!! በህይወት ለአላችሁ ደግሞ እግዚአብሔር ውለታችሁን ይክፈል !!!

ከታላቅ አክብሮት ጋር ,

ወንደማሁ የትም ጌታ

Meketachew

አያ ሙሄ እንዳለው :

Quote:

እኛም ሃገርን ለመጠበቅ ወገንን ለማገልገል አስተምሮ እዚህ ያደረሰንን ህዝብ አደራ ለመወጣት አለመቻላችን ሲታወቀን ግማሾቻችን በትምህርት ስም ከአገር ወጣን ሌላውም እንደየዘመዱ ወደ መሃል አገር ነጎደ :: ምስኪኑና ቀሪው ግን የማይቀርለትን ፅዋ ተጎነጨ ! ሊተካ የማይችል ትውልድ ከሰመ ! በወታደራዊ ችሎታቸው እንኳንስ ከአፍሪካ ከኃያላን መንግስታት የጦር መኮንኖች ጋር ትምህርታቸውን ተከታትለው ባገኙት ታላቅ ውጤት የወርቅ ሜዳሊያ ያገኙት (ምሳሌ ብ /ጄ ተስፋዬ ትርፌ ) ተረሸኑ ; ተገደሉ መንገድ ላይ ቆመው ለመኑ ! አይ መኖር እኛም እየኖርን ነው

ወገን ብዙ ትዝታዎችን ቀሰቀስክ :: የቀደሞውን ጀግና የኢትዮጵያ ወታደር ልበ ሙሉ ወታደራዊ ገድል ዝንተ አለም ስናስታውሰው እንኖራለን :: ወደፊትም ደግሞ አኩሪ ተጋድሎውን በመዘከር በክብር በታሪክ መዝገብ ላይ እንዲሰፈር የሚደረግበት ወቅት እሩቅ አይሆንም :: እግዚአብሄር ነፍሳቸውን ይባርክልን :: በህይወት የሚገኙ ጀግኖች ገድሉን ለታሪክ በፅሁፍ እንደሚያስቀምጡት እገምታለሁ :: ይህም ታላቅ ውለታ ነውና :: እስከዛው አገራችን ከመሰሪዎች እንድትላቀቅ የበኩላችንን እንጣር ::

ላሊበላ 4

አያ ሙሄ ! እንዴት ሰነበትክ :: ወንድሜ አንተ ለውይይት እንዳቀረብከው

ሁሉ : የሻቢያ ብርታት የሠራዊቱ በየአቅጣጫው መሸርሸርና ከዚያ የሠራዊቱ ቆራጥ የድል እርምጃዎች ተገድበው ወደ መፈራረስ ያደረሰው ምን ይመስልኃል ?

1ኛ : ከአነሳሱ ደርጉ ሥልጣኑን እንጂ ስለ አገር ምንነትና ችግሮቹዋንም ልክ እንደ ባቢሎን ግንብ የተገነባቺዋን ኢትዮጵያ እንዴት ማስተዳደር እንደአለበት ባለማወቁ ::

2ኛ : ወታደራዊ ገዥዎቹ መንፈሳቸው በቶርነት ገጥመን አሸንፈን ሶሻሊስት ኢትዮጵያን መሥርተን ከዚያ እናበለጽጋታለን ብቻ በማለትና የራሳቸውን ልብ አዳምጠው በመነሳታቸው ::

3ኛ : ቀይ ሽብር ነጭ ሽብር እየተባለ በየመንገዱ የሰው ልጅ ተገድሎ ሬሣው ለ 12 ሰዓት ደሙ ረግቶ ዝምቦች ወረውት ህዝብ እያለፈው ሲሄድ ለመሆኑ ያመንግሥት ወይም አስተዳደር ሰው ይባላል ወይስ ምን ለማለት ይቻላል :: አንባቢ ራሳቺሁ ፍረዱት :: ፍርኃት በፍርኃት ህዝባቺን አደረጉት ::

4ኛ : ወደ ኤርትራ ከሄድን ሕዝቡ መኪናና መደብሩን ጋራዡን ቤቱን በርካሽ እየሸጠ "የናት አገር ጥሪ " እያለ ሲያፈተልክ የአስተዳደሩ ሰዎ ይህን ጉዳይ አጥንቶ የሚሄዱትን ሰዎ ሃሣብ ለማስቀየር የተደረገ የለሰለሰ ርምጃ ተወስዶ ነበር ወይ ?

5ኛ : በደርጉ ውስጥ የነበሩ ከ 8 የሚበልጡ የኤርትራ ተወላጅ ከሰሜን የመጡ አባሎች ከውስጣቸው እየፈሩ ሲከዱ ምን ዓይነት አስተሳሰብና ለምንስ እንደጠፉ ተመራምሮ ነገሩን ለውይይት ያቀረበ ነበረ ወይ ?

6ኛ : በሰሜን ማለትም በኤርትራ ክልል ውስጥ የነበረው ወታደራዊ ሁኔታስ ምን ይመስል ነበር ? ያንን ለማቀዝቀዝ ምን እርምጃ እንደተወሰደ ቢያንስ ጀነራል አማን ያመጡትን ከመቀበል ፋንታ እንደገና እሳቸውን ወንጅሎ መግደልስ ተገቢ ነበር ወይ ?

ቀጥሎም ኮሎኔል አጥናፉ አባተ በዚያ በተለሳለሰና አገር ወዳድ በሆነ ሁኔታቸው ድጋፍ ሲገባቸው እሳቸውንም ወንጅሎ መግደል ምንኛ የሚቀፍ ስርዓት ነበር ?

7ኛ : ከሁሉ የሰሜኑ ጦር ሁኔታ ያንን ጦር በስተግራው እየገባ ዘወትር በውጊያዎች ወቅት ድጋፍ የሰጡ የነበሩት እነኛ የኮማንዲስ ብርጌዶች በመጀመሪያ አዛዣቸው ፈርተው ሱዳን ገቡ :: ቀጥሎም እነሱ ከነሙሉ ትጥቃቸውና ባጄቶቻቸው የየመሣሪያዎቻቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጥይቶችና መለዋወጫቸው ጋራ ወደ ሻቢያ ገቡ ::

እነዚህ ኮማንዲሶች ታላቅ ወንድምዬው ሻቢያውስጥ ሲሆን ታናሽዬው ደግሞ እናት አገር ወይም ሞት በሚል የሚመራና በኢትዮጵያ የፖሊስ ኮማንዶነት የሚሰራ ሆኑ :: እነዚህ በዚህ ዓይነት ሲኖሩ በደርጉ ጊዜ እንዲያውም ዛቻዎች ይደርስባቸው ጀመር በዚያን የተነሳ ሻቢያ ያላሰበውን ኃይልና በትክክልም ከማንኛውም መጪ ኃይል መክተው ነጻ እንደሚያወጡት ስለ አመነ ከትንሽ ክትትል በኌላ የሻቢያ ከጓድ አንስቶ እስከ ብርጌዶቹና ክፍለጦሮቹ ድረስ እነኛን ኮማንዲስ የሚባሉትን ጎበዝ ወታደሮች አመራር ላይ አስቀመጣቸው ::

ከዚያ እንግዲህ ደርጉ ቀይ ኮከብ ነጭ ኮከብ እያለ ቢነሳ አንድ ጊዜ ያጠፋው ከፍተኛ ጥፋቱን ለመሸፈን ካልሆነ በስተቀር ያንን አካባቢ ሊቆጣጠረው አይችልም ነበር :: የመሳሪያ ብዛት ሳይሆን አንድን ተዋጊ የሚገነባው ከሁሉ በፊት ለዓላማ ዝግጁነትና አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ የሚባባልበትና የሩቅና የቅርብ ግቦቹን የሚያዩ ትውልዶች ሲኖሩት ነው :: በዚያ ምክንያት ይመስለኛል የሰሜኑ 2ኛው ክፍለጦር ያለምንም ውጤት ሊእተን የቻለው ::

ለወደፊቱ ከነዚህ ካነሳሁዋቸው ውስጥ ና ከሌሎቹም በደንብ እያሰብኩ ከውኜ እልክላቺሁዋለሁ ::

ስህተቶቻቺን ከኌላ የሚነገሩን ባለማዳመጥ ዘወትር እልኸኛ ሆነን ስለተፈጠርንና በትግስትና በለዘብታ ስለማናስብ ይመስለኛል :: ሰው ሰው የሚለውን የሚሰጠውንም ምክር መስማት አለበት ::

የአፋበት ሽንፈት የኢትዮጵያን ሽንፈቶች ሁሉ ይዞ የመጣ ነው :: በዚያው ልክ ታዲያ እዚያ የተቃጠለ አቡዋራና ትንፋሽን የሚያቃጥል ሙቀትና የገረረ ጸሐይ ውስጥ በቀበሮ ጉድኳድ ታሽጎ 15 ዓመት መኖር ወይም መቆየት ሳያንሰው እዚያ ድረስ ሄዶ አብሯቸው የኖረውንና ባለ እድለኛውን መሪያቸውን ጀነራል ታሪኩን መግደላቸው ራሱን የቻለ አፍራሽ ስራ ነበር :: ታዲያ አፋበትን ሻቢያው ሲቆጣጠር የቀዳሁትን ቪዲዮ አልፎ አልፎ ስመለከተው በሚያሳዝን ሁኔታ ቅሬታ ይፈጥርብኛል :: ስለዚይያ ጉዳይም ሁሉ አንስቼ እጽፍልኃለሁ አንተም መልስህን እንደምጸጠኝ ተስፋ አደርጋለሁ ::

ሰላምታዬ ለሁላችሁም

ይድረስልኝ

ላሊበላ 4

በተለይ " ነበር "የምትለዋን አንዲት የደርጉ የዕለት ሁኔታን ጉዳዮች የምትዘረዝርን መጽሐፍ ብታነባት የነበረው ገልቱነት ምን ይመስል እንደነበረ ታስተውለዋለህ ::

 

አያ ሙሄ

ወንድሜ ላሊበላ ጠቅለል ያለ ፖለቲካዊ ግምገማህን አንብቤዋለሁ :: ከሞላ ጎደል ብስማማም ስለአብዛዎኞቹ ከመስማት በስተቀር አስተያየት ለመስጠት በወቅቱ አልነበርኩም :: ከዘረዘርከው ውስጥ በአንዱ ነጥብ ለመወያየት እፈልጋለሁ :: በተቻለኝ መጠን ወታደራዊ ውሎዎችን ያካተተ ፖለቲካዊ ውይይት ለማድረግ እሞክራለሁ :: ጠለቅ የለ በለውጡ ጊዜ የነበረውን የፖለቲካ ጉዞ ስህተት ምንም እንኳ የምዘነጋው ባልሆንም ለህዝቡም ይሁን ለሁላችን የተሰወረ ስላልሆነ ለህዝብ በውል ያልተገለፁለትና እኛም መቋጫ ላይ ያልደረስንባቸው ክስተቶች ብንወያይ መልካም ነው :: በተለይም እርስዎ ቀደም ብለው ስለወጡ ያለፈውን ቢያብራሩልን እኔ ደግሞ ከወደኃላ የነበረውን ለመግለፅ እሞክራለሁ :: ሌሎችም ጓዶቻችን ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ተስፋ አድርጋለሁ ::

ነበርንም አንብቤዋለሁ ደራሲውንም አውቀዋለሁ :: የተዋጣለትና የላይ ከላይ ታሪክ ጠቅለል አድርጎ አንዱን ከአንዱ ሳያበላልጥ ኃቅ ለማስያዝ ሙከራ እንዳደረገ ራሴም ከማውቃቸውና በቅርብ አብረው የነበሩ አለቆቼ ከመሰከሩት ለመረዳት ችያለሁ ::

ጠቅለል ብለ መልኩ መንግስቱ ኃ /ማርያም እንዴት አድርጎ የራሱን መንበረ -ሥልጣን ሲያደላድል እንደነበርና እንዴትስ አድርጎ አብረውት የነበሩትን እንዳስወገደ ተመክተናል ::

ያም ስህተት ነው ወደ መጨረሻ ላይ ራሱ ላይ እየወጣ ሄዶ ለድርብ ድርብርብ ጥፋት የዳረገን ::

የብ /ጄ ታሪኩ አገዳደል እንኳንስ እኛን ቀርቶ የፖለቲካ ካድሬዎችንም ያስቆጣ ነበር :: እዚህ ላይ ቀደም ብሎ በተመሳሳይ ጥያቄ የ 3ኛው አንበሳ ክ /ጦር አካል የሆኑት 9ኛ እ /ብርጌድ , 10ኛ እ /ብርጌድ , 12ኛ እ /ብርጌድና 92ኛ ሚ /ብርጌድ በ 1975 ወይ እንዋጋ ወይ ጉዳዩ በሰላም እንዲያልቅ ጥረት ይደረግ እኛ ምሽግ ውስጥ መኖር መሮናል ለምንድነው ቀስ በቀስ እንድናልቅ የምንደረገው ? ደርግስ እስከ መቼ ነው የጊ /ወ /አስተዳደር የሚሆነው የሚለውን ጥያቄ በማንሳታቸው :: መንግስት መከላከያ ወረዳቸውን ለ 19ኛ ተራራው ክ /ጦር አስረክበው ወደ ቀምጭውሃ እንዲመለሱ ሲያደርግ የ 9ኛ እ /ብርጌድ አካል የሆነው 93ኛ ሻለቃና የ 92ኛ ሚ /ብርጌድ አካል የሆነው 924ኛ ሻለቃ የተሳፈሩበትን ካሚዮኖች አስገድደው አስመራ ገቡ :: አመፁ ወደ ሌሎች ክፍሎች እንዳይስፋፋ ስለተፈራ ሁሉም የ 3ኛ ክ /ጦር ብርጌዶች አስመራ እንዲገቡና እረፍት እንዲያደርጉ ትጥቃቸውንም ዓዲ ጓዕዳድ ፈትተው ኤክስፖ እንዲገቡ ከተደረገ በኃላ ከሰራዊቱ መካከል ቀንደኛ አሳዳሚዎች በመባል 19 የሰራዊቱ አባላት ተመርጠው "አብዮታዊ እርምጃ " ተወስዶባቸዋል :: አሳዛኝ መንግስት ከድጡ ወድ ማጡ እንዲሉም ተመሳሳይ ጥያቄ በሰራዊቱ ለብ /ጄ ታሪኩ በመቀረቡና እሳቸውም ለርዕሰ ብሄሩ ኃሳቡን በመደገፍ ጥያቄ በማቅረባቸው "አብዮታዊ እርምጃ እንዲወሰደባቸው " ተወሰነ :: ሜ /ጄ ራጋሳ ጂማ ከሰራዊቱ ተባረሩ :: ይህ ነው ውድቀት !

ከዚያ እነ ሃምሳ አለቃ ለገሠ አስፋው ወታደራዊ መሪ ሆነው ለሽንፈት ዳረጉን !

 

ዝርዝሩ

አያ ሙሔ በእውነት እንዴት ያለ ዘገባ መሰለህ የምትዘግበው በጣም ወደድኩት አዎ ወያኔ እና ሻእቢያ የኢትዮጵያን ሕዝብ በጦርነት አሸነፍን ብለው አፋቸውን ሞልተው አያወሩም እጅግ ውስብስብ በሆነ ሆዳም ሴራ እንጂ ::አንድ ቃለ መጠይቅ ላስታውስህ ኮ /ል ተስፋዬ ወ /ስላሴ በአንድ ወቅት ለአንድ መጽሔት የሰጡትን "ኤርትራ እንድትገነጠል ኢትዮጵያንም ለዚህ ካበቋት ምክንያቶች አንዱ እኔ በመሆኔ እጅግ በጣም አዝናለሁ " ብለዋል ታዲያ ማዘን ምን ጠቀማት ለአገራችን "ፊቱን ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያረጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ " ይላል ያገሬ ሰው አዎ ያጓንዋት ድንጋይ ተመልሳ ባናት እንዲሉም ለሞት ፍርድ በቁ እሳቸውም :: ሰዎች ዛሬም የምንሰራውን የማናውቅ ወይም ለጊዜያዊ ጥቅሞች ሆዳችንን በማገልገል ላይ ያለን አለን የኌላ መጸጸት አንድም ጊዜ ወደ ኌላ ሊመልስ እና አገራችንን ሊታደግ አይችልም እና ዛሬውኑ አረማመዳችንን እንመርምር ::አቶ ሙሔም የቀድሞ ጦር በሰፊው ሊዘከር ይገባዋል እንዲያውም የራሱ ዌብ ሳይት ቢኖረው ታሪካዊ ነት ነው እና በደንብ ቢታሰብበት ደስ ዪለኛል በጣም ነው ያከበርኩህ ደህና ሁንልኝ

ላሊበላ 4

ሠላምታዬን አቀርባለሁ አያሙሄ !

ድንቅ ትንተናሕ ደስ አሰኝቶኛል :: አዎ ኮሎኔል መንግስቱ ህእ / ማርያም ላይ ይሄዳል ያሁሉ ጥፋት ::

1ኛ : ሠራዊቱ በሳቸው ብቻ እንዲያም አድርገው ቀርጸው በመገንባታቸው :: እሳቸው ከሌሉና ከሄዱ ምን ሊደርስ እንደነበረና እንደደረሰም ታይቷል ተፈጽሟል ::

2ኛ : ከፍተኛ ወታደራዊ ብቃት የነበራቸውን መኮንኖች ኮማንደሮቻቸውንና የበታች ሹሞች ሳይቀሩ መፍጀታቸው ::

የናቅፋው ብቻ ሳይሆን ማሕበር የነበሩት የ 34 ሻለቃን አዛዥ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ኮሎኔሉ መተው የገደሉዋቸው በሠራዊቱ ፊት ::

3ኛ : ከረን የነበረውን 12ኛ ብርጌድና በስሩ የነበሩትን / 31-35-30ኛ ሻለቆችን 2ኛ ሻለቃን ጭምር ማንሳት አልነበረባቸውም :: ከዚያ በኌላ ነው ሣህል አውራጃ ውስጥ ሻቢያ በግልጽ መንቀሳቀስ የጀመረው ::

4ኛ : ወታደራዊ መንግሥት ደግሞ ከ 3 ወር በኌላ ወደ ካፑ መመለስ ነበረበት :: ይኼንን ቢያደርግ ኑሮ ወያኔም አትመሰረት ነበር :: ሻቢያም ለከፍተኛ አገራ አውዳሚ ትግል አስቦ ባልተነሳም ነበር ::

ለአገራቺን ከቀድሞ እስካሁን ይህቺን የሥልታን ቦታ ለመድረስ የያዘውም አልሰጥም በማለት አገራቸውን እያወቁ ሲያፈርሱ ኖረዋል :: ካሁንስ በኈላ ምን ዓይነት ኢትዮጵያ ትኖረናለች ?

እንግዲህ ያወታደራዊ መንግሥት በምንም ዓይነት ስልጣን መጨበጥ የለበትም ነበር :: ሲቪሉ ውስጥ አገር መሪነትን ሊረከቡ እንዲቻል በፓርቲዎች ተደራጅተው እስከሚመጡ ድረስ ብቻ የአደራ መንግስት ብቻ ይዞ መቆየትና ለመልቀቅም ሲጠየቅ ወዲያውን ሻንጣውን ይዞ ወደ ጦር ካምፑ መግባት ነበረበት ::

ያጥፋት የዛሬዋን ኢትዮጵያ እንድናይ አድርጎናል :: የነገውንስ ቢሆን ማን ያውቃል ::

አክባሪህ

ላሊበላ 4

 

 

በይሉል

አያሙሄም ሆነ ላሊበላ ቆንጆ ዉይይት ይዛችሁዋል .

ያለፈዉን በሚገባ መተቸት እና ለወደፊቱ የሚሆን ብልሀት መቀየስ የሚቻለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው .

ባለፈው ላይ ብዙ መቆየትም ጥሩ አይደለም . የሚገኘውን ልምድ እና እዉቀት ይዞ በፍጥነት መነቃነቅ ጠቃሚ ነው .

 

እኔ መለዮ ለባሽ ባልሆንም ምጽዋ ----መርሳ ፋጡማ --- ጢዮ -- በይሉል ---አሰብ በመሳሰሉት አካባቢዎች ከጀብሀ ጀምሮ እስከ ሻእቢያ የነበሩትን እንቅስቃሴዎች ከሞላ ጎደል አዉቃለሁ . ሰራዊቱ በሚገባ ተዋግቶዋል . ደሙንም አፍስሶዋል . አጥንቱን ከስክሶዋል .

በስሙም ተነግዶዋል . በገንዘቡም ዉስኪ ጨልጠዉበታል ----ደመወዙንም ቁማር ተጫዉተዉበታል . ኮንትሮባንድ ነግደዉበታል .

ንጹሀን ዜጎችን እያፈኑ ቶርች ያደረጉ አዛዦችን አዉቃለሁ . የአባወራ ሚስቶችን የሚያማግጡ ---በማካሮቭ ሺጉጣቸው ኢሰባዊ ድርጊት የሚፈጽሙ ----ህዝቡን ---ነጋዴዉን ያማረሩ ሁሉ እናዉቃለን . ወያኔ እና ሻእቢያ ጉያ እንድንጠለል ምክንያት የሆኑ አዛዦች አዉቃለሁ .

ጭቁኑ ወታደር ደሙን እያፈሰሰ --አጥንቱን እየከሰከሰ ለሀገሩ በሚገባ ተዋግቶዋል .

በታሪካችን ዉስጥ ተገቢዉን ስፍራ ይዞ ለልጅ ልጆቻችን ይተላለፋል .

እነጉዋድ ፈርጣጭ ጄኔራልም በአሳፋሪ ታሪካቸው ለዘላለም እንድናስታዉሳቸው ስላደረጉ ምስጋናችንን እናቀርብላቸዋለን . የወደፊቱ ትዉልድም በሚገባ ይማርባቸዋል .

 

አያ ሙሄ

በመጀመሪያ ወታደራዊ ሠላምታ

3ኛው አንበሳው ክ /ጦር ከአመፁ ማግስት ያጋጠመው ዕድል ቢኖር የአመፁ መሪዎች መረሸን እንደነበር ከላይ አስቀምጨዋለሁ :: ከዚያስ .....

የአመፁ መሪዎች መረሸናችው እንደታወቀ በክ /ጦሩ ብርጌዶች መካከል የሚተላለፉት የመገናኛ መልዕክቶች ጥብቅ ክትትል እንዲደረግባቸው ከበላይ አካል መመሪያ ተሰጠ ::

(በነገራችን ላይ አንበሳው 3ኛ ክ /ጦር የርዕሰ ብሄሩ እናት ክፍል በመሆኑ አብዛኛውን የጦር አዛዦችና ፖለቲካ ካድሬዎች ክስተቱን ለማርገብና ዝናውን ላለማጉደፍ ሲያሳዩት የነበረውን ከፍተኛ ጥረት ሳልገልፅ ለማለፍ አልፈልግም )::

ከአመፁ በኃላ ክ /ጦሩን የመከላከያ ወረዳ ማስያዝ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዝን ስለሚችል በኤርትራ ዳጋማዎች አካባቢ የአሰሳና በተለይም ደቀመሃሪ አካባቢ (ማይ ዕዳጋ ) የነበረውን አፈር ቁፋሮ (ለብርጭቆ ፋብሪካ የሚውል አፈር ) ይጠብቅ ነበር :: ከዚሁም ጋር በተደራቢ ከሳህል ወደ ዳጋማው (ከበሳ ) የኤርትራው ክፍል የሚንቀሳቀስውን የሻዕቢያ መፈናፈኛ አሳጥቶም ነበር ::

3ኛ ክ /ጦርን ከሌሎች ለየት የሚያደርገው የውጊያው ችሎታው "ቆረጣ " የሚባለው ሲሆን ከሚታወቁት የጎሬላ ውጊያ ታክቲኮች አንዱ ነው :: ሠራዊቱም የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው የበታች ሹማምንትና በተለያየ ጊዜ የሰለጠነ ስብጥር ችሎታ ያለው ሰራዊት ነበር :: እዚህ ላይ የክ /ጦሩ አዛዦችና ብርጌድ አዛዦችም ተሰሚነት የነበራቸውና የየራሳቸውን የውጊያ ስልት የመንደፍ ስልጣን የነበራቸው ነበሩ ብል ማጋነን አይሆንብኝም ::

ክ /ጦሩ በኤርትራ ደጋማ ክፍሎች ለ 5 ወራት ከቆየ በኃላ በየካቲት 1975 አካባቢ ወደ ትግራይ እንዲቀሳቀስ ተደረገ :: 9ኛና 12ኛ እ /ብርጌድ ሽሬ (ከሽሬ -ዓዲ ዳዕሮ ) 10ኛ እ /ብርጌድ አክሱም 92ኛ ሚ /ብርጌድ ዓድዋ ላይ ሆኖ ከኤርትራ የሚመጣውን ኮንቮይ እንዲያጅብ ተደረገ :: በወቅቱ 17ኛ ክ /ጦር ሽሬ አካባቢ ሆኖ በምዕራብ ትግራይ የነበረውን የወያኔን እንቅስቃሴ በመቆጣጠርና አንዳንድ አካባቢዎችንም በመቆጣጠር ትዕዛዝ ይጠባበቅ ነበር ::

አስፈላጊው መሰናዶ ተጠናቆ የውጊያ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ሽሬ ላይ በብ /ጄ አበበ ገብረየስ ስብሰባ የሚመራ ስብሰባ ተደረገ :: የመሰብሰቢያ ወረዳውን ዓዲ ዳዕሮ ላይ ያደረገው 3ኛና 17ኛ ክ /ጦሮች , ብርጌዶች አዛዦችና ፖለቲካ ኃላፊዎች ስብሰባው ላይ ሲገኙ በውጊያው ትዕዛዝ ላይ የ 10ኛ ብርጌድ አዛዥ አሰላለፍን አስመልክቶ የውጊያው ዕቅድ እንዲቀየር ኃሳብ በመቅረቡ ሁሉም አዛዦች ተስማምተውበት የሚከተለው ዕቅድ ተግባራዊ ሆነ ::

1. 9ኛና 12ኛ ብርጌድ ከዓዲ ዳዕሮ ፍጥነት ባለው መጓጓዣ ወደኃላ ተመልሰው ወደ እንዳባጉና በመጓዝ በእግር የተከዜን ወንዝ ተከትለው ወደ ሰሜን ምዕራብ እንዲያስሱ .

2. 10ኛ ና 92 ብርጌድ ከዓዲ ዳዕሮ በእግር በመጓዝ ጠላት ለመከላከል ከተዘጋጀበት የፃዕዳ ምድሪ ምሽግ ጀርባ ባልታሰበ ሁኔታ እንዲገባና ዓዲ ሃገራይን እንዲቆጣጠር ከዚያም ከኤርትራ በትኮምቢያ በኩል ከሚመጣው የሰንጥቅ ሜካናይዝድ ጋር ሽራሮ ላይ እንዲገናኝና ፊቱን ወደ ተከዜ በማዞር ተከዜ ላይ ከእንዳባጉና ከሚመጡት 9ኛና 12ኛ ብርጌድ ጋር እንዲገናኝ ;

3. 17ኛ ክ /ጦር ደግሞ በወገን እንዲያዙ የተፈለጉት ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን ከተሞች ላይ እየተከታተለ የመከላከያ ወረዳውን እንዲመሰርትና ለሚደረጉት መንግስታዊና ህዝባዊ መደራጀቶች ጥበቃ እንዲያደርግ ;

በዚሁም መሠረት በጥቂት መስዋዕትነት አካባቢውን በቀላሉ በመቆጣጠር የወያኔን ኃይል እየተከታተለ እያባረረ ወደ ዳባትና በኃላም ወደ ኤርትራ ዘለቀ ::

እዚህ ላይ የአድዋና የሽሬ ሲቪል ህዝባዊ ሰራዊቶች ከሠራዊቱ ግንባር ቀደም በመሆን የወያኔን ዱካ በመከተል በመረጃና በቅኝት ያደረጉትን አስተዋፅኦ ስላደንቅ አላልፍም ::

3ኛ ክ /ጦር ባርንቱ ላይ ለጥቂት ቀናት እንዲያርፍ ከተደረገ በኃላ የ 2ኛ ክ /ጦር መለብሶ ላይ ከሻዕብያና ወያኔ ጥምር ጦር ጋር የሞት ሽረት ትንቅንቅ ላይ መሆኑ ስለታወቀ 3ኛ ክ /ጦር መንጥር ዕዝ ቀዳሚ መምሪያ (መለብሶ ) ሄዶ ሪፖርት እንዲያደርግ ትዕዛዝ ደረሰው :: መጓጓዣውም በፍጥነት ደረሰ :: መቼም ሁሉም በቅንነት ኃላፊነቱን ሲወጣና ነገሮች ሲስተካከሉ ያለው ደስታና የሞራል ንቃት መግለፅ ያዳግታል ::

2ኛ ክ /ጦርን ለመርዳት ወደ መንጥር ዕዝ ሲከንፍ የነበረው 3ኛ ክ /ጦር ብቻ ሳይሆን ከናደው ግንባርም 18ኛ ተራራ ክ /ጦርም ነበር :: የሶስተኛ ክ /ጦር አካል የሆነው ግንባር ቀደም ሻለቃ መንጥር ዕዝ ማዘዣ አካባቢ ሲደርስ የዕዙ አዛዥ የነበሩት ብ /ጄ ረጋሳ ጂማ (በኃላ ሜ /ጄ ) ሽጉጣቸውን በእጃቸው ደግነው ከውጊያው አጭር ርቀት ላይ ሆነው ነበር ያገኛችው :: የሻለቃው ዘመቻ መኮንንም ማንነታቸውን እንደለየና ስሜታቸውን እንደተረዳ ; ጌታዬ ተመልሰው ማዘዣ ጣቢያ ላይ የማይሄዱ ከሆነ ለበላይ አሳውቄ በቁጥጥር ስር ላውሎት የምገደድ መሆኑን ላሳውቆት እወዳለሁ ሲላቸው ! መቶ አለቃ አንተ ብቻ ቶሎ ተንቀሳቀስ እኔ ምንም አልሆን ብለው ከሰራዊቱ ጎን ለመሰላፋቸው ትዝታዬ ነው ! እንዲህ ያሉ መሪዎቻን ነበሩ ...

ይቀጥላል !!!! የትዝታ ተምስጦ ሲያጠቃኝ መስመሬን ስለምስት ፅሁፌን ለማቋረጥ እገደዳለሁ

የውቃው ዕዝ መደምደሰስ ምክንያትና የቦታው አቀማመጥ

ውቃው ዕዝ የነበረው አልጌና በተባለው የቀይባህርን ተከትሎ ከቃሮራ ጀምሮ የሰሜናዊ ምሥራቅ የሳህል ተራሮችን በመቆጣጠር ነው :: መጀመሪያ ላይ ወደ አልጌና ለመሄድ የሚቻለው በመርከብና ጀልባ ብቻ ሲሆን በኃላ ላይ ግን በመንገድ መጓጓዣም ለመገናኘትም ተሞክሮ ነበር :: የቦታው አቀማመጥ አስቸጋሪና ለፍጡራን የማይመች ቦታ ነው :: የሚጠጣ ውሃ ለማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ሲሆን የናቅፋን ተራሮች አሽቅቦ የሚመለከት ሰንሰላታማ ተራራ የተሞላ ነው :: ተራራው ላይ ለመውጣት ጉልበት ብቻ ሳይሆን ብልሃትም ያሻል :: ለምሳሌ እንደ መርከብ በመሳሰሉት ተራሮች ላይ ሰራዊትን ለማሰለፍ እጅግ አስቸጋሪና ለየት ያለ ወታደራዊ ዕቅዶች የሚያስፈልጉት ጉዳይ ነው ::

አልጌናን ለመቆጣጠር በሩስኪ አማካሪዎች (01 ጓዶች ) የተጠናውን ቋሚ የመከላከያ እቅድ በመቃወም ; የቀድሞው ውቃው ዕዝ አዛዥ ብ /ጄ አበራ አበበ "በቋሚ ሠራዊት ከማስያዝ ይልቅ በኮማንዶና አየር ወለድ ማስጠበቅ " ይሻላል ብለው ሃሳብ ቢያቀርቡም ተሰሚነት ባለማግኘታቸው ውጤቱ እንደተፈራው ሆነ ::

አልጌና በቋሚ መከላከያ ለመያዝ እስከ 5 ክ /ጦር የሚደርስ ኃይል የሚያስፈልግና በባህሩ አቅጣጫ ያለውን ሜዳማ ክፍል ለመቆጣጠር አንድ ሜካናይዝድ ክ /ጦር በተደራቢነት ያስፈልግ ነበር :: ይሁንና ከቀይ ኮከብ ዘመቻ መክሸፍ ጋር ተዳምሮ ብዛት ያላቸው ዕዞች የኃይል መመናመን ተፈጥሮ ስለነበር የውቃው ዕዝ በ 15ኛና 23ኛ ክ /ጦሮች ብቻ እንዲወሰን ተደርጎ ነበር :: ከዚህ በተጨማሪ የዕዙ አዛዥ ተነስተው ምክትል አዛዡ ብ /ጄ ሁሴን አህመድ አዛዥ ሆነው ነበር ::

ሻዕቢያም በበኩሉ አልጌናን (መርሳ ፋጡማ ) ለወደብነት የፈልገው ስለነበርና ሠራዊቱ እጅግ ሩቅ ስለሆነ ነጥሎ መምታት ይመቸው ዘንድ ከጀርባ በኩል ዞሮ ለመምታት እንዳቀደ የ 23ኛ ክ /ጦር አዛዥ የነበሩትና የኤርትራ ክ /ሃገር ተወላጅ የሆኑት ኮሎኔል መሐሪ ምስግና በመረጃ ስለደረሱበት ሠራዊቱ የመልሶ ማጥቃት ዝግጅት በመድረጉ ሻዕቢያን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ መልሶት ነበር :: ይህ ትልቅ ሽንፈት የደረሰበት የሻዕቢያ ኃይል ከሁሉም ግንባሮች ሠራዊቱን በማሰባሰብ ባልታሰብ ሁኔታ ማጥቃቱን ሰነዝሮ የዕዙን ማዘዣ በመቆጣጠሩ የዕዙን ም /አዛዥ ኮሎኔል ግርማ ተሰማ የዕዙ ድርጅት መምሪያ ኃላፊ ሌ /ኮሎኔል ሐድጉ ከሌሎች መምሪያ መኮንኖች ጋር ሲማረኩ የዕዙ አዛዥ እንዲሁም የ 23ኛ ክ /ጦር አዝዥ የነበሩት ኮሎኔል መሐሪ ምስግና ከጥቂት ሠራዊት ጋር አምልጠው ወጡ ::

ብ /ጄ ሁሴን አህመድም በሜ /ጄ መርዕድ ንጉሴና ሌሎች ጥረት ከመረሸን ድነው የመክት ዕዝ አዛዥ እንዲሆኑ ተደረጉ :: በኃላም እስከ መጨረሻው ሜ /ጄ ሆነው የሁአሰ አዛዥ ነበሩ ::

ላሊበላ 4

አያሙሄ ! አዎ የምትላቸው ሁሉ ትክክሎቺና የነበሩም ነበሩ :: እንዳልከው ያቺ ናቅፋ ብዙዎቹን የኢትዮጵያን ልጆች ተፈታትናለች ::

አብዮቱ ከመፈንዳቱ 1 ዓመት በፊት ፋሲካ ሲፈሰክ የነበርነው እዚያ ነበር :: እጅግ የክረምት ዝናብና ጋሌታና ኢንኮዶ ብቻ ተቋድሰን አሳለፍነው ሁሉም በጊዚያዊ ምሽግና በጥበቃ ላይ ሆኖ ::

አልጌና የነበረው ከባሌ ክፍለ ሀገር ተቀይሮ የመጣው 2ኛ ሻለቃ ነበር :: ይህ ሻለቃም እድለኛ አልነበረም :: ዘወትር የሻብ ዕያና የጀብሐ ወንጭፎት ያጠቁት ነበር :: ሠራዊቶች ደግሞ ደፋር ጀግኖች ነበሩ ::

እነዛ ወታደሮች ከመሪዎቻቸው ጋር ሆነ ሻቢያ እስካለበት ደጃፉ ድረስ ሄደው አልቀው ነበር :: ለነሱ እርዳታ ለመድረስ ነበር ወደዚያ የሄድነው ::

የ 12ኛ ብርጌድ አዛዡ ደግሞ የ 2ኛ ሻለቃ አዛዥ ሆነው ባሌም አብረዋቸው የኖሩ ኮሎኔል ከበደ ይባላሉ :: ይወዱዋቸዋል የቀድሞ ክፍላቸውን እሳቸውም ልጆቼ እያሉ ነበር በሄሊኮፕተር ሳይቀር ሄደው የሚጎበኙዋቸው :: ያንን ያንን መሳይ ስመለከት ደስ ይሉኝ ነበር ኮሎኔሉ ::

ሞራል ያላቸና አስተዋይ መሪም ነበሩ :: ከዚያ አንድ ሻምበል ጦር በሙሉ በአልጌና በስተግራ በኩል ባለው ተራራ

አልፈህ ስትሄድ የተቀጣጠለ ተራራ ታያለህ ሻቢያ በነዚያ ተራሮች ላይ ክንዱን አስፍቶ ተቆጣጥሮታል :: እናኛ ተዋጊ ሻምበሎችም ግንባሩ ላይ መጡለት መሬቱ ደግሞ ገዥ መሬት ሳይሆን ሜዳ ነው :: በዚያ ምክንያት ሳያንቀሳቅሳቸው የጥይቱ ቀለህ የተኮሱት በየአንዳንዱ የወደቁት ወንድሞቻቺን ፊት ተከምሯል :: ታዲያ ያንን መረጃ ያቀናበረ የ 2ኛ መምሪያ መኮንን ተሳስቶል :: ያንን ሁሉ የሻቢያ ተዋጊ አንድ ሻምበል ሄዶ ፓትሮል አድርጎ ይምጣ ብሎ ማሳመኑ ያስገርም ነበር ::

ተዚያ ያተራራ ደብረሳላ ይባላል :: ካቆርደት በላይ ጀምሮ እስከ ሱዳን የሚዘልቅ ተራራ ነው :: እነኛን የሞቱትን ወታደሮች ከነመሪያቸው በሚገባ ጉድጓድ ምሰው ቀብረው ክርስቲያኑን የእንጨት መስቀል እስላሙንም የእንጨት የስላሞች ምልክት በማድረግ ነበር ጥለው የሄዱት ሻቢያዎች :: ጠመንጃቸውንም የሚፈልጉትን ወስደው የቀረውን በየመቃብራቸው ላይ ሰክተው ከዚያም ሄልሜታቸውን ሳይቀር ተውት ሄደው ነበር :: ለምን ያንን አደረጉ ? አዎ ወታደሩ ብቻ ነበር ሄልሜት የሚያደርገው ሻቢያዎች ሄልሜት ማድረጉ ኪሎ ጨምሮ ለኮማንዲሶችና ለ 31ኞች ለ 35ኞች ለ 30ኞች የሚያጋልጣቸው የሚያደክማቸው እንደሆነ ይረዱታል ::

ከዚያ ወደ ቃሩራ ስናመራ ደግሞ ጀበኃዎች ጠበቁን :: የተድላ ባይሩ ልጅ ነበር ለጥቂት ነው ከዚያ ትንሽ ተራራ ስር ያመለጠን :: በዚያም ምክንያት ወደ 2 ወር እዚያ ሰፈርን :: ተወኝ ጋሌጣው ሰለቸን :: እንጀራ አማረን :: ንፋሱ (ከምሲኑ ) አይናቺንን ሊያጠፋው ደረሰ :: መነጽር የሚባል አይገኝ :: በመጨረሻ ወደ ቃሩራ ለቀን ለ 2 ቀን እንድንሄድና የኢትዮጵያና ሱዳንን ጠረፍ ሁኔታ እንድናይ ተፈቀደ :: ጉዞ ወደዚያ አደረግን ::

ስንመለስ ወደ አልጌና ሳይሆን የምንሄድበት በጣሊያኑ ምሽግ በኩል ባለው መሬት ሆነ ሻቢያ አድፍጦ እንደሚጠብቀን ስልሚታወቅ እኛም አሳሳትናቸው በቀጥታ ከታች ስንመጣ አመራሩ የያዘው ወደ ናቅፋ የመግደያ መሬቶች ውስጥና የዚያ የሠማይ ስባሪ ወደሚመሳል ተራራ ነበረ ::

አዛዡ ወዲያውኑ አቅጣጫህን ቀይር በሚል ትዛዝ በመስጠታቸው መኪኖቹ ሁሉ ወደ ጣሊያን ምሽግ ፊታቸውን እየዘፈኑ መለሱ ::

ታስታውስ እንደሆነ ያየጣሊያን ምሽግ ተሰርቶ የነበረው ጣሊያኖች በዚያ በኩል ጃንሆይ ስለሚመጡ ይዘን እዚህ ውስጥ እድሜ ልካቸውን ሙሉ እናስራቸዋለን ብለው የሰሩትና በጣም የስትራተጂም ቦታ ነው ::

አልቀረም ጀበሃዎች በቀበሩት ጸረ መኪናና ሰው በቤንዚን ጭምር አጥምደው ቆዩን የፊተኛው መኪና ቃኝዎችን እንደያዘ ከ 27 ሰዎች ጋር ነደደ :: እንግዲህ አስበው ወንድሞቻቺን ቅድም ያየናቸውን ከ 3 ደቂቃ በሁዋላ አጣናቸው ::

እንግዲህ እነኝህን ቦታዎች የምናስሳቸው የነበረው ቢያንስ 1 ሻለቃ ወይም 2ሻለቃዎች ሆነን ነበር :: ኮማንዲሶች ግን ራሳቸው በሻለቃ እንኳን ባይሆን 3 ሻምበሎች ዘወትር ከጎናቺን ይሰለፉ ነበር ::

ባጣም አድርጌ የማናደንቃቸው ናቸው ኮማንዲስ የሚባሉት :: ወንድሙን ሳይቀር አይምሩም ከአገር ቤት ነው መተው የሚቀጠሩት በዝዚህ ላይ ከትግርኛ በስተቀር አማርኛ አይቺሉም :: እውነተኞች ናቸው :: ማዕረግ ሲያገኙ ደግሞ ጀበኃውንም ሆነ ሻቢያውን እየተኮሱ ሄደው ማጅራቱን ይዘው ነው የሚያመጡት : ያኔውኑ ም /መ : ይሰጣቸዋል :: ያንን ጓደኛው ታየ ነገ ጠዋት ፎክሮ ይሄድና ጀበኃዎቹን ሰብስቦ ይመጣል ልክ ጓደኛው ያገኘውን እድገት እንዲሰጠው በአይኑ ይጠብቃል :: መቸስ የሚያስደንቁኝ ሰዎች ነበሩ ::

የኮሎኔል መንግስቱ ስህተት የነኛን የኮማንዲሶች አዛዥ ባያስሩ ባያስፈራሩ ኑሮ ወደ ሻቢያ አይገባም ነበር :: ከዚያም ዕድገታቸውን ክብካቤያቸውን በሚገባ ጠብቀው ቢያዙ ኑሮ ኢትዮጵያ ብዙ ሠራዊት በዚያ በኩል ማሰለፍ አይኖርባትም ነበር :: ታናሽዬው ኮማንዲስ ሲሆን ታላቅዬው ጀበሐ ወይም ሻቢያ ይሆኑ ነበር :: አንድ ቤተሰቦች ስለነበሩ ልብ ለልብ ይተዋወቁ ነበር ::

ያአልሆነም የሚያሳዝነውም እንደዚያ ያለው ሁኔታን በትግስት ተቻቺሎ ቢያዙ ነበር ጥሩ ውጤቶችን ያተርፉልን ነበር :: እስራኤሎች የ 40 ዓመት የእንኮዶ ስጋ ለሠራዊታቸው የሚሆን ተከፍሎ ነው እነኛን ኮማንዲሶች መጥተውና እነሱም በመርከብ እስከዚያ እየሄዱ በሚያስደንቅ ውጤት ተምረው የሚመጡ የነብርቱት ::

አሁን የምትለኝ ሁሉ የኮሎኔሎቹ ተከቦ መማረክና እንዲሁም ለማምለጥ ጥረት ያደረጉት ጭምር ራሱ ድፍረት ነበር :: ዕቅድ ወጥቶ ሁኔታው ተጣርቶና የሚመጣው ውጤትም ተገምቶ ከተሰራ በኈላ ነበር የሚዘመተው :: ደግሞ ሽፍታ እንደሚያደርገው ተኩስ እንጂ አንድ ሰዓት ችለው ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጋራ አይዋጉም ነበር :: ሳታስበው ግን ብዙ ጉዳት ያደርሱብን ነበር :: ለማንኛውም ላሁንም ሆነ ለወደፊቱ የአገራችን ሰራዊ የምመክረው ! (ላብ ማፍሰስ ከደም መፍሰስ ያድናል ) ምንጊዜም ገዥ መሬቶችን ለመያዝ መሽቀዳደም ይገባል :: የጠላትን ሁኔታና የአመራሩን የሞራሉንና የዲሲፕሊኑን የማጥቃትና የመከላከል አቅሙን ሳያጣሩ ጠላቴ ነው ብሎ ፊት ለፊት ከመግጠም ይልቅ ብልኃት ማሰብ ይገባል :: ከዚያም በሚቻልህ ሁሉ ከጠላትህ ጋር ማታ አትግጠመው ::

ጭላማን ተገን አድርገህ እተኛበት ቦታ ድረስ ሄደህ አተራምሰው በዚያን ጊዜ ድሉ ያንተ ይሆናል ::

የወሎውን የንጉሥ ሚካኤልን ግዙፍ ሠራዊት ጉድ ያደረጉት በሌሊት በተኛበት ሄደው ነው : ንጉሱንና ሠራዊታቸውን በ (ሠገሌ ጊዜ ) የማረኳቸው ያባይሆን ኖሮ ኢትዮጵያ ገጽተዋ እስካሁን አይለወጥም ነበር ::

ልጅ ኢያሱ ዳግማዊ ምኒልክ ከህጻንነታቸው ጀምሮ በመከሩዋቸው መሠረት ትግራይና ወሎ ውስጥ 350ሺህ ሠራዊትን አሰልጥነው በቀጥታ ጣሊያን