የኔ አየር ሃይል !
ከመቶ አለቃ መኮንን !
ጸሀፊው - ቢሌ  ኣቀናባሪ - አሚጎ

አንድ ወቅት የአየር ሀይል ወታደር ነበርኩ … .ወታደር ሆኘ ብዙ እንደኔው ወታደር የሆኑ ጓደኞች አሉኝ…አንዳንዴ እኔ እንደወታደር ሆኘ ስናገር ሌላው ሰው ይገባው ይሆን እላለሁ በቅን ልቦና ነው እንደተባለው ሰው የወለደውን ሲስሙለት የፃፈውን ሲያነቡለት ይደሰታል።
ከወታደሮቹ ሌላ ሲቪል የሆኑ ጓደኞች አሉኝ የወታደሮቹ ጓደኝነት የወንድም ያህል ቢሆንም የሲቢሎቹም ያው ነው … .እና አንዳንዴ የሲቢል ጓደኞቼ ይጠይቁኛል እስቲ ስለአየር ሃይል ንገረን ይሉኛል… .እንዴት ነው የአገር ድንበር በአየር የሚጠበቀው ይሉኛል… መስመሩ የቱ ጋ ነው ይሉኛል… አውሮፕላን እንዴት ይዋጋል ይሉኛል… ሌላ… ሌላም ለኔና ለጓደኞቼ ቀላል የሆነ ግን ለማያውቀው ሰው ትንሽ ግር የሚል ጥያቄ እጠየቃለሁ የምናገረው ከባለሙያነት አንፃር ስለሆነ ቃላት መርጬ አስተካክየ ነው … .እንደወረደ ነው… .እንድንግባባ ነው።
የማንኛውም አገር አየር ሃይል የሚጠብቀው የአገሪቱን የአየር ክልል ቢሆንም ካሉት ሰፊ የስራ ድርሻዎች አንፃር በማንኛውም ጊዜ የሲቢል አየር መንገድ ሊያደርገው በማይችለው ቦታ ሁሉ አየር ሀይል የማጓጓዣ እና ለአስቸኳይ ጊዜ የሚደርስ እርዳታ እንደማንኛውም እግረኛ ወታደር በአየር ተጉዞ ያደርሳል ይህ ሲደረግ የነበረ ነው።
አየር ሃይል <ቤተሰብ > ነው ይባላል ይህ ትልቅ አባባል ነው ይህ የተባለው አየር ሃይል በአንድ ቡድን በአንድ ግለሰብ ብቻውን የሚሰራ ስላልሆነ ነው … .ግልፅ ለማድረግ የአየር ሃይል የመጨረሻ ግብ አውሮፕላኑን አየር ላይ አውሎ ግዳጅ መፈፀም ቢሆንም ያን ለማድረግ ግን ከተራ ተላላኪ ጀምሮ እስከ ምግብ ቤት አስተናጋጅ ድረስ ለዚያ ግዳጅ የየራሳቸው ድርሻ ስላላቸው ነው … ..እስቲ አንድ ጠዋት አየር ሃይል ጊቢ ልውሰዳችሁ ።
ጠዋት ተላላኪው ቴሌግራም ይዞ ከዘመቻ ሲሮጥ በረራ ሜዳ ይደርሳል ያን ሰአት በራሪ ፓይለቶች ቁርስ እየበሉ ይሆናል ይህ መዘጋጀት ያለበት ምግብ ቤት ነው ቴክኒሽያኑ አውሮፕላኑ ለበረራ ዝግጁ መሆኑን ቼክ ያደርጋል ይህ የሞተር ቴክኒሽያን ነው የአውሮፕላኑ አካል ቴክኒሽያን ደግሞ አውሮፕላኑ መላ ሰውነቱ ደህና እንደሆነ እየዞረ አይቶ የራሱን ሪፓርት ይፅፋል ድንገት አውሮፕላኑ አየር ላይ ሆኖ ችግር ቢደርስበት ፓይለቱን ለማትረፍ የፓራሹቱን ስራ ባለሙያው ልክ መሆኑን ያረጋግጣል ይህ ከሆነ በኋላ በተለየ መልኩ የሰለጠነ የአውሮፕላኑ መገናኛ ሰራተኛ የአውሮፕላኑ የውስጥ መገናኛ በደንብ መስራቱን ያረጋግጣል ይህ ሁሉ ሪፓርት ከቀረበ በኋላ አውሮፕላኑ የሚሄደው ጠላትን ለመደብደብ ወይንም ወደ አስጊ ወረዳ ከሆነ ትክክለኛው መሳሪያ ይጫንለታል ይህ በአውሮፕላኑ ዙሪያ የሚደረግ ሲሆን በምድር ደግሞ የምድር መገናኛ ቴክኒሽያኖች አውሮፕላኑ አየር ላይ ከወጣ በኋላ እንዴት እንደሚያገኙት መሳሪያቸውን አዘጋጅተው ይጠብቁታል ከነዚህ መሳሪያዎች ውስጥ አንዱ < ቢከን > የሚባለው ሲሆን ይህ መሳሪይ አውሮፕላኑ ከየትኛውም ክልል በየትኛው አቅጣጫ እንደሆነ አውሮፕላኑ ውስጥ ያመለክተዋል ።
ሌላው ደግሞ <ጃይሮ ኮምፓስ > ሲሆን ይህ አውሮፕላኑ ከተነሳበት ወይንም ማረፍ ከሚፈልግበት አውሮፕላን ማረፊያ ድርስ ምን ያህል ርቀት ላይ እንዳለ ወይንም ምን ያህል ርቆ እንደሄደ ያሳየዋል ይህ መሳሪያ ለለሊት በረራ እና በደመና ወይንም ጥሩ ባለሆነ የአየር ጠባይ የሚረዳ መሳሪያ ነው በተለይ ለጀማሪ ፓይለቶች እንደ መሪ ሆኖ የሚያገለግል ነው።
ለዚህ ሁሉ ደግሞ እንደአንድ ንጉስ ዙፋኑ ላይ ቁጭ ብሎ አንተ በዚህ አንተ በዚህ የሚል የታወር ማን ይኖራል የታወር ማን እያንዳንዱን ሴክተር ወይንም አካባቢ ለይቶ የሚያውቅ ሲሆን በአየር ላይ ያሉ አውሮፕላኖች በምን አየነት ከፍታ እንደሚበሩ እና ወዴት እንደሚሄዱ በደንብ ጠንቅቆ ያውቃል ለምሳሌ አንድ አውሮፕላን የሆነ ችግር ደርሶበት የሚመለስ ከሆነ ማንኛውንም አውሮፕላን ከዚያ አካባቢ በማግለል አደጋ ለደረሰበት አውሮፕላን ሙሉ እርዳታ ይሰጣል ይህ አይነቱ ሁኔታ በተለምዶ <ሜይ ዴይ > ተብሎ በአለም አቀፍ ደረጃ ይታወቃል።
ይህ ሁሉ ሆኖ ደግሞ የሁሉንም የስራ እንቅቃሴ በቅርብ የሚከታተለው የዘመቻ አካል ከበላይ ሆኖ ማንኛውንም አይነት እንቅስቃሴ ይቆጣጠራል።ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው አውሮፕላን ተነስቶ አየር ላይ የሚወጣው።
የአየር ድንበር እንደመሬት ድንበር ተለክቶ የተቀመጠ ሳይሆን በአየር መከላከያ እና በራዳር መለኪያ ተለክቶ ያለ ድንበር ነው በማንኛውም የድንበር ከተማ በግልፅ ወይንም በድብቅ የሚተከለው ይህ መሳሪያ ምንም አይነት ምዝገባ ሳያደርግ የመሬቱን ድንበር ዘሎ ወደ አየር ክልላችን የመጣውን ማንኛውንም አውሮፕላን ለራዳር ሰራተኛው ይናገራል ይህን ያህል ኪሎ ሜትር ወደ ኢትይጵያ አየር ክልል እየገባ ነው ይላል ይህን ያየው የራዳር ሰራተኛው በልምድ ምናልባት ገና አዲስ የተመረቀ የሱማሌ ፓይለት ከሆነ ትንሽ ይጠብቀዋል ካልሆነ ግን ወዲያው አጠገቡ በማንኛውም ሰአት ለሚመደበው የዘመቻ አዛዥ ያስረዳል የዘመቻ አዛዥ ለሚመለከተው ክፍል በስልጣን ተዋረድ ያመለክታል ይህ የሚሆነው ደግሞ በደቂቃ ወይንም ከደቂቃ ባነሰ ጊዜ ነው በዚህ አይነት ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በተሟላ ሁኔታ ሰልጥነው የሚጠብቁት የአየር ላየር ውጊያ ፓይለቶች ተነስተው አየር ላይ በመሆን ወደ አየር ክልላችን የገባውን አውሮፕላን <ኢንተርሴፕት >ያደርጉታል ይህን ለማድረግ በደህናው ቀን ልምምድ የሚደረግ ሲሆን የልምምዱ አይነት <ስክራምብል > ተብሎ ሲታወቅ ከማናኛውም ቦታ ከምግብ ቤት ወይንም ከካፊቴርያ ወይንም ከየትኛውም የአየር ሃይሉ ግቢ ተነስቶ ማንኛውንም መሰናዶ አድርጎ አውሮፕላኑን አየር ላይ ለማውጣት ከአምስት እስከ ስድስት ደቂቃ ብቻ ይወስዳል በዚህ አይነት ለምሳሌ ከሱማሌ ተነስቶ ወደ ድሬዳዋ የሚያመራ ማንኛውም አውሮፕላን ገና ጂጂጋ ሳይደርስ ጀግናው የኢትዮጵያ አየር ሃይል አየር ላይ ያስተናግደዋል።
አውሮፕላን የሚዋጋው እንደማንኛውም እግረኛ በሚደርሰው መረጃ መሰረት ሲሆን በማናኛውም ሰአት <ሪኮ > የሚባሉ ወይንም በሙሉ ስማቸው <ሪኮነሰንስ > የሚያደርጉ በምድር ጦር <አብሪ > እንደሚባለው በጠዋት ተነስተው የኢትዮጵያን ተራሮች እና ሜዳዎች እንደምን አደራችሁ የሚሉ ፓይለቶች ለዚሁ ሙያ በደንብ የተዘጋጀ አውሮፕላን ይዘው ያዩትን ይናገራሉ በዚህ አይነት ለዘመቻ የሚያፈልጉ መሰናዶዎች ተደርገው እርምጃ መውሰድ የተዋጊ ፓይለቶቹ ሀላፊነት ሲሆን አውሮፕላኑን አየር ላይ ለማውጣት ግን ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች በሙሉ ተግባራዊ ይሆናሉ ።ይህን የሚያደርጉት በቦንብ መጣል የሰለጠኑ ተዋጊ ፓይለቶች ሲሆኑ ብዙውን ጊዜ ስራቸው ለምድር ጦር ድጋፍ መስጠት ይሆናል ከነዚህ ጋራ አንድ ላይ የተዋጊ ሄሊኮፕተር ሚና ከቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች ጋራ አንድ ነው ።
በማንኛውም ጊዜ እንደማንኛውም ወታደር አንድ ፓይለት አደጋ ቢደርስበት እሱን ለማንሳት አስፈላጊ ከሆነ አየር ላይ ካልሆነ ደግሞ በጊቢ ውስጥ ሆነው የሚጠብቁ <ሬስኩዩ ቲም > የሚባሉ በዚህ ሙያ የተሟላ ልምድ ያላቸው ፓይለቶች ይኖራሉ ።
እኔ ብዙ ቦታ ኖሬያለሁ ይህን የምለው በብዙ የአለም ክፍል እንደኖረ ሰው ነው በዚህ ዙረቴ ብዙ ነገር ተምሬያለሁ ብዙ ሰው አውቄያለሁ አሁንም ድረስ ግን የማይገባኝ ጉዳይ በዚያ አለም እንደዚህ በቴክኖሎጂ ባልሰለጠነበት ዘመን የ ኢትዮጵያ አየር ሃይል እንደዛ አይነት የተራቀቀ ስራ መስራቱ ይገርመኛል የ ኢትዮጵያ አየር ሃይል የራሱ የሆነ የሴፍቲ ክፍል የራሱ የሆነ የቁጠባ ባንክ የራሱ የሆነ ከአለም የወታደራዊ ኮሌጆች ስታንደርድ እኩል የሆነ አካዳሚ እንዲሁም የራሱ የሆነ የማኔጅመንት ትምህርት ቤት እንደዚሁም ከወዳጅ አገር ድረስ እየመጡ የሚሰለጥኑበት የቴክኒክ ትምህርት ቤት ያለው በቤተሰብ ደረጃ ሙሉ ግልጋሎት የሚሰጥ ዳቦ ቤት የስጋ ቤት እንደዚሁም ከልብስ ጀምሮ ማንኛውንም ቁሳቁስ የሚያቀርብ የራሱ ትልቅ ማርኬት እና በጊዜው መለኪያ ከማንኛውም ሆስፒታል በደረጃው የላቀ ሀኪም ቤት የነበረው ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ሙሉ ጊዜያቸውን ሰውተው የገነቡት ትልቅ ተቋም ነበር ።
ቤቱ ሃላፊነት በሚሰማቸው እና በሙያቸው ጥሩ ልምድ ባካበቱ አዛዦች የሚመራ ነበር እኔ አንድ ወቅት እንደማንኛውም ወታደር የአየር ሃይል ተማሪ ነበርኩ እና ጀኔራል አምሃ ደስታ የአየር ሃይል ማኔጅመንት ያስተምሩናል …አንድ ቀን ሁል ጊዜ የሚከነክነኝን ጥያቄ ጠየቅሁ እንደዚህ ነበር ያልኩት … .በዛ ወቅት ጀግናውን የአየር ሃይል ፓይለት ጀነራል ለገሰ ተፈራን ጨምሮ በርካታ ወታደሮች እና ሲቢሎች በሱማሌ እስር ቤት ይማቅቁ ነበር …
ጌታየ ለምን አይፈቅዱልንም እኛ እዚህ ያለነው እንበቃ የለም እንዴ ? አልኩ የኔ የኮርስ ጓዶቼን በመተማመን ለምንድን ነው በሄሊኮፕተር ሄደን ተዋግተን ሰዎቻችንን የማናመጣው አልኩ …ደግሞ ለሱማሌ የሚል ፉከራ ነገር ሳልጨምር አልቀረሁም…አብረውኝ ያሉት በሙሉ የድጋፍ ጭብጨባ ሰጡኝ… ..ያን ጊዜ ልጅነትም አለ መሞት ሲባል ሌላ ሰፈር የመሄድ ያህል ቀላል ነበር… ..እና ዘራፍ አልን … .
ጀነራሉ ፈገግ ብለው …ልክ ነህ ሄዳችሁ እንደምታመጡ አምናለሁ ግና አየህ አካባቢው ሌሎች ኢትዮጵያውያን አሉ እነዚህን ስናመጣ እነዛ ላይ የሚወስዱት እርምጃ የከፋ ይሆናል ይህን ማየትም አለብን አሉና ለማንኛውም የዚህ ኮርስ አባላት ይህን ግዳጅ እንዳስመዘገቡ ማስታወሻ እይዛለሁ አሉን።
ይህ ለኔ በራሱ ትልቅ የማኔጅመንት ሃሳብ ነበር … .በሌላ ጊዜ ስለ አገር ፍቅር ሲያስረዱን …አገራችሁን መውደድ ያለባችሁ እናት ልጇን እንደምትወደው መሆን አለበት…እናት ልጇን ይዛ በመንገድ ስትሄድ የደነበረ በሬ ቢመጣ ካለምንም ጥርጥር ወደ ሁዋላ ታደርገዋለች የዚህ አይነት ፍቅር የኮንፊደንስ ፍቅር ይባላል አገራችሁንም በዚህ አይነት ነው መውደድ ያለባችሁ … .ይህን ሲሉ የነበርው ሁኔታ በቃላት ሊገለጽ ባይችልም ምናልባት 50 የምንሆን የአንድ ኮርስ አባላት በዝምታ እናያቸው ነበር ..እናት ኢትዮጵያ እንደዚህ አይነት ሰዎች ነበሯት … ..አየር ሃይል እንደዚህ አይነት መኮንኖች ነበሩት፡
እኔ በግሌ በፕሮፌሽን ደረጃ ፖለቲከኛ አይደለሁም ቀድሜ እንደገለፅኩት ወታደር ነኝ ሌላ ምንም ልሆን አልችልም እና ይህች ትንሽ መጣጥፌ ያልሆነችውን ፓለቲካ ፓለቲካ እንድትሸት አልፈልግም ሆኖም አንድ ወቅት የሰሜን አሜሪካን
የስፖርት ፌስቲቫል ተካፍዬ ስመለስ አንድ አረጋዊ ሰው ዋሽንግተን አውሮፕላን ማረፊያ አገኘሁና በአውሮፕላኑ መዘግየት ይህንንም ያንንም እያነሳን ስንጫወት የአየር ሃይል ባልደረባ መሆኔን ገለፅኩላቸው የአጋጣሚው ጉዳይ እሳቸውም በምድር ጦር ውስጥ በጊዜው ባለከፍተኛ ማእረግ እንደነበራቸው ነገሩኝ እና ይህን ጠየቁኝ… .
አየር ሃይል ውስጥ ማን ማንን ታውቃለህ አሉኝ…
እኔም ይህን መልሼላቸዋለሁ
1. ኦሮሞውን ሻለቃ ከበደ ጫኬ
2. ኤርትራዊውን መቶ አለቃ አማኑኤልን
3. የጅማውን ሻምበል ሰለሞን ክፍሌን
4. የትግራዩን ኮለኔል ሃብተዮሃንስን
5. የጎንደሩን ሻምበል በላይ (ጠቃሹን )
6. የጅጅጋውን መቶ አለቃ ወጋየሁ ይማምን
7. የሓረሩን መቶ አለቃ ጥላሁን ሀይሉን
8. የሸዋውን መቶ አለቃ መርድ ዳጨውን
9. የሾኔውን ሻለቃ በዛብህ ጴጥሮስን
10. የጉራጌውን በድሩ ተማምን።
የኔ አየር ሃይል እንደዚህ ነበር…… .የኢትዮጵያ አየር ሃይል።
     
    
ቢሌ
ውድ የዋርካ እድምተኞች ዪህንን እውነተኛ የኢትዮጵያ የታሪክ አካል ለናንተ ለማሳወቅ ነው :: ታሪኩ እንደዚህ ነው , ጊዜው በዚያ ቀውጢ ዘመን ጀግናው የኢትዮጵያ ሰራዊት ወያኔን አይቀጡ ቅጣት በሚቀጣበት ጉና ተራራ አካባቢ ነበር :: ውጊያው በጣም ተጥዋጡፎ የነበረው ጋሳይ እምተባል መነደር ውስጥ ወደ ደብረታቦር የሚወስደው መንገድ ላይ ነበር :: በወቅቱ የአየር ወለድ አንድ ብርጌድ በቻ ነበር የዎያነን 5 ክፍለጦር ገተሮ የያዘው :: የበርጌዱ መጠሪም 'ቆቅ " ዪባል ነበር :: ቆቅ አደገግኛ ሁነታላይ ስለነበር ጀግናው አየር ሀይል የማያቅዋርጥ የአየር ድጋፍ ዪሰጥ ነበር :: በወቅቱ የረገፈው የወያኔ መንጋ የጋሳይ ህዝብ ዪቁጠረው , አንድ የሚግ 21 ተዋጊ አውሮትላን አብራሪ ኮሎኔል ጌ .መ ጋሳይ መንደር ላይ አዉሮትላኑ ዪመታና በእሳት ዪያያዛል , ለብ አድርጉ ዪህ ጀግና በዙ ለምድ ያካበተ በሶማሌ ጦርነት ብዙ የጀግነነት ተግባር የፈፀመ ለዚሁም መሰከር ከዋርካው መንጌ ሳይሆን ከእኢትዮጵያ ህዝብ በቀድሞው መሪ ኮሎኔል መንግስቱ አማካኝነት የጦርሜዳ ጀብዱ መዳይ ተስሽላሚ ነው :: ባካበተው ለምድ አውሮፕላኑ እየነደደ ወደ 20 ኪሜ . ከጦር ቀጠናው ርቆ በረረ :: አብሮት የነበረው ሻለቃ ነፍሱን ዪማረው አምላካችን በስደት ላይ አርፏል , የሽፋን በረራ እየበረረ የእሳቱን እድገት በሬድዮ እየነገረው ሁነትውን እና አቅጣጫውን ለባህርዳር ጣቢያ እያሳወቅ ተከተለው ::
ኮሎኔል ጌ .መ , ወደ 20 ኪ .ሜ ከበረረ በህዋላ , የአውሮፕላኑ መቆጣጠሪያ ለገመና አልሰራም አለ ጌ .መ ያለው ሁለት አማራጭ በቻ ነበረ , አንዱ ከነአውሮፕላኑ መሬት መግባት ለላው ደግሞ ከአውሮፕላኑላይ በዣንጥላ መውረድ ነበር :: እንግዲህ ልታውቁት የሚገባ ነገር , አውሮፕላኑ እንደተመታ እና እሳት እንደተያያዘ በዙ የተገጠሙለት መሳሪያዎች ለጌ .መ . ነግረውታል :: የጀግንነቱ መጠን የሚለካው በዣንጥላ ወዲያው ወርዶ እጁን ለወያኔ ከሚሰጥ አብሮ መቃጠልን መርጦ በዙ እስከሚችለው ተጉዞ የዎያኔን ቀጠና ካለፈ በህዋላ በዣንጥላ ወደማያውቀው ጀግና የጎንደር ገበሬ መንደር ደረሰ :: አብሮት የነበረው ሌላው ጀግና እልህ እየተናነቀው ወደ ባህርዳ የአየር ጣብያ በቻውን ተመለሰ :: በአየርሀይል ታሪክ አንድ አውሮፕላን በቻውን ከጦር ዎሎ ሲመለስ ግቢው በሙሉ ጸጥ ዪላል ሁሉም በእልህ ዪዋጣል , በተለይ የአውሮፕላንዋ Crew Chief ማለትም ለበዙ አመታት ላብቻው የአውሮፕላንዋ ሀላፊ ቴክኒሺያን ወንድሙን እንዳጣ ለአውሮፕላንዋ ያለቅሳል , ሁሉም እሱን ያጽናናል የዘለለዉን ፓይለት ሁኔታ ይከታተላል ::
ጌ .መ . መሬት እንደደረሰ , የአንድ እግሩ አውራጣት በጣም ተጎድቶ ነበረ :: ለግነዛቤ ያህል , ከተዋጊ አውሮፕላን የሚዘለለው , ህይወትን ለማትረፍ ብቻ ሲሆን አውሮፕላኑ የሚወድቅበተን ቦታ መምረጥ በጣም አስፈላጊ ነው አንድ ራስን ለማዳን ሲባል በከተማ ላይ ህዝብ በበዛበት ቦታ ላይ አይጣልም :: ጌ .መ .ም ዪህን ሁሉ እያሰበ , እጁንም ላለመስጠት በዙ ደክሟል , ከአውሮፕላኑ የሚያስፈነጥረው ሀይል , የአንድ ሰው ከብደት ሲባዛ በ 21 ጊዜ ሲሆን ያም ሀይል ቀጫጭን ሰሮችን የወገብ አጥንቶችን ሊጎዳ ይችላል እናም ጌ .መ ሲዘል ያደረገው የበረራ ጫማ ተገንጥሎ ነበር :: ጀግናው ጌ .መ የጎንደር ገበሬዎች ,ጀግኖች እጅ ገባ , በአካባቢው በሩቅ የተኩስ ድምጽ ዪሰማ ነበር ::
የተኩሱ ድምጽ እየቀረበ መጣ , ገበሬዎቹ የጌ .መን የበረራ ልብስ አስወልቀው ሌላ የነሱን ልብስ ሰጥተውት የቆሰለውን በአገርበሀል እያከሙት ዋሉ :: የዎያኔ ጀሌ አካባቢውን ከመውረሩራቸው በፊት , አስተዋዮቹ ገበሬዎች የጌ .መን የበረራ ልብሰና ሽጉጥ ሜዳላይ የወደቀ ሙቀጫ ውስጥ ደበቁት ,ጌ .መን ነጠላ ፊቱን ሸፍነው የተከመረ የእህል ገለባ ውስጥ ደበቁት :; ዎያኔዎች አካባቢዎን ያምሳሉ ገበሬዎቹን ያንገላታሉ , ከሰማይ የዎረደውን ሰውየ ውለዱ ብለው አካባቢውን ያመሱታል :: ቆራጦቹ ገበሬዎች ግን ለምንም ነገር ሳይደነግጡ , የዎያኔ ጀሌ የያዘው መሳሪያ ሳያስበረግጋቸው በኢትዮጵያዊ ወኔ ሂዱና የጣላችሁበት ቦታ ፈለጉ እኛ ማንንም አላየንም ብለው ዪመልስዋቸዋል :: መሽትሽት ሲል ከገለባውስጥ አውጥተውት ህክምናቸውን ቀጠሉ :: ከዛን ቀን ጀምሮ ለ 21 ቀናት ከገበሬዎች ጋር ከረመ :: ጌ .መ በሀርዳር ከመምጣቱ በፊት , በግዳጅ ላይ ጋምቤላ ነበር : ከሚወዳት ባለበቱ ከተለያት ስንበትበት በሎ ነበር , ከጋምቤላ በቀጥታ ነበር በሀርዳር የመጣው :: የጌ .መን ከአውሮፕላን መዝለል ከውድ ባለበቱ ከወይህእሮ ቆ . በስተቀር ሁሉም ያውቃል , በህይወት ይኑር ይትረፍ ማነም አያውቅም ነበር :: ሁነታው እስኪታወቅ ድረስ , በተለይ የጌ .መ squadron አብራሪዎች በባለቤቱ በወይዘሮ ቆ . እንዳይታዩ ጥብቅ ትዛዝ ተሰጥቶ ነበር :
ጌ .መ ከቁስሉ ማገገም ጀመረ , ባካባቢው ማለትም እሱ የሚኖርበት የገበሬ መንደር ዉስጥ 8 ሰው ብቻ ነበር ማንነቱን የሚያውቀው ሌላው ያካባቢ ህእዝብ ጌ .መን የሚያውቀው ዘመዱን ሊጠይ ከሩቅ ሀገር የመጣ ቄስ መሆኑን ነበር የሚያውቁት :: አለባበሱ እንደቄስ ጥምጥም ጠምጥሞ የተበጫጨቀ ቁምጣ ሱሪ እንዲሁ ያለቀች እና ያደፈች ሳሪያን ቢጤ ኮት በላይዋላይ , እንዲሁ ያደፈች ነጠላ ለብሶ ነበር የከረመው :: 21 ቀን አብሮ ከውድ የኢትዮጵያ የጎንደር ገበሬዎች ጋር ሲከርም የዎያኔ ጀሌዎች አዛዦች ባካባቢው እና በደብረታቦር ከተማ ነበሩ : ብዙጊዜ ከዎያኔ አለቆች ጋራ አብሮ ጠላ ቤት እየጠጡ ብዙ ነገሮችን አብረው ያወሩ ነበር :: ስለ አየርሀይል ተዋጊነት በየዎያኔን ጦር ላይ እንዴት ጉዳት እንደሚያደርስባቸው ያጫውቱት ነበር :: ጌ .መ 21 ቀን ከሰነበተ በህዋላ , ቁስሉም በደን ሲድነለት ወደ በሀርዳር ለመሄድ ውጥን ተዘጋጀ :: ከ 8 ውስጠ አዋቂ ገበረዎች , አንድ በድሜ የገፉ ጠንካራ ገበሬ እና ዘመዳቸው የሆነች ወጣት በጣም ቀልጣፋ ማንበብ መጻፍ የምታውቅ አብረውት ወደ ባህርዳር ለመግዋዝ ዝግጅቱ ሁሉ ተተናቀቀ ::
ወደ ባህርዳር ለመግዋዝ ዋና መክንያት የሆነው ቄስ ጌ .መ የሳምባ በሺታ ስለአመማቸው ለህከመና ተብሎነው :: መታወቂያ ቢጤም ፎቶ የሌለው ተዘጋጀ ረጂሙ ጉዞ ተጀመረ , ያጀግና የጎንደር ገበሬ ውስጡን የሚያውቀው በጸሎት የማያውቀውም በጸሎት ጌ .መን እና እነኛን ሁለት ጀግኖች ሰፈርተኛው ሁሉ ሸኛቸው :: ጌ .መም ሆነ እነኛ ገበሬዎች በሀርዳር በማን ቁጥጥር ስር እንደሆነ ምንም መረጃ የላቸዎም , ጌ .መ በሺተኛ ስለሆነ በቅሎላይ ተኝቶ ነው መንገዱን ሁሉ የተግዋዘው አዛውንቱ ገበሬ እና ለጂቱ በእግራቸው ነበር የተግዋዙት , መንገዱም 24 ሰአታት ነበር የፈጀባቸው , በመንገዳቸው ላይ ብዙጊዜ የዎያኔ ጀሌዎች እያቆሙ ዪጠይቅዋቸው ነበር , ሽማግለው እና ለጂቱ ወንደማቺን በጠና ሳምባውን ታሞ በሀርዳር ለማሳከም ነው የምንሄደው እያሉ ብዙውን ኬላ አለፉ :: ወያኔዎች ከጥዪት ይልቅ , የሳምባን በሺታ ነበር የሚፈሩት ባዛንጊዜ , አንዳንዱ ኬላልይ , ፊተሻው ጠበቅ ይልና ከብዙ ጭቅጭቅ በህዋላ ነበር የሚለቀቁት በተለይ የመታወቂያው ነገር ፎቶ ስለሌለው ብዙስቃይ ነበር , ባብዛኛው ግን ገና የሳምባ ነገር ሲነሳ ፈታሾቹ ይሮጡ ነበር :: እንደማይደረስ የለም በሀርዳር ተገባ ያገኙትን ሰው ሁኔታውን ቢጠይቁ ያገኙት መልስ , የኢትዮጵያ ሰራዊትም ዎያኔም ከተማውንአይቆጣጠሩትም , የኢትዮጵያ ህዝብ ከሌላው የአለም ህዝብ የሚለየው በጨዋነቱ አምላኩን በመፍራቱ , በባህሉ , በተፈጥሮ በተሰጠው የአምላክ ጸጋ ያለመንግስት መተዳደር የሚችል ህዝብ መሆኑን በተደጋጋሚ አስመስክሯል :: በከተማው የኢትዮጵያ ፖሊስ ሰራዊት በቻ ነበረ በዛን ወቅት : ጌ .መና የችግር ጊዜ ዘመዶቹ , ወደፖሊስ ጣቢያ ለመሄድ ወሰኑ :: ፖሊስ ጣብያው አካባቢ እንደደረሱ , ቀልጣፋዋ ልጅ ብቻዋን ወደጣቢያው ጊቢ ገባች , ያገኘችው ኩሩ ኢትዮጵያዊ የፖሊስ ሻላቃ ነበር , ጠጋ ብላም ጥብቅ ሚስጥር ዪዤነው የመጣሁት ከዛበፊት ግን መንግስት አለዎይ ? ብላትጠይቀዋለች , ለመሆኑ አንቺ ማነሽና ነው የምትጠይቂኝ ዪላታል , አይ ለማወቅ በየነው ትለዋለች , ለመሆኑ መንድነው ሚስጥሩ ዪላታል , በሩቅ እያሳየች ያበቅሎላይ ያለው ዎንድሜ ሊያናግሮት ዪፈለጋል ስትለው , ታዲያ ለምን እሱ አይመጣም እያለ ብልሁ ሻላቃ ወደ ጌ .ም ዪሄዳል , ጌ .መ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንነቱን ለሻለቃው ዪነግረዋል , ሻለቃውም በጣም በመጠራጠር ና ቢሮ እንሂድ እና ራዲዮ አደርጋለሁ ዪለዋል , ጌ .መ እና ጀግኖቹ አብረው ወደጊቢው ይገባሉ :: ሻለቃው የሬድዮ መልክት አዲሳበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያስተላልፋል , ፖሊስ መምሪያውም አንዴ መስመር ላይ ጠብቀን አየርሀይል መምሪያ አነጋግረን መልሱን እንሰጥሀለን ይሉታል , ወዲያው ብዙም ሳይቆይ አስቸክዋይ ትዛዝ ለሻለቃው ተሰጠው :: ሻለቃው በዎታደራዊ ስነስራት ራዲዮኑን አስቀምጦ በተጠንቀቅ ቆሞ , "ጌታዬ ባስቸክዋይ መራዊ የሚባል ቦታ እንድወስዶት ከፖሊስ ዋና አዛዥ ትዛዝ ተሰጥቶኛል የጦሩም ጠቅላይ ማዘዣ ጣቢያም ያለው መራዊ ነው ለጀነራል ክንፈገብርኤል እንዳስረክቦት ታዝዣለሁ ብሎ ወደጂፕ መኪናው ያመራሉ :: በቅሎዋም በአደራ ፖሊስ ጣቢያ ተቀመጠች ::

ዜናው ጌ .መ የመገኘቱ ከቀኑ 9ሰአት በኢትዮጵያ አቆጣጠር በድፈን አየርሀይል አስተጋባ : በ 6ኛው የትራንስፖርት ሬጅመንት አዲሳበባ ልደታ ያሉት የሄሊኮፕተር አብራሪዎች ሽሚያ ገቡ ወደ መራዊ በርሮ ጌ .መን ለማምጣት : ወዲያው አንድ ሚ 8 የትራንስፖርት ሄሊኮፕተር ባስቸክዋይ ወደ መራዊ ተላከ : ወይዘሮ ቆ . አሁንም ሁኔታው ሚስጥር ነው ለስዋ :: ያኩሩ ሻለቃ ጂፑን እያክለፈለፈ ወደ መራዊ ጌ .መን እና እነኛን ጀግኖች ይዞ ተፈተለከ : መራዊ ደርሶ ለጀነራል ክንፈገብርኤል በወታደራዊ ስነስርአት ጀግኖቹን አስረከበ : ጀነራሉም ሲያዩአቸው እንባቀረሽ ሲቃ እየተናነቃቸው የለበሱትን አዲስ ካኔተራ አውለቀው ለኮሎል ጌ .መ አለበሱት : ወዲያው ያን ገበሬዎቹ ያለበሱት ልብስ ዎልቆ አዲስ የጦር ሰራዊት ለብስ ለበስ :: በነገራችን ላይ , ሁለቱ ገበሬዎች እግራቸው ተላልጦና ቆስሎ መራመድ አቅቷቸው ነበር : ሄሊኮፕተርዋም መራዊ ኮማንድፖስት አረፈች ::

የጌ .መ መኖርያ ቤቱ ያለው ደብረዘይት ነው , በዛን ወቅት ብዙ ቁጥር የሚሆነው ተዋጊ በራሪ መኖርያው ደብረዘይት ሆኖ በተለያየ የህገሪቱ ክፍል እየተዘዋወረ ሀገሩን ያገለግል ነበር : እንዳጋጣሚ ብዙ በራሪዎች ደብረዘይት ነበሩ : ሁሉም በደስታና በሲቃ ተወጥሮ ድብረዘይት መኮንኖች ክበብ ውስጥ የዋርካው መንጌ የሚወደውን አይነት መጠጥ ሁሉም መኮንኖች የሄሊኮፕተርዋን መምጣት እየተጠባበቁ ተያይዘውታል : ሰአቱ በግምት 1ሰአት ተኩል ይሆናል ጨልምዋል ወጣቱ የሄሊኮፕተርዋ ፓይለት ደስታውን ለማብሰር በክበቡ ጣራ ላይ ዝቅ ብሎ በረረ : በአየርሀይል ታሪክና በሀል ድል ሲመታ , አይሮፕላን ከጥገና ወጥታ ምርመራዋን ስታልፍ የመረመራት ፓይለት , ጦር ሜዳ በለስ የቀናው ዝቅ ብሎ እና በሀይለኛ ፍጥነት በቤዝ ላይ ማለፍ ዋና ባህላችው ነው : ብዛት ያለው የአየርሀይል መኮንን ከነመለኪያው የክበቡ ግቢ ውስጥ ደስታውን ይገልጻል የጌ .መን ከቤዝ መምጣት በጉጉት ይጠባበቃል :: ጌ .መ ከነ የችግር ጊዜ ወዳጆቹ ገበሬዎቹ ጋራ በታርጋ ቁጥር አኃ 1250 ቶዮታ ክሩዘር ወደቤቱ ሳይሆን ወደ የጦር ሜዳ ግዋዶቹ ጋ መኮንኖች ክበብ አዲስ "ቀሰ " የሚባለውን የጦርሰራዊት ሙሉ ልብስ እንደለበሰ ከመኪናው ዱብ አለ : ግማሹ ያለቅሳል በደስታ ሲቃ , ግማሹ በሁለቱ ገበሬዎች ማንነት ለማወቅ ዪጣደፋል , ግማሹ ዊስኪ ጌ .መን ለመጋት ዪታገላል ደስታው ጦፍዋል : ጌ .መ አይኖቹላይ ከወንድልጅ የሚወጣ መጠነኛ እንባ ዪታያል ::

በዛ ሁሉ የደስታ ትርምስ መሀል እንዴት ወደቤቱ እንደሚወስዱት የቅርብ ግዋደኞቹ መመካከር ጀመሩ ከላይ እንደጠቀስኩት ባለቤቱ መንም የምታውቀው ነገር ስለሌለ ያሁሉ ሰራዊት ሆ ብሎ በምሽት ሲሄድ ሊፈጥርባት የሚችለውን የመደናገጥ ሁኔታ ለመቀነስ ሁለት የቅርብ ግዋደኞቹ ቀድመው ተላኩ : የተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ ሊጠይቅዋት እንደመጡ ብቻ አሳውቀው , ጌ .መ መቼ እንደሚመጣ እንዲጠይቅዋት እና የስልክ ግንኙነት እንዳላቸው እና ሌላም ሌላም ወሬ በተለይ ዛሬ ጠዋት በሬድዮ አየር ላይ እንዳገኙት እና ያው የወታደር ነገር ትዛዞች በየደቂቃው ስለሚለዋወጡ በቅርብም ሊመጣ እንደሚችል የመሳሰለውን እንዲያጫውትዋት ነበር : እነሱ በተላኩ በግምት 20 ደቂቃ ዪሆናል ያበደስታ የተዋጠ ሰራዊት እንደሰርግ በየመኪናው ታጭቆ በ Convoy መልክ ወደ ጌ .መ መኖርያ ቤት ጉዞ ተጀመረ :እግቢው መግቢያ ላይ ሁሉም ተራግፎ ሆ እየተባለ በሽጉጥ ተኩስ ግቢው ቀለጠ : ሁለቱ የተላኩት ወይዘሮ ቆ . ከግራና ከቀኝ ይዘዋት በረንዳው ላይ ብቅ አሉ : ወይዘሮ ቆ . በጣም ግራ በተጋባ ሁኔታ ምን እንደተፈጠረ አልገባትም ሁሉም ይጨፍራል ግማሹ እንክዋን ደስያለሽ ይላል በዚያ በግፍያመሀል ባልዋን በማታውቀው ዩኒፎርም ስታየው የእንባ ከረጢቶችዋ ፈነዱ መጀመርያ እንደመሸሽ ብላ ከዛተጠመጠመችበት አሁንም አልገባትም ታለቅሳለች አብረውት የነበሩትን ሽማግሌ እና ያቺ ጀግና ወጣት ሴት ስታይ ድንጋጤው ጨመረባት ለቅሶዋም በሀይለኛ ሲቃ እየባሰበት ሄደ : እንደምንም ወደቤት ተገባ ሽማግሌው እና ወጣትዋ ሴት ትልቁ ሶፋ ላይ ተቀመጡ ሌላው ባገኘው ነገር ላይ ተቀመጠ ብዛት ያለው ተጠጋግቶ በረንዳውላ ይ ሳይቀር ቆሞ ለጊዜው የረሳሁት አለቃ ጸጥታ ጠይቆ ወይዘሮ ቆ . ደግፎ ታሪኩን ያስረዳት ጀመረ : ግማሹ ያለቅሳል ግማሹ በጸጥታ ያዳምጣል : ንግግሩ እንዳለቀ ደስታና ፈገግታ የሞላበት ለቅሶ ቅልቅል ወይዘሮ ቆ . ይታይባት ጀመር ::

ወይዘሮ ቆ . እየተረጋጋች መጣች ሁሉም ጌ .መን በጥያቄ ያጣድፈው ገባ ጌ .መም በደስታ ተሞልቶ የደረሰበትን በተመስጦ ያብራራል በተለይ ሲለገበሬዎቹ አውርቶ አይጠግብም አንዳንዴ በመሀል ገበሬዎቹን የዛን ቀን , እዛቦታ , ከጋሼ እከሌ ጋር እያለ የነሱን ምስክርነት እያጣቀሰ ማብራራቱን ቀጠለ :: አንዱ ከመሀል ጌ .መን እባክህ ገበሬዎቹ የሰጡህን ልብስ ልበስ እና እንይህ አለው : ጌ .መም ዎዲያው ቀይሮ መጣ ግማሹ ሲያዝን ግማሹ ይስቅ ጀመር : በህዋላ ሀሳቡን ማን እንዳመጣ አይታወቅም , ታሪኩ ከነ ልብሱ በቪዲዮ መቀረጽ አለበት ታሪካችን ነው ተብሎ የዛኑ ቀን ዪሁን በማግስቱ ሙሉ ታሪኩ ተቀረታጸ :: የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ሀገሬ ለረፍት ሄጄ ደብረዘይት በፊት የማውቃቸውን የስራባልደረቦቼን አየርሀይል Ducumentation/ archive center ውስጥ እንዳለ ብጠይቃቸው ሁሉም equipment and video tapes ወያኔ ሲገባ እንደተዘረፈ አጫወቱኝ :: ሌላ ኮፒ ጌ .መ ጋር እንዳለ አውቃለሁ :: በማግስቱ ለጌ .መ እና ለነኛ ወድ ጀግና ገበረዎች ሙሉ የጤና መርመራ በአየርሀይል ዶክተሮች ተደረገላቸው :: ካዛን ቀን ጀምሮ እጂግ በጣም ጥሩ የሆነ እንክብካቤ ለሁለቱ ገበሬውች በኮሚቴ አማካኝነ ይደረግላቸው ነበር : ገበሬዎቹ ወርያህል እንደቆዩ , እንግዲህ ወዳገራችን መሄድ እነፈለጋለን በለው ጌ .መን ማማከር ጀመሩ :: ጌ .መም , ሁኔታውን ለኮሚቴው አሳወቀ ::
ኮሚቴው ጉዳዩን በጥብቅ ከመረመረ በህዋላ , ለነኚህ ጀግኖች በተቻለ አቅም ውለታቸውን እንዴት ለመክፈል እንደሚቻል ጥናት ተደረገ :: ኮሚቴው በጥናቱ መሰረት እንዴት ወደ ቀየአችው መመለስ እንደሚችሉ በዙ ከተዎያየና ሰዎቹንም ካነጋገረ በህዋላ ውሳኔ ላይ ተደረሰ : ሰዎቹን ማንም ሳያውቅ ሳአቱና ቀኑ ሳይታወቅ በአየርሀይል አውሮፕላን በሀርዳር ድረስ ማድረስ ታቀደ : ባዛን ጊዜ ደብረታቦር እና አካባቢው በዎያኔ ቁጥጥር ስለነበረ እስከ ቀያቸው ማድረስ እንደማይቻል ኮሚቴውም ገበሬዎቹም ተስማምተውበታል :: ሌላው የኮሚቴው ውሳኔ ለአየርሀይል አዛዥና ለማናጅመንት አባላት ለገበሬዎቹ የገንዘብ ሽልማት ለመስጠት ዎሳኔውን አቀረበ : የቀለረበውም ፕሮፖሳል ጸደቀ :: ውሳኔውም እንደሚከተለው ነበር : ለሁለቱ ከጌ .መ ጋር ለመጡት ለያንዳንዳቸው ስምንት ሺህ የኢትዮጵያ ብር ሲሆን እዛ እገበሬ መንደር ለቀሩት ለያንዳንዳቸው ደግሞ ሁለት ሺህ የኢትዮጵያ ብር እንዲሰጣቸው ተወሰነ ::

በውነቱ ላደረጉት ኢትዮጵያዊ ጀግንነት የተሰጣቸው ሽልማት ሲያንሳቸው ነው : ሁላቺንም በዛን ወቅት ሀገሪቱ በብዙ ቀውስ ተወጥራ እንደነበር የምናውቀው ነው : የተደረገላቸው ሽልማት ከልብ እና ከውነተኛ ስሜት እንደተሰጠ አውቃለሁ :: በጣም የሚገርመው , ሁለቱ ገበሬዎች በጪራሽ ገንዘብ አንቀበለም እኛም ለሀገራችን ድርሻችንን ነው ያበረከትነው ብለው አሻፈረኝ አሉ : በስንት መከራ ተለምነው ይህ ገንዘብ ለውለታ ሳይሆን እርሻችሁን እንድታሻሽሉበት , መታከሚያም እንዲሆናችሁ ተብሎ ነው እንጂ ኩሩ ኢትዮጵያዊ እንደሆናችሁ ስራችሁ ምስክራችን ነው ተብለው በግድ እሺ አሉ : ገበሬውቹ ከተስማሙ በህዋላ ገንዘቡ አንተ ወንደማችን ዘንድ ይቀመጥልን ለእጃችን መቶ ብር ይበቃናል በለው አሉት ጌ .መን : ጌ .መም , እንደሱ ሳይሆን አብሬአችሁ ባህርዳር እሄዳለሁ እዛ ሰንደርስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስላለ በስማችሁ ዪቀመጥና የሚበቃችሁን በእጃችሁ ከባንክ ደብትራችሁ ጋር ይዛችሁ ወደአገራችሁ ትሄዳላችሁ ብሎ አስረድቶ በዚህ ተስማሙ :: ባዛን ጊዜ ባህርዳር በመንግስት ቁጥጥር ስር ነበር ጌ .መም ከጀግኖቹ ጋራ አብሮ ወደ ባህርዳር በአየርሀይል ልዩ አውሮፕላን ተግዋዘ :: ከላይ የገለጽኩትን ሁሉ ጌ .መ የባንክ ደብተር ከፍቶ ተላቅሰው ተለያዩ : ተፈጸመ !
1. ይህንን ባጭሩ ያቀረብኩት ታሪክ ምንያህል የጎንደር ገበሬ በወቅቱ ስለወያኔ ግንዛቤ እንደነበረው ላማሳወቅ ነው ::
2. ያጀግና ፓይለት እንደገና ተመልሶ ሀገሩ እስከመጨረሻ ሲያገለግል ነበር ::
3. በነገራችን ላይ , ያን ሁሉ ዘመን አየርሀይል ወያኔን ሲደበድብ , ሀገር ላለማስገንጠል ሲታገል ብዙ ደክሟል : ወያኔ ግን አንድም የአየርሀይል ፓይለት አልማረከም ::
4. አንድ ወጣት በራሪ መቀሌ ላይ ተመትቶ በዣንጥላ ወርዶ እጁን ላለመስጠት በሺጉጥ ተታኩሶ ህይወቱ አልፏል : ጥላሁን )
5. አንድ የትራንስፖርት ሄሊኮፕተር ቦታ ጠፍቶት ትግራይ ወስጥ አርፎ ድንገት በወያኔ ቁጥጥር ስር ይወድቃል : ለስድስት ወር በወያኔ ቁጥጥር ስር ከርሞ ጠባቂዎቹን አንድ ወንድ አንድ ሴት አሳምኖ ላማምለጥ ችሏል : ወያኔዎቹም አየርሀይል ስራ ሰጥቷቸው ተጋብተው ይኖሩ ነበር , አሁን የት እንዳሉ አላውቅም ::
6. ወያኔ ሀገሪትዋን ሲቆጣጠር 95% ተዋጊውን አብራሪ አላገኘም :: 5% የሚሆኑት ጀግኖች አሁንም በእስር ዪማቅቃሉ : አንድ ጀግና ተዋጊ በራሪ በህክምና ማጣት እሰርቤት አርፏል ::
7. ጌ .መ ከነቤተሰቡ እዚህ አሜሪካ በሰላም ይኖራል ::
8. መልካሙን ሁሉ ለኢትዮጵያ እና ለህዝቦችዋ እመኛለሁ ::
አክባሪያችሁ
    
ታሪኮቹን የሚልክልኝ ወዳጄ , በመጽሀፍ መልክ ለማዘጋጀት እንደሚጥር ነግሮግኛል : ይህ አንጋፋ አየር ሀይል በ ጡት ነካሽ ልጆች እዚህ አሳፋሪ ደረጃ በመድረሱ እውነተኛ የእትዮጵያ ልጆች የሆኑ ሁሉ አንጀታቸው እንዳረረ ይገኛል :: ሌላው የሚያጽናናን ነገር ቢኖር , በአስተዳደር , በቴክኒክ , በበረራ ሙያ እጂግ ብዙ ልምድ ያላቸው የቀድሞው አየርሀይል አባላት በጥሩ የኑሮ ሁኔታ እና በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ :: ጠንካራም የመረዳጃ መሀበርም አላቸው : ህልማቸው ሀገር ተመልሶ የፈረሰውን መገንባት እና ቢያንስ ድሮ የነበረበት ቦታ አየርሀኡሉን መመለስ ነው :: አንዳንዶቹ እንዳውም የሌላ ሀገር አየርሀይል Operations Commander ደረጃ ላይ ያሉ አሉ : በግልም ተቀጥረው የሚበሩ አሉ : አንድ ቀን ይህ ሁሉ ሀይል እንደሚመለስ አልጠራጠርም ::
ስለ ገበሬዎቹ ሁኔታ ለማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው : ጊዘው ከ 17 አመት በላይ ይሆነዋል : አንድ ነገር ግን በርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ጌ .መ . ሁልጊዜ የሚመኘው ቦታው ድረስ መሄድ እንደሚፈልግ ነው ::