ደራሲ - ቢሌ

            ከዚህ በታች ያለው ታሪክ የወዳጄ እውነተኛ ታሪክ ሲሆን በወያኔ መንግስት ተብየው የደረሰበትን አሰቃቂ በደል ለሀገር ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ለማሳወቅ እና የወያኔን ማንነት አንባቢያን እንዲረዱ እነሆ ታሪኩን ለናንተ ፍርድ አቅርቤዋለሁ :: መልካም ንባብ ::


 ሞቶ መነሳት

            ግንቦት -98 ድንገት ከፍተኛ ግርግር ተሰማ። ትልቂቱ ኢትዮጵያ ትንሺቱ ኤርትራ ወረረችኝ በማለት ወያኔዎች ያላዝናሉ።የሚገቡበት ቀዳዳ ጠፍቱአቸዋል።ምክንያቱን አልወቀው እንጂ ወያኔዎች ከፍተኛ ውጥረት ላይ ናቸው።ያገኙትንም ሁሉ እያፈሱ ወደ ትግራይ ማጉዋጉዋዝ ጀምረዋል :: ‘ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግምባር’ የሚለውን የደርግ መፈክር እያስታወሰኝ ነው :: አየር ሃይልም ከክተት አዋጁ ጀምሮ በአስቸኩይ ለውጊያ ዝግጁ እንዲሆን ትእዛዝ የደረሰው በመሆኑ እኔም ከስልጠና ስኳድሮን ወደ ተዋጊ ሚግ -23 ቦምብ ጣይ ስኳድሮን ተዛውሪያለሁ :: ሁሉም በራሪ መኖሪያ ቤቱን ለቆ ደብረ ዘይት በሚገኘው የአየር ሃይል መኮንኖች ክበብ እንዲኖር በወጣው ትእዛዝ መሰረት ጠቅልሎ ገብቱአል።እኔም ከአዲስ አበባ መኖርያ ቤቴን ለቅቄ ደብረ ዘይት ከትሚያለሁ :: ጠዋት የስልጠና ስኳድሮን፣ከሰአት በኋላ ደግሞ ከተዋጊ ስኳድሮን ጋር መደበኛ ተግባሬን በማከናወን ላይ ነኝ :: በአበሻ ግንቦት 27 ቀን 1990፣በፈረንጆቹ ደግሞ ጁን 5 1998 ነው :: በጠዋቱ የስልጠና በረራዎችን አከናውኜ ከሰዓት በኋላ ደግሞ የውጊያ ስኳድሮን ሚግ -23 አውሮፕላንን የውስጥ አካል የፋሚላራይዜሽን (ትውውቅ ) የክፍል ውስጥ ትምህርት እየወሰደኩኝ ነው :: በአበሻ ከቀኑ 11 ሰዓት ይሆናል፣በፈረንጆቹ ከሰዓት በኋላ 5 ሰዓት :: ሻለቃ በሪሁ የተባለ በአየር ሃይል የመከላከያ ሴኩሪቲ ሰራተኛ፣ለብርቱ ጉዳይ እንደሚፈልገኝ ይነግረኛል ::ትምህርት ላይ ነኝና እንደጨረስኩ እንደምንነጋገር ተስማምተን ውጪ ይጠብቀኛል :: ሻለቃ በሪሁ ኪዳነ ማለት ከአየር ሃይሉ ዋና አዛዥ ጀነራል አበበ ተ /ሃይማኖት (የበረሃ ስሙ ‘ጆቤ’ ) ጋር በቅርብ ከሚሰሩ የትግራይ ተወላጆች መካከል አንደኛው ነው :: ከመከላከያ ዋናው መሥሪያ ቤት ጋር የተያያዘ የደህንነት ሥራ ሲሰራ የኖረ ሲሆን፣ አየር ሃይልም ከመጣ በኋላ ያንኑ የጆሮ ጠቢነት ሥራን የሚያከናውን ነው :: እግረመንገዱን ግን በአየር ሃይል የበረራ ት /ቤት የበረራ ሙያ ሥልጠና እንዲያደርግ ተፈቅዶለት፣በመጀመርያ ደረጃ የበረራ ስኳድሮን ውስጥ ተመድቦ በችሎታ ማነስ ከበረራ ሙያ የተባረረ ሲሆን፣ለወያኔዎች በሚሰጥ ልዩ ችሮታ ብቻ በሄሊኮፕተር ስኳድሮን አዛዥ ሆኖ ተመድቦ እየሰራ ያለ ነው :: እኔና አንድ የሥራ ባልደረባዬ የክፍል ውስጥ ትምህርታችንን ጨርሰን ስንወጣ በሪሁን ባለማግኘታችን አንዲት ለስኳድሮናችን የተመደበች መኪና እያሽከረከርኩኝ በቀድሞው ስያሜው የጀግኖች አምባ፣በወያኔዎች ዘመን ግን የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ተብሎ ከሚጠራው ቅጥር ግቢ ለቀን ስንወጣ፣በሪሁ ከኋላ በከፍተኛ ፍጥነት እያሽከረከረ ይደርስብኝና በምልክት ካስቆመኝ በኋላ፣ወደ እኔ በመቅረብ ለከፍተኛ የሥራ ጉዳይ እንደፈሚልገኝና እርሱ በያዛት መኪና አብረን እንድንሄድ በጠየቀኝ መሰረት የያዝኳትን መኪና ከጎኔ ለነበረው የሥራ ባልደረባዬ ሰጥቼ በበሪሁ መኪና ወደ ዋናው የአየር ሃይል ግቢ አመራን :: በመንገዳችን ላይ ግን ሱዳን ኤርትራን ደግፋ ልትወረን ጦሯን ወደ ድንበር እያስጠጋች ነውና፣የኢትዮጵያንና ሱዳንን ወሰን የሚያካልል ለበረራ የምንጠቀምበትን ማፕ (ካርታ ) ከእኔ ቢሮ ፈልጌ እንዳገኝለት ይጠይቀኛል :: የነገረኝ ታሪክ እውነትነት ሊኖረው እንደሚችል ባልጠራጠርም ከእኔ ቢሮ ማፕ መፈለጉ ግን አልመስልህ አለኝ :: ይህንን ለሚያክል የአገር ጉዳይ በዚህ ላይ በሪሁን ለሚያክል ምርጥ የወያኔ ካድሬ፣ የአየር ሃይሉ የኤሪያል ፎቶ ሴክሽን (ክፍል ) በሰፊው ክፍት ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ አልነበረኝም።ማፑም ከእኔ ቢሮ ይልቅ እዝያው ፎቶ ሴክሽን እንደሚሻል ግልፅ ነው :: ይህንን በአእምሮዬ እያመላለስኩ ወደ ቢሮዬ ደረስን ::እኔ ካርታውን ስፈልግለት በሪሁ ግን ሥልክ በመደወል ተጠመደ ::እዚያ ይደውላል፣እዚህ ይደውላል ::ሻለቃ አብርሃ መንጁስን ለማግኘት ይጥራል ሻለቃ አብረሃ መንጁስ ደግሞ የአየር ሃይሉ የደህንነት ክፍል ሃላፊ ሆኖ የሚሰራ ወያኔ ነው።እርግጠኛ ነኝ የትምህርት ደረጃው ኤለመንተሪን ያጋመሰ እንኳ አይደለም ::ግን ሃይለኛ ነው።ነገር ማነፍነፍ ይችልበታል፣ ከማይመቹኝ መንጋ የወያኔ ካድሬዎች ውስጥ ቁጥር አንዱ ነው :: በሪሁ በዚህ ከሥራ ሰዓት ውጪ ቢሮዬ ድረስ ይዞኝ መጥቶ አብረሃን ለማግኘት በሥልክ መጠመዱ ግራ አጋባኝ ::እንደነገረኝ ከሆነ የፈለገኝ ለብርቱና አስቸኳይ ጉዳይ ነው፣ ታድያ ወደ ሌላ ማተኮሩ ምን የሚሉት ነው ? ለነገሩ ወያኔዎች የአገር ይሁን የግል ጉዳይ መች ያስጨንቃቸዋል ?እኔ ግን አንዴ ካርታ ፈልግልኝ ብሎኛልና ፈልጌ አምጥቼ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጥኩለት ::በሪሁ ዞር ብሎም አላየው ::ይመስለኛል አበረሃን በሥልክ አግኝቶት ተነጋግረዋል ::ንግግራቸው በትግሪኛ በመሆኑ ሙሉ ለሙሉ አይገባኝም።እንድፈልግለት ጠይቆኝ ያገኘሁለትን ካርታ ዞር ብሎም ሳያየው እዚያው ጠረጴዛ ላይ እንደተወው እንውጣ ብሎኝ ከቢሮዬ ወጣ ስንል አብረሃ መንጁስን እዚያው እቢሮዬ ደጃፍ ላይ ግጥምጥም አልን :: ዙርያውን ብቃኝ ማንንም ሰው ማየት አልቻልኩም፣ መኪናም በአካባቢው ዝር አላለም፡ታድያ በምን እዚህ ድረስ መጣ ብዬ ተገረምኩ። ምክንያቱም የእኔ ቢሮ የሚገኝበት የበረራ ት /ቤት ከዋናው ጠቅላይ መምሪያ የ 3 እና 4 ኪ /ሜ እርቀት ላይ ነው። ወዲያው ግን በበሪሁ መኪና ሆነን ጉዞ ጀመርን። በሪሁ ያሽከረክራል፣እኔ ከጎኑ ተቀምጫለሁ፣አብረሃ ከኋላ ተሳፍሯል። በቀጥታ ሻለቃ አመዴ ወደሚባለው ሌላው ትግሬ ባለሥልጣን ቢሮ አመራን። አመዴ ማለት የበረሃ ሥሙ ነው።ትክክለኛ ሥሙ ግን ሲሳይ በላይ በመባል ይታወቃል።በእድሜው ገፋ ያለ፣በትምህርቱ ግን ከ 5ኛ ክፍል ያልዘለለ፣የራሱ ሃሳብ ካልሆነ በስተቀር የሌላን ሰው ሃሳብ በፍፁም በበጎ የማያይ፣ጅላ ጅል መሥሎ ግን አስቸጋሪ ሰው ነው። አቅሙን አያውቅም። ቢተው በላይ የሚባለው የወያኔ ቁንጮ (የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦችን መንግስት ከአባተ ኪሾ ጀርባ ሆኖ ሲያስተዳድርና ሲገዛ የኖረ፣በኋላ ግን ከመለስ ጋር ተጋጭቶ በእሥር ሲማቅቅ የነበረው ) ታድያ አመዴ የዚህ ቱባ ባለሥልጣን ወንድም ነው።በዚህም ምክንያት ይመስላል አመዴ አየር ሃይል ውስጥ እንዳሻው ይፈልጣል ይቆርጣል ። ትልቁን የአየር ሀይል ኦፐሬሽን መምሪያንም ያዛል። በተጨማሪም እንደ በሪሁ ሁሉ የበረራ ሥልጠና እንዲወስድ ተፈቅዶለት በረራን ሞክሯል።ይሁን እንጂ እጅግ ደካማ በመሆኑና እድሜውም ተጨምሮ በአየር ሃይሉ ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ የችሎታ ማነስ ሥልጠናውን እንዲያቆም ቢደረግም ከፍተኛ ረብሻ ፈጥሮ ከበረራ ይስቆሙትን የበረራ አስተማሪዎችን ቁም ስቅል ሲያሳይ የነበረ ነው። ታድያ በሪሁና አብረሃ እኔን ይዘው እዚሁ የኦፐሬሽን መምሪያ ሃላፊ ነኝ ከሚለው አመዴ ቢሮ ጎራ ለማለት እኔን መኪናዋ ውስጥ እንድጠብቃቸው ነግረውኝ ወደ ውስጥ የዘለቁት። ጊዜው እየመሸ ነው።ጠዋት ነው በማለዳ ከቤቴ የወጣሁ ነኝ … .. ደካክሞኛል።ቶሎ በጊዚያዊነት ወደ ተሰጠችኝ የአየር ሃይል መኮንኖች ክበብ መኝታ ቤቴ ቢያደርሱኝ ጓጉቺያለሁ።  በሪሁና አብርሃ አመዴ ቢሮ ቆይተው ከዚያም ወደ አየር ሃይሉ ዋና አዛዥ ጀ /ል አበበ ተ /ሃይማኖት ቢሮ ገቡ።እኔም የአካል ዝለቱ ሥለ በረታብኝ እዚያው መኪናዋ ውስጥ ወንበር ላይ እራሴን ጋለል አድርጌ እንደማንቅላፋት እያደረገኝ ነው ። ረዥሙና አድካሚው የጦርነት ወሬ የሚናፈስበት ቀን አድክሞኛል። የአየር ሃይሉ ዋና አዛዥ አበበ ተ /ሃይማኖት በበረሃ ሥሙ ‘ጆቤ’ በመባል በሰፊው ይታወቃል። እብሪተኛ ነው።ደርግን በማሸነፋቸው ከፍተኛ እብጠት ካበጡት የወያኔ የጦር መሪዎች አንደኛው ነው። እሱ ያለው ነገር ሁሉ ተፈፃሚነት ያገኛል እየተባለ ይወራለታል። በዙሪያው ያሉ ረዳቶቹ ሲሶ የመንግሥት ሥልጣን አለው ብለው ያምናሉ ። የቀድሞ የአየር ሃይል ከፍተኛ መኮንንችን፣ በራሪዎችን፣ባለሌላ ማዕረግተኞችን፣ሴት ወንዱን ሁሉ ቁጭ ብድግ ያሥደርጋል።እሱ የሚናገረው ቃል የእግዚአብሄር ቃል አይነት እንደሆነች መወሰድ ከተጀመረ ውሎ አድሯል። እዚያችው መኪና ውስጥ ደገፍ እንዳልኩ የመኪናው በር ሲከፈት አይኔን ገለጥ አድርጌ ስመለከት በሪሁና አብረሃ ተያይዘው መተዋል፣ቀኑም መጨላለም ጀምሯል።ወደ መኝታ ቤትህ እናድርስህ ብለውኝ መኪናዋን በሪሁ ሲያንቀሳቅስ የእፎይታ ረዥም ትንፋሽ ተነፈስኩ። ገና መንገድ እንደጀመርን አብረሃ ከኋላ ተቀምጦ ሲጋራ አቀጣጠለ።ከወያኔዎቹ ብሽቅ ባህርይ ውሥጥ ለሰው ሥሜት ደንታ ማጣታቸው ነበር።መኪና ውስጥ፣ምግብ ቤት ውስጥ የትም ቦታ …… .. ያጨሳሉ።ለእነርሱ ሁሉም ሥፍራ ምንም የማድረግ ፈቃድ አለን ብለው ጭንቅላታቸውን አሳምነውታል። መኪናው ውሥጥ መጨሱ አልተመቸኝም።ከድካም ጋራ ተዳምሮ የሲጋራው ጢስ አቅለሸለሸኝ። ድንገት እንኳ ሰምቶኝ ሲጋራውን መኪና ውስጥ ማጨሱን እንዲያቋርጥ እንዳልነግረው በረዥም የሬድዮ ግንኙነት ተጠምዷል።አብረሃ እርጋታ አይታይበትም፡ለነገሩ በተፈጥሮው ቀዥቃዣ ነው።ሰውነቱ እላዩ ላይ ያለቀ ጣዕረ ሞት።አይኖቹ ጉድጓዳቸው ውሥጥ እንኳ ሆነው ተጠራጣሪና ያለማቁዋረጥ ወዲያ ወዲህ ያማትራሉ።ምላሱ መቼም አይጣል ነው።በዚህ እየሞተ ባለ ሰውነቱ ላይ ሲጋራ ! አንዴ በሬድዮ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከበሪሁ ጋር ያወራሉ።ወሪያቸው እኔን ያገለለ የትግርኛ ቋንቋ በመሆኑ ከሲጋራው በላይ አስጨንቆኛል።ባዕድነትም፣ብቸኝነትም ዋጠኝ። በወሪያቸው መሃል ሲጋራውን ላስቆመው ወደ አብረሃ ዞር ስል፣ ከጨረሳት ሲጋራ ላይ አዲስ ሲጋራ ሲለኩስ ደረስኩበትና ተሥፋ ቆርጬ ያሰብኩትንም ሳልናገር ከዞርኩበት ተመልሼ ወደ ፊት ለፊቴ በመዞር ተስተካክዬ ተቀመጥኩ ።ይሁን እንጂ በዚህ ዓይነት ብዙ መጓዝ አልቻልኩም ። ሁኔታው ሁሉ እየከነከነኝ በመምጣቱ ፣ በተጨማሪም የሬድዮ ግንኙነቱ ፣ በማይገባኝ ቋንቋ መጯጯኋቸው ስለበረታብኝ ተመልሼ ወደ አብረሃ አቅጣጫ እንደገና ዞሬ ስመለከት፡እኛ ከአለንባት መኪና ውሥጥ ሆኖ ከኋላ ከሚከተለን መኪና ጋር ምልክት ሲሰጣጥና ሲነጋገር ደረስኩበት። አንዳች ነገር ሰውነቴን ውርር አደረግኝ ። አሻግሬ ከኋላ የሚከተለንን መኪና ስመለከት ደብዛዛ ቢጫማ ቀለም ያለው ቶዮታ ላንድ ክሩዘር ነው ። እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ የደከመ አካሌን እረፍት እንዳያደርግ ለምን ያንገላቱታል በሚል አጉል ግድየለሽነታቸው ቅር ሲለኝ አመሸሁ እንጂ አንዳች አደገኛ ነገር እየተፈፀመ መሆኑን አልተጠራጠርኩም ነበር ። እርግጥ ነው እኔን ያገለለው የትግሪኛ ቋንቋ ንግግራቸው ፣ የሬድዮ ግንኙነቱን ጨምሮ ባዕድነት እንዲሰማኝ አድርጎኛል ።ድሮም ቢሆን እኔ የእነሱ እንዳልሆንኩ ሁሉ ፣ እነሱም የእኔ ያለመሆናቸውን ስለማውቅ ባእድነቴን ተቀብዬዋለሁ።  የአብረሃ ከሚከተለን መኪና ውሥጥ ካሉ ሰዎች ጋር በምልክት መነጋገሩ ፣ በዚህ እየመሸ ባለ ሠዓት እነዚህ ሁለት ሰዎች መካከል መገኘቴ ፣ የሬድዮ ግንኙነቱ ፣ በአጠቃላይ ከእኔ ጋር አንድም የጋራ የሆነ ጨዋታ በመካከላችን ያለመነሳቱና ከሁሉም በላይ ግን ከእኔ ቢሮ ማፕ ( ካርታ ) ፈልጎ ቢሮዬ ከደረስን በኋላ ግን የማፑ ( የካርታው ) ሥም ያለመነሳቱ ፤ ሁሉንም በአንድ ጊዜ ስመዝነው አደጋ መስል ነገር ውሥጥ እሆን ያለሁት ? ከማለት ያለፈ ብዙም አልተጠራጠርኩም ። በሰላም ሥራውን ሰርቶ የሚውልን ሰው በሠላም ወደ ማረፊያው ለመመለስ የሚከለክለው ሰው እንደማይኖር እርግጠኛ ሆንኩ ።ነገር ግን የሆነ ነገር ደስ አልልህ አለኝ። ይህንን እያሰላሰልኩ ባለሁበት ቅጽበት ሻለቃ አብረሃ ከኋላ ወንበር ተቀምጦ እንዳለ ከደብረ ዘይት ወደ ምዕራብ አቅጣጫ 8-10 ኪ /ሜ ላይ ወጣ ብላ ወደምትገኘው ዱከም ወስዶ እራት ሊጋብዘን እንደሚፈልግ ድንገተኛ ሃሳብ ይሰንዝራል ። እኔ መቼም ከነዚህ ሰዎች ጋር እራት የሚያገባብዝም ሆነ አብሮ የሚያስመሽ ጓደኝነትም ሆነ ቅርርብ የለኝም ፤ … .. ታድያ የምን እራት ግብዣ እንደሚያወራ አልገባህ አለኝ ። ስለዚህም እኔ እራት መብላት እንደማልፈልግና ባይሆን እኔን ወደ መኝታ ክፍሌ አድርሰውኝ እነሱ ለእራት እንዲወጡ ሃሳቤን ገለፅኩ ። ሁለቱም መልስ አልሰጡኝም ። በዚች ቅፅበት ወደ ዱከምና መኮንኖች ክበብ መገንጠያ ( በቀለ ሞላ ሆቴል ) ጋ ስንደርስ መኪናዋን እያሽከረከረ ያለው በሪሁ እራት አብሪያቸው መብላት ያለመፈለጌን ትኩረት ሳይሰጠው ወደ መኮንኖች ክበብ ከማቅናት ይልቅ ቀጥታውን የዱከምን መስመር ይዞ ፍጥነቱን ጨምሮ ተፈተለከ ። አሁን በእርግጥ ቅር ተሰኘሁ ። ሰውነቴም ተጨነቀ ። ምንድነው ነገሩ ? የሚለው ጥርጣሬዬም በረታ ። በሪሁ ሃሳቤን ለመስረቅ ይመስላል ፍጥነቱን እየጨመረ አደገኛ አነዳድ መንዳት ጀመሯል ። ወደ ኋላ ዞሬ ስመለከት ከኋላ የሚከተለን መኪና አብሮን ፍጥነቱን ጨምሮ ጭራችንን ይዞ ይከተለናል ። አብረሃ አይኑን አያርገበግብም ። ብቻ አፉን ከፍቶ በላይ በላዩ እየተነፈሰ ሲጋራውን ቶሎ ቶሎ ይስባል ። ወደ እኔ አቅጣጫ አይመለከትም ። አይኑን ከአይኔ ያሸሻል ። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን የደብረ ዘይትን ከተማ እየለቀቅን ዱከም ከተማ መዳረሻ ላይ ወደ አለው ሰው አልባ ጭር ያለ ሜዳ ላይ ደረስን ። ከሁሉም በላይ አካባቢው ጨለማ ወርሶታል ። ወደ መሃል አካባቢ ስንደርስ ደግሞ አብረሃ ሌላ ጥያቄ አመጣ። መፀዳዳት እፈልጋለሁና መኪናውን አቁምልኝ ብሎ በሪሁንን ይጠይቃል። ( ይህንን ንግግር ለመጀመሪያ ጊዜ በአማርኛ ሲጠቀም ) ። ወደ ዱከም መንደሮች ለመግባት ጥቂት በቀረችን እርቀት ላይ ሆኖ ሜዳ ላይ የመፀዳዳት ፍላጎቱ አልዋጥልህ አለኝ ። መኪናዋን እያሽከረከረ ያለው በሪሁ ግን መኪናዋን ለማቆም ፍጥነቱን እየቀነሰ ከመንገዱ ቀኝ ጠርዝ ላይ ሲያቆምና ከኋላችን ይከተለን የነበረው መኪና እኔ በተቀመጥኩበት ቀኝ ጠርዝ በኩል ሙሉ ለሙሉ እይታዬን ከልሎ ሲቆም እኩል ሆነ ። በፍጥነትም አራት ሰዎች ከቀኝ ከቆመው መኪና ውስጥ ዘለው በመውረድ እኔ በተቀመጥኩበት በኩል ያለውን በር በመክፈት በትግርኛ መጯጯህ ያለበት ትግል ቢጤ ግብግብ ከመፈጠሩ በስተቀር ብዙም ትዝ የሚለኝ ነገር የለም ። ከሄድኩበት ሰመመን አይነት ነገር ስነቃ ፣ በመኪና ውስጥ እየተጓዝኩ መሆኔን ቀጥሎም ሰዎች በትግሪኛ ቋንቋ እንደሚያወሩ ተሰማኝ ። አካባቢዬን ለመቃኘት አይኔን ለመግለጥ ብሞክር ምንም ለታየኝ አልቻለም ። አይኔ በአንዳች ነገር ተሸፍኗል ። እጅግ ደነገጥኩኝ ። አይኔን የሸፈነውን ነገር ለማስለቀቅ ብሞክር እጆቼን ማንቀሳቀስ ተሳነኝ ። ሁለቱም እጆቼ የፊጢኝ ታስረዋል ። ድንጋጤዬን መቆጣጠር ስለአቃተኝ ድምፅ አውጥቼ ጮህኩኝ ። የመኪናው ወለል ላይ እንዳስተኙኝና የመኪና መሸፈኛ ሸራ ነገር እንዳለበሱኝም አስተዋልኩ ። ደጋግሜ ጮህኩ ። ዝም እንድል በማስጠንቀቂያ አይነት ቃና ተነገረኝ ። ምን እንዳጠፋሁና ወዴትስ እየወሰዱኝ እንደሆነ ደጋግሜ ጠየቅሁ ። ”ዝም ጥሩ” የሚል አማርኛ ሆኖ ትግሪኛዊ ዘዬ በያዘ አነጋገር መልስ ተሰጠኝ “ሱቅ ፅቡቅ” መሆኑ ነው በትግሪኛ ። አማራጭ አልነበረኝምና ዝም ማለትን መረጥኩ ። ያላቋረጠ የሬድዮ ግንኙነት በትግሪኛ ቋንቋ ያደርጋሉ ። አልፎ አልፎ መኪናው ሙሉ ለሙሉ ይቆማል ። ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ግን ያለበሱኝን ሸራ መሰል ነገር ከላዬ ይገፉና እንድነሳ ትዕዛዝ ይሰጡኛል። እጅ እግሬ በመታሰሩ ግን አልቻልኩም ። በኋላ ግን በሁለት ሰዎች ግራና ቀኝ ተደግፌ ተነሳሁ ። እንደያዙኝም ከመኪናው አወረዱኝ ። አይኔ ተሸፍኗልና ዙሪያዬን መማተር አልቻልኩም ። ግራና ቀኝ እንደተደገፍኩ መራመድ ጀመርን ። የሆነ በር ሲከፈት ይሰማኛል ::  በሩን እንዳለፍንም ደረጃ ነገር ላይ ቁልቁል ወረድን። ከዚያም በድጋሚ አንድ በር ከፍተው ወደ ውስጥ ገፈተሩኝ ። ሚዛኔን ስቼ በፊት ለፊቴ ዥው ብዬ ወደቅሁኝ ። ቀጥለው ግን የአይኔን መሸፈኛ ፈቱልኝ ። ወዲያው ግን በሩን ዘግተውብኝ ከውጪ ሲቆልፉት ተሰማኝ ። ዛሬ ድረስ የዚያች ክፍል በር አዘጋግ ድምፅ ጆሮዬ ላይ ያስተጋባል ። የገደል ማሚቶ ያጀበው የከባድ የብረት በር ድምፅ ……… .. ። ዙሪያዬን ለማስተዋል ሞከርኩኝ ፤ ድቅድቅ ጨለማ ዙሪያዬን ውጦኛል ። ምናምኒት ጭላንጭል ለምልክት አትታይም ። ደንገጥሁ ፤ ጭንቀት በአንድ ጊዜ ወረስኝ ። የት ይሆን ያመጡኝ ? እጅ እግሬንስ ማሰር ለምን አስፈለገ ? ምን ጥፋት አግኝተውብኝ ይሆን ? እንደዚህ የሚታሰር ሰው መጨረሻው ምን ይሆን ? ጭንቅላቴ ጥያቄ በላይ በላዩ ያፈልቅ ጀመር። ለአንዱም ግን መልስ ማግኘት አቃተኝ። ውልደቴ አዲስ አበባ ይሁን እንጂ እድገቴ ሙሉ ለሙሉ ደብረ ዘይት ነው። እዚያው አየር ሀይል ደጃፍ ላይ አየር ሀይሎችን እያየሁ አደግሁ ፤ ከዚያም እዚያው አየር ሀይል ተቀጠርኩ። አለቀ። ወደ ግራ ወደ ቀኝ የሞከርኩት ነገር የለም። በ 1983 ዓ .ም . ለበረራ ሙያ ወደ ቀድሞዋ ሶቭየት ሀብረት ለስልጠና ስላክ የነበረኝ ደስታ ወሰን አልነበረውም።ተስፋዬ ሁሉ እሩቅና ጥልቅ ነበር።ከአመታት በኋላም አንድ የስልጠናና አንድ የውግያ አውሮፕላን የበረራ ትምህርቴን አጠናቅቄ ወደ አገሬ ስመለስ ከአሁን በኋላ የአገር ሀብት ነኝ ብዬ ነበር።ብዙ ወጪ ወጥቶብኛላ ! ። በተፈጥሮ ባህሪዬም ጠንቃቃ ሊያሰኝ የሚችል ቁጥብ ብሆንም ፤ ከጓደኞቼና በአጠቃላይ የስራ ባልደረቦቼ ጋር ስቆ ተጫውቶ ከመዋል በስተቀረ ወንጀለኛ ወንጀል ደፍሮ የሚሰራ ልብ የለኝም ። አደገኛ የሚባል ስብዕናም አልተላበስኩም። ወያኔ አገሪቱን ተቆጣጥሮ የአየር ሀይልን በረራ ት /ቤት “ሀ” ብሎ ስራውን ሲጀምር በበረራ አስተማሪነት አገልግያለሁ ። እያደርም እስከ ሃላፊነት ። የምሰራው ለወያኔዎች ሳይሆን ፣ ለኢትዮጵያ ነው ብዬ አስብ ነበር ። እያደር ግን የአንድን ብሄር ብቻ መርጦ ወደ በረራ ስልጠና የማምጣቱ አካሄድ ባይዋጥልኝም፤ ሙያዬን ገና “ሀ” ብዬ መጀመሬ ነበርና እስኪ ትንሽ ልሥራ ፤ ነገሮችም ይቀየሩ ይሆናል በሚል ተስፋ ቀናቶች ተቆጠሩና አመታትን ወለዱ።ዛሬ ዛሬ ግን ከወያኔዎች ጋራ ውዬ ባደርኩባቸው ጊዚያቶች አገሬንና ህዝቤን ከድቼ የነበረ ዓይነት ስሜት ይሰማኛል። እዚህ ጨለማ ቤት ውሥጥ ሆኜ በሰከንድ ውሥጥ ከውልደቴ እስከዚህች ደቂቃ ድረስ ያለችውን ጊዜ በአይነ ህሊናዬ ዳሰስኩት።ከፍርሃት በላይም ሃዘን አጥንቴን ዘልቆ ተሰማኝ። እስርን በበረራ ተማሪነት ዘመኔ ከጓደኞቼ ጋር የዲሲፕሊን ጥፋት አጥፍተን ስንገኝ ከእነጓደኞቼ ለአንድ ቀን ወደ ከተማ እንዳንወጣ የመጠበቅ አይነት በአንድ ቦታ እንውላለን ፣ እናድራለን ። ያንን ታድያ እሥር እንለው ነበር ። ዛሬ ግን ሰማይ የተደፋብኝ ያክል ተሰማኝ ። ከሰላማዊ ህይወቴ በአንድ ጊዜ ድቅድቅ ጨለማ ውሥጥ የፊጢኝ ታስሮ መገኘት ምን ይባላል ? ለምን ያክል እዚህች ጨለማ ክፍል ውስጥ እንደቆየሁ መገመት ቢያቅተኝም ፤ እዚያው የቆምኩበት ሳሰላስል ሌሊቱ ተገባድዋል ። እርግጠኛ ነኝ ከምድር በታች የተሰራች ክፍል ውስጥ ነኝ ። ቀስ በቀስ ውርጭ መሰል ቅዝቃዜ ተሰማኝ ። ጠዋት ከቤቴ ስወጣ የግንቦት ጀንበር ክርር ብላ ታቃጥል ነበርና ጃኬት እንኳ አልደረብኩም ። ከውስጥ ከአንዲት ስስ ካኒተራ በስተቀር ከላይ የበረራ ቱታ ነው የለበስኩት ። ቅዝቃዜው ጀርባዬን እየጨመደደኝ ቢመጣም ደንታ አልነበረኝም። እግሬን ድንዝዝ ብሎኝ ለረዥም ሰዓታት መቆሜን ይነግረኛል ። ከአንዲት ቦታ በፍፁም አልተንቀሳቀስኩም ። ጭንቅላቴ ሊፈነዳ ደርሷል ።  ጫማዬን፣ ቀበቶዬን አስወልቀውኛል ። በኪሴ ውስጥ የነበረች ብጣሽ ወረቀት እንኳ አልቀረችም ። ሰዓቱ ስንት እየሆነ እንዳለም መገመት በፍጹም አልቻልኩም ። ለነገሩ ግድም አይሰጠኝም ። የእኔ ጭንቀት ምን ያደርጉኝ ይሆን ነው ። በደርግ ዘመን የወጣቶች የእስር ቤት ውስጥ ድብደባ በእራሴ ላይ ባይደርስም በቅርብ እያየሁትና እየሰማሁት ነው ያደግኩት ። የፈለጉትን ያድርጉኝ ፤ ብቻ እንዳይደበድቡኝ ነው ፀሎቴ ። ሰው የት እንደገባሁ ያውቅ ይሆን ? ከሁሉም በላይ እናቴና ፍቅረኛዬ ታወሱኝ ። በይበልጥ እናቴ የልብ ህመምተኛ ናት ። መድሃኒት ለአንዲት ቀን አይደለም ሰዓቱን እንኳ ብታሳስት ህይወቷ አደጋ ላይ እንደሚሆን በሀኪሞች ተነግሯታል ። ትንሽ ነፍሷ እንዲቆይልኝ እማላደርገው ነገር የለም ። አሁን ታድያ ምን ይውጣት ይሆን ? የእኔን መሰወር ሰምታ የመድሃኒት መውሰጃ ሰዓቷን መከታተል ታቆም ይሆን ? ለህይወቷስ መጥፋት እኔ ሰበብ እሆን ይሆን ? ……………… . በጭንቀት እራሴ ዞረ። ይህንኑ በማሰላሰል ብቻ ከአንድ ቦታ በፍፁም ሳልንቀሳቅስ ለረዥም ሰዓታት ቆምኩ ። በመጨረሻ ግን የሆነ መስኮት ነገር ተከፍቶ ወዲያው በፍጥነት የመዘጋት አይነት ድምፅ ተሰማኝ ። ወደ ውስጥ የገባ ነገር እንደሌለ በማዳመጥ አረጋገጥሁ ። አልፎ አልፎ የኮቴና የመንጓጓት ድምፅ ይሰማኛል። ወዲያው ግን እረጭ አለ ። እግሬን በማንቀሳቀስ ትንሽ ወዲህና ወዲያ እንዳልል እንኳ ምን ታይቶኝ ? ድንግዝግዝ ያለ ጨለማ ወርሶኛል ። ከአሁኑ ሞቴን መረጥኩ ። ሊመጣ የሚችለው መንገላታት ከአሁኑ አሳሰበኝ ። በእርግጥ ምግብ ከቀመስኩ 24ሰዓት ሳይሆነኝ አይቀርም ። እያቅለሸለሸኝና እያጥወለወለኝ ነው ። አሁን አሁን ያለሁበት ክፍልም ሽታ እንዳለው እየታወቀኝ ነው ። ቀስ እያልኩም ከምናምን ጋራ እንዳልጋጭ እጄን ወደፊት ዘርግቼ ለመራመድ ሞከርኩ ። እግሮቼ በአንድነት ተያይዘው በሰንሰለት ታስረዋልና በእግሬ ጣቶች መሬቱን እየቆነጠጥኩ ለመንሸራተት መሞከር እንጂ መራመድ የማይታስብ ሆነ ። እንደምንም እየተንፏቀኩ ግድግዳ ጋ ደረስኩ ። ወደ ግድግዳው በተጠጋሁ ቁጥር ግን ሽታውና ክርፋቱ ባሰብኝ ። ይሁን እንጂ በታሰሩት ሁለት እጆቼ ግድግዳውን እየዳሰስኩ ዙርያውን ለመቃኘት ሞከርኩ ። ከባድ ነው ። መነቃነቅ አቃተኝ ። በመቆም ብዛት በደነዘዘው እግሬ የትም መድረስ አልቻልኩም ። ተሥፋ መቁረጥ ግን አልፈለኩም ። መዳሰሴን ቀጠልኩ ። ያለሁባት ክፍል እጅግ ጠባብ ናት ። ግድግዳው ብሎኬት ዓይነት ይሰማኛል ። የተፈረካከሰ ግድግዳ ነው ። መዳሰሴን ቀጠልኩ ። ድንገት ጄሪካን ነገር እግሬ ነክቶ ተደፋ ። ፈሳሽ ነገር ነው ። እጅግ መጥፎ ሽታ አለው ። ሽንት መሆን አለበት ። የተደፋውን ጄሪካን ለማንሳት አልቻልኩም ። በአንድ በኩል ግማቱ ፣ በሌላው ደግሞ እግሬ መታሰሩ ለማጎንበስ ሚዛኔን መጠበቅ አቃተኝ ። ምንም ማድረግ አልችልም ። የፈሰሰው ግማት ላይ በእግሬ መንሸራተቱን ቀጥያለሁ ። የብረት መዝጊያ ነገር ነካሁ ። በሩ መሃል ላይ ደግሞ ትንሽ መስኮት ነገር ያለው ይመስለኛል ። እቃ ማስቀመጫ ትንሽ መደርደሪያ ነገር አለው ። ኩባያ ነገር ከተቀመጠበት በእጄ ነክቼው ተደፋና መሬት ሲሚንቶው ላይ ሲወድቅ አገሩን በጩህት በጠበጠው ። ክው ብዬ ደነገጥኩ ። ያልጠበቅኩት ድምፅ ነበርና እኔኑ መልሶ አስደነገጠኝ ። ሁኔታውንም እስከማገናዝብ የልቤ ምት ጨመረ ። እንዲሁ እያልኩ ያለሁባትን ክፍል በዳበሳ ጨረስኳት ። እጅግ ጠባብ ነች ። ወለሉ ላይ የፈሰሰው ሽንት መሰል ነገር ግማታም ፈሳሽ ምን አልባትም እዚህች ጠባብ ክፍል ውሥጥ ሌላ የእኔ ቢጤ ይኖር ይሆን የሚለውን ጥያቄ በአእምሮዬ ውሥጥ አጫረው ። በአይኔ ማየት ባልችል ፣ አንዳች ኮሽታ ድምፅ በማጣቴ ብቻዬን መሆኔን አረጋገጥኩኝ ። ይሁን እንጂ እስከ ቅርብ ሰዓት ድረስ ሌላ ሰው ነበረበት ማለት ነው ። ጭንቀቱና ጥርጣሬው እየባሰብኝ መጣ ። ከሁሉም በላይ በደርግ ጊዜ የነበረው የወጣቶች የጅምላ ግርፊያና ግድያ ታወሰኝ ። እጅግ አሰቃቂ ዘመን ነበር ። ዛሬ ደግሞ እኔም በተራዬ እዚህ አደገኛ ክስተት ደጃፍ ላይ ሳላስበው ድንገት መገኘቴ መፈጠሬን አስጠላኝ ። እስከ አሁን ማንም ወደ እኔ የመጣ የለም ። ከክፍሌ ውጪ ግን አልፎ አልፎ የመንጓጓት ድምፅ ይሰማኛል ። በሃሳብ ደንዝዤ ከአንድ ቦታ ሳልነቃነቅ ተገትሬ ባለሁበት ሰዓት ፤ የአለሁባት ክፍል በር ተከፈተና ባትሪ የያዙ ሁለት ሰዎች ወደ ውስጥ በመግባት ግራና ቀኝ ደግፈውኝ ወደ ውጭ እንድራመድ ትእዛዝ ሰጡኝ ። መንፈሴ መሰበር ጀምሯል ። የመብላት ፍላጎት አይኑረኝ እንጂ ምግብ አለማግኘቴም አድክሞኛል ። ሃሳቡ ፣ ጭንቀትና ፍርሃቱ በአንድነት ተባብረው መንፈሴንም አካሌንም ስብርብር አድርገውታል ። በተስፋ መቁረጥ ዝም ከማለትና የሚሉኝን ከማድረግ በስተቀር ቃል አልተነፈስኩም ። በሁለት ሰዎች እንደተደገፍኩ ከአለሁባት ክፍል ቀጥላ ወደ አለች ሌላ ክፍል ውስጥ አስገቡኝ።ክፍሏ ጠበብ ያለች ነች ።ደብዘዝ ያለ መብራት በርቶባታል ። ውስጧ ንፅህናዋ የተጠበቀ አይደለም ። ቆሸሽ ካለ ጠረጴዛ ጅርባ አንድ ሰው ተቀምጧል ። ጥቁር ነው ። ከርዳዳ ፀጉሩ የተበጠረ አይመስልም ። ግዙፍ ሰውነቱና የደፈረሰው አይኑ ሰላም አይሰጡም ። ምንም ሳይተነፍስ ዝም ብሎ አተኩሮ ያየኛል ። ከጎኑ የቆመ ቀላ ያለ ቀጭን አጭር ሰው አለ ። ሁለቱም አተኩረው ያዩኛል ። ግራና ቀኝ ደግፈው ያመጡኝ ስዎች ውስጥ ካሉት ጋራ በትግርኛ ቋንቋ ከተነጋገሩ በኋላ ክፍሏን ለቀው ወጡ ። ከበሩ አጠገብ ካለች ቆሻሻ ወንበር ላይ እንድቀመጥ ቀዩ አጭሩ ሰውዬ ምልክት ሰጠኝ ። ቀጥሎም ማን እንደሆንኩ የህይወት ታሪኬን እንድነግረው ጠየቀኝ ። አጠር አጠር አድርጌ ደብረ ዘይት ከተማ ማደጌን፤አየር ሀይል መቀጠሬን ፣ ለበረራ ሙያ የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት መላኬንና ከደርግ መሸነፍ በኋላም በበረራ አስተማሪነት እያገለገልኩና የጀት በረራ ስልጠና ስኳድሮን አዛዥ መሆኔን ሁለት ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ ጠቅለል አድርጌ ነገርኩት። ለተወሰነች ደቂቃ ትኩር ብለው ስያዩኝ እኔም ምን ሊከተል እንደሚችል በመጓጓት መልሼ አይን አይናቸውን እያየሁ ሳለ አሁንም ቀድሞ ጥያቄ ያቀረበልኝ ቀዩ አጭሩ ሰውዬ እዚህ እንድመጣ ያደረገኝን ጥፋት እንድናዘዝ ይጠይቀኛል። እኔም በመመለስ እስከ አሁን ጥፋቴ ግልፅ እንዳልሆነልኝና አጥፍተሃል የምባለው ነገር ካለ ግን ቢነገረኝ ለመናዘዝ ዝግጁ መሆኔን አሳውቅሁ ። ሁለቱም እርስ በእርሳቸው እየተያዩ የለበጣ ፈገግታ ተሰጣጡ። የተናገርኩትን ያለማመን ሁኔታ መግለጫ ሆኖ ተሰማኝ ። አንድ ሁለት ቃላት በትግሪኛ ተነጋገሩና ያው የሚያናግረኝ የነበረው ሰውዬ “ እኛ የምንነግርህ ምንም ነገር የለም እራስህ በፈቃደኝነት ብትናዘዝ የሚሻልህ ይመስለኛል፤እምቢ ካልክ ግን ምርጫው ያንተ ነው “ የሚል የማስፈራራት ቃና ባለው አይነት ተናገረኝ ። ቶሎ ብዬ እራሴን ፈተሽኩ ። ምን አድርጌ እንደሆነ አወጣሁ አውረድኩ ግን ጥፋት ነው የምለው ምንም ነገር አንዳልፈፀምኩ እርግጠኛ ሆንኩ። በመሆኑም እኔ ከሰላማዊ የዕለት ተዕለት ተግባሬ ላይ በማላውቃቸው ሰዎች ታፍኜ እንደመጣሁና አጥፍቻለሁ የምለው ምንም ነገር ትዝ እንደማይለኝ በእርግጠኛነት ተናገርኩ ።አሁንም ሁለቱ በትግሪኛ ተነጋገሩና ከዚያም ወደ እኔ በመዞር በሰላም ሁሉንም እንድትነግረን እድል ተሰጥቶህ ልትጠቀምበት ፈቃደኛ አልሆንክም ስለዚህ የ 24 ሰዓት ጊዜ እንሰጥሃለንና ተጠቀምበት ብለው ደግፈው ያመጡኝን ሰዎች ጠርተው በተለመደው የትግሪኛ ቋንቋ የሆነ ነገር ብለዋቸው በመጣሁበት ዓይነት እግሬን የታሰርኩበት ሰንሰለት እንደልብ ስለማያራምደኝ ግራና ቀኝ ደግፈው ቀስ እያልኩ እየተራመድኩ ወደዚያች መልኳን እንኳ በእርግጥ ወደ ማላውቃት ጨለማ ክፍሌ መልሰውኝ በሩን በጀርባዬ ቆለፏት። በእርግጥ ነገሩ ጠጠር ብሏል ማለት ነው ።አንድ ነገር ግን መላልሶ ቅር ያሰኘኝ ጀመር ። አገሪቷን እንደፈለጉ እያደረጉ ያሉት ትግሪኛ ተናጋሪዎች መሆናቸውን ከተረዳሁ አመታት ያለፉኝ ቢሆንም እንደዚህ ግን ሁሉንም ጉዳይ ፈላጭ ቆራጭ መሆናቸው በእጅጉ አሳዘነኝ ። ኢትዮጵያ የማን ናት ? እኔስ የማን እሆን ይሆን ? መልስ ላገኝለት አልቻልኩም። ድሮ ድሮ ልጅ ሆኜ ደብረ ዘይት ከተማ ከትግራይ ቤተሰብ የተወለደ የቅርብ ጓደኛ ነበረኝ። አብረን ውለን እናድራለን።አብረን አንድ ክፍል ውስጥ ቁጭ ብለን ተምረናል።እነሱ ቤት ሄጄ እበላለሁ እጠጣለሁ፤ እሱም በተራው እኛ እቤት እየመጣ ይበላል ይጠጣል።አንድም ቀን ትግሬ መሆኑ ትዝ ሳይለኝ አንድ ላይ ስራ ገብተናል። በአየር ሀይል ቆይታዬም ውስጥ እጅግ ቅርበት ያለን፣ ለአንድ ድቂቃ እንኳ መለያየት የሚያቅተን ቤተሰቦቻቸው ትግሬዎች የሆኑ ጓደኞች አሉኝ ። በሰላም እንኖራለን ።  አሁን እየደረሰብኝ ባልው ሁኔታ ግን ስሜቴ ደፈረሰብኝ ። ከስራ ቦታዬ እያታለሉ አቆይተው ያሳፈኑኝ ትግሬዎች ነበሩ ። በመኪና አፍነው ወደዚች ጨለማ ክፍል ያመጡኝም ትግሬዎች ናቸው ። ከአለሁባት ጨለማ ክፍልም እየገፉ ቢሮ መሰል ነገር ውስጥ ያስገቡኝም ትግሬዎች ናቸው ። ጥፋቴን ተናዘዝ እያሉ የሚያስለፈልፉኝም ትግሬዎች።እንዴት ነው ይህች አገር ያለ ትግሬ ውላ ማደር አቃታት ማለት ነው ? ይህች አገር የትግሬዎች ከሆነችስ ታድያ የእኔ አገር የት ነው ? ለምን ያክል ሰዓት አንድ ቦታ ቆሜ በሃሳብ እንደምብሰለሰል መገመት አልቻልኩም እንጂ መቀመጥ ከነመኖሩም ረስቼዋለሁ ።ጋደም እንኳ ለማለት የክፍሏን ዙርያ በዳበሳ ባስስ ምናምኒት ጨርቅ እንኳ ማግኘት አልቻልኩም። አሁን አሁንስ ረሃቡም በቅጡ እንዳላስብ እያደረግኝ ነው። ድክምክም ብያለሁ ። በዳበሳ በሩ ላይ ካለው መደርደሪያ ነገር ላይ ቁራሽ ዳቦ ነገር አገኝሁ ። ለካስ በበሩ መሃል ባለችው ማሸንቆሪያ ነገር ደረቅ ዳቦ ይጥሉልኛል ።ይሁን እንጂ የቤቱ ግማት እህል ለመብላት አይደለም ለመተንፈሱም ይግድ በመሆኑ እንጂ አይቻልም። አሁን ግን አማራጭ የለም ። እጄ ሁሉ ቆሽሿል ። በሽንቱም በዳበሳውም እንዳልነበረ ሆኗል።ግን ዳቦዋን በታሰሩት ሁለት እጆቼ መሃል ይዤ አንድ ሁለቴ በጥርሴ እየገመጥኩኝ አኝኬ ለመዋጥ ሞከርኩ ። ከዚያ በላይ ግን መውሰድ አልቻልኩም ። ለካስ ውሀም ያስፈልገኛል ፤ ማግኘት ግን አልቻልኩም ። በጥም ተቃጠልኩ ። አካሌ በመዛሉ ግድግዳ ተደግፌ ቁጢጥ አልኩኝ ። ቅዝቃዜውም እየበረታብኝ መጣ ። በዚህ ዓይነት እየተሰቃየሁ እያለሁ ያለሁበት ክፍል በር ተከፈተ ። ወደ ውስጥ ገበተው ይዘውኝ ወጡ ፤ ሽንት መሽናት እንደምፈልግ ነገርኳቸው ። ነገር ግን ውስጥ ጄሪካን እንደነበረልኝ ከመጠቆም በስተቀር ያደረጉልኝ አልነበረም ። በቀጥታ ከጐኔ ወደ አለች ክፍል ሊያስገቡኝ የበሩን ደፍ እንዳለፍኩኝ ሃይለኛ ቡጢ ሰውነቴ ላይ አረፈ ። ተሽከርክሬ ወደቅሁ ።በኤሌክትሪክ ገመድ ዓይነት ክፉኛ ገረፉኝ ፤ የጠየቁኝ ነገር የለም ። እንድናገርም ምንም ጊዜ አልሰጡኝም ። ውስጥ እግሬን፣ ውስጥ እጄን፣ ጀርባዬን ይገርፉኛል። ተቃጠልኩ ። በመጨረሻ ግን እራሴን ሳትኩ ።ስነቃ እንደዝያው እጅ እግሬ በታሰረበት አኳኋን ወለል ላይ ተዘርሪያለሁ ። እሬሳዬ እንጂ በህይወት ከዚህች ክፍል እንደማልወጣ እርግጠኛ ሆንኩ ። ለሁለተኛና ለሶስተኛ ጊዜም እንዲሁ እየተሸከሙ ወስደው መፈጠሬን እስክጠላ ገርፈውና ቀጥቅጠው ይመልሱኛል ።የለበስኳትን የበረራ ቱታ በላዬ ላይ ቦጫጨቁዋት ። እግሬና ጀርባዬ ክፉኛ ቆሰለ ።በጣም አዘንኩ ፤ በጣም አለቀስኩ ። ጥፋቴን እንኳ አውቄ በሆነ ኖሮ ደስ ባለኝ። ግን ምን ተገኝቶብኝ ይሆን ? የፈለገውን ጥፋት አጥፍተሃል ቢሉኝ እንኳ፣ ለዚህ ቅጣት የሚያደርስ ወንጀል የሚሰራ ልብም ስብዕናም እንደሌለኝ ለራሴ እርግጥኛ ሆንኩ ። ትግሬ ይሁን ወያኔ ጠላቴ የትኛው እንደሆነ ለመለየት ተሳነኝ ። ሁለቱንም ግን በጅምላ እንድጠላ ውስጤ ጥንስስ ተጠነሰሰ። ስንቱ ኢትዮጵያዊ በወያኔና በትግሬ መከላከል ያለውን ልዩነት እንዳያይ አድርገውት ይሆን ? ቤት ይቁጠረው ……… . ። ከአሁን በኋላ ለእራሴ እራሴው ካልሆኩኝ በስተቀር ማንም ሊያስታምመኝም ሊያድነኝም እንደማይመጣ አረጋግጫለሁ ። ስለዚህ በረሃብ ብዛት ሰውነቴ ላይ ያሉ ደምስሮች ሁሉ መንዘር ጀምረው ከፍተኛ ህመም ፈጠሩብኝ ። ሆዴን ሳይሆን ንዝረቱን ማቆምና ማስታገስ ነበረብኝ ። በሆዴ እየተሳብኩ በዳበሳ የማገኛትን ደረቅ ዳቦ በምራቄ እያራስኩ መቀማመስ ጀመርኩኝ ። አሁን አሁን በቀን አንዴ ዳቦና ኩባያ ውሃ በበሩ አሸንቁረው ያስቀምጡልኝ ጀመር። ማንንም አላይም፤ እነሱም ወደውስጥ መግባት አይፈልጉም ። በቀን አንድ ጊዜም እዚያው ኰሪደር መሰል መተላለፊያ ውስጥ ባልች ሽንት ቤት ውስጥ መፀዳዳት ጀመርኩ ። የሚገርመው ግን የእጄንም ሆነ የእግሬን ሰንሰለት ያለመፍታታቸው ነው ። በምፀዳዳበት ጊዜ እግሬ በመታሰሩ ምክንያት ሚዛኔን ጠብቄ መቀመጥ አልቻልኩም ። እጄ በመታሰሩ ደግሞ ሱሪዬን መፍታት እንኳ ብችልም መልሶ ለመታጠቅ ግን ፈፅሞ የማይታሰብ ነው ። ይሄ ደግሞ እጅግ ቅስም ይሰራል ። በዚህ ዓይነት አሰቃቂ አኳኋን በግምት ለአንድ 20 ቀናት እንደቆየሁ አንድ ቀን ከለመድኩት ሰዓት ውጪ የክፍሌ በር ተከፍቶ ሁለት ሰዎች እየተጣደፉ በመግባት ግራና ቀኝ ደግፈው አይኔን በመሸፈን ይዘውኝ በመውጣት መኪና ላይ ጭነውኝ መንገድ ቀጠልን ። ይዘውኝ የሚሄዱትን ሰዎች ቁጥራቸውን በውል ባላውቀውም ከሁለት በላይ ናቸው። ዘና ያለ ወሬ የያዙ ይመስላሉ ። የሚጠቀሙት ያው የተለመደውን ትግሪኛ ነው ። ልቤ እጅግ ቢፈራም የማመጣው ነገር ማለመኖሩ ተስፋ ቆርጫለሁ ። አሁን እኔነቴ ብዙውን በድን ሆኗል ። በልቤ እፀልያለሁ ። ከውጪ የሚገባው አየር ቀዝቃዛ ነው ። ያፈኑኝ ዕለት ግንቦት መጨረሻ ደረቅና ሞቃታማ እንደነበር አስታውሳለሁ ።አሁን ክረምቱ እየገባ መሰለኝ ። እንደ ግምቴ ከሆነ አሁን ሰኔ ሳይጋመስ አይቀርም። እርግጠኛ ነኝ ከ 30-40 ደቂቃ በላይ ተጉዘናል … .. መጨረሻ ግን መኪናዋ ሙሉ ለሙሉ ቆመችና ግራና ቀኝ ደግፈውኝ ወረድኩ ። ከሆነ ሰው ጋርም በትግሪኛ ተነጋግረው ወደ ሆነች ክፍል ገፍተው ካስገቡኝ በኋላ አይኔ የተሸፈነበትን ጨርቅ ገልጠውልኝ በሩን ከጀርባዬ ቆልፈው ድምፃቸው እየራቀኝ በመምጣቱ መሄዳቸውን ገመትኩኝ ። የአሁኗም ክፍሌ ጠባብ ናት …… እንዲያውም ከበፊቱ በጣም የምትጠብ ይመስለኛል። ምክንያቱም በዳበሳ ስቃኛት ጊዜ አልፈጀችብኝም ። ቅዝቃዜዋ ግን አይጣል ነው ። ከበሩ በላይ ባለች የአየር ማስገቢያ ቀዳዳ በኩል ቀዝቃዛ ንፋስ ወደ ውስጥ ይነፍሳል … . ወለሉን ስዳብስ ፎጣ መሳይ ጨርቅ ነገር ከአንደኛው ማዕዘን ላይ ተዘርግቷል። አሁን አሁን እስካልደበደቡኝ ድረስ ተመስገን ማለት ጀምሪያለሁ ።ለረዥም ሰዓታት አንድ ቦታ ቆምኩኝ …… ይሁን እንጂ ቅዝቃዜውን መቋቋም አቃተኝ … .. አጥንትን የሚሰብር ብርድ ተሰማኝ ። ስለዚህም እዚያች ፎጣ መሳይ ብጣሽ ጨርቅ ነገር ላይ ኩርምት ብዬ ቁጭ አልኩኝ። የተለመደው የዝምታ ኑሮ በአዲሷ ጠባብ ጨለማ ክፍሌ ውስጥም ቀጠለ … . የሚያናግረኝ የለም … . እንዲህ አጥፍተሃልም የለም … እንዲሁ ዝም ዝም ብቻ ።ክፍሏ ውስጥ በእግሬ በመራመድ እንኳ እንቅስቃሴ እንዳላደርግ አንደኛ ክፍሏ ጨለማ የወረሳት ናት ፤ ሁለተኛ ጥበቷ ብዙም ሊያንቀሳቅስኝ አይችልም… . ከሁሉም በላይ ግን የእግሬ በሰንሰለት መታሰር ሁሉንም እርግፍ አድርጐ ከመተው በስተቀር አማራጭ እንደማይኖር ይነግረኛል ። አሁን አሁን በቀን አንድ ዳቦ ሊጥሉልኝ ከበሩ በታች በተሰራች ጠባብ መስኮት ነገር ከፈት አድርገው በፍጥነት ሲዘጓት ይሰማኛል ።አካባቢዬ ሁሉ እረጭ ያለ ፀጥታ የወረሰው በመሆኑና ቅዝቃዜውም እየከበደኝ በመሆኑ ከእነ ህይወቴ የተቀበርኩ እየመሰለኝ መጣ ። ይህንን ቅዝቃዜና ዝምታ መቋቋም እንደማልችል ከውዲሁ ለእራሴ ነገርኩት …… አሁንም እንደበፊቱ እኩለ ሌሊት ግድም ይመስለኛል ( ሰዓት መለየት በእጅጉ ጠፍቶብኛል )… . እዚያችው ከጠባቡዋ ክፍሌ ጐን በተሰራች ሽንት ቤት እንድጠቀም ያደርጉኛል ………… ..ባትሪ የያዙ ሰዎች ከመሆናቸው በስተቀር አንድም ጊዜ ፊታቸውን ለማየት አልታደልኩም ። እርስ በእርሳቸው ሲነጋገሩ ግን የትግሪኛ ቋንቋ መሆኑን አረጋግጫለሁ ። ከዚህ አሰቃቂ መከራ ልገላገል የምችለው ግን በአንድ መንገድ ብቻ መሆኑን አምኛለሁ …… .. ያም እራሴን ማጥፋት ብቻ …… . በምን እራሴን ላጠፋ እንደምችል ግን ማግኘት አቃተኝ ። ብዙ ሰዎች በቅርብ ከማውቃቸው ጭምር ጥሩ ህይወት እየነበራቸው በወጣትነት ዘመናቸው እራሳቸውን አጥፍተዋል ። ታድያ ለእኔ እዚህ ጉድጓድ ውስጥ በህይወት ተቀብሮ ነፍሴ እስከምትወጣ ከመጠበቅ በስተቀር ቆይቶ ለማይቀርልኝ ሞት ከውዲሁ ስቃዬን ለማሳጠር ወሰንኩ።  እጄም እግሬም በሰንሰለት የታሰረ ከመሆኑም በላይ ይሄነው ይምለው እራሴን በቶሎ ለማጥፋት ልጠቀም የምችልበት ነገር አጣሁ…… .. አንድ አማራጭ ግን አለ ፤ ይኅውም ምግብ ማቆም ብቻ ነበር ። አንድ ቀን በጣም ሆድ ብሶኝ እያለቀስኩ ፀለይኩ ……… በህይወት ዘመኔ እግዚአብሄርን አስቀይሜውለሁ ብዬ የማስባቸውን ጥቃቅን ነገሮች ሳይቀሩ በማስታውስ አምላኬን ይቅርታ ጠየቅሁ ። ከዚያች ቀን ጀምሮም አንዳችም ከሚሰጡኝ ዳቦ ላለመቅመስ ወሰንኩ ። እርግጠኛ ነኝ ሶስት ቀን ያለምግብ ያሳለፍኩ ይመስለኛል ። ምግብ ስለማልውስድ ነው መሰለኝ ውሃ በፍፁም ትዝ ብሎኝ አያውቅም …… . ርቦኝ ርቦኝ… .. ሆዴም ጮሆ ጮሆ መጨረሻ ላይ ትቶኛል ። ሙሉ ለሙሉ የመብላት ፍላጐቴ ጠፍቷል…… .እየደከምኩና እንቅልፍ እንቅልፍ እያለኝ መጣ ።ምን አልባት አራተኛው ቀን ይመስለኛል ሰውነቴን ሁሉ ይነዝረኝ ገባ ። ጭንቅላቴን ፣ እጆቼን ፣ አንገቴ አካባቢና አይኔ አካባቢ ያለውን ሁሉ ንዝረት መቋቋም አቃተኝ ። የህመም ስቃዬን ማስታገስ ነበረኝ ፤ በሩ ስር ሁልጊዜ በዳበሳ ከማገኛት ኩባያ ውስጥ ያገኘሁትን ውሃ በአንድ ትንፋሽ አንስቼ ጨለጥቁት ። ላብ ነገር እንዳጠመቀኝ ትዝ ይለኛል ። በተረፈ ለረዥም ጊዜ እዚያች ቀዝቃዛ ሲመንቶ ላይ በተዘረጋች ብጣሽ ፎጣ መሳይ ጨርቅ ላይ ኩርምት ብዬ ተኛሁ ። ስነቃ እጅግ እርቦኛል …… . ምንም ማድረግ አልቻልኩም ፤ በዳበሳ መሬት ላይ ያገኝሁትን ዳቦ አንስቼ መብላት ጀመርኩ ። ከመጀመሪያው ቀን የበለጠ ድምፅ አውጥቼ ስቅስቅ ብዬ አልቅስኩ ። መብላቴን ፣ መሸነፌን አልወደድኩትም …… ምክንያቱም የጊዜ ጉዳይ እንጂ ከዚህች ክፍል እሬሳዬ እንደሚወጣ እርግጠኛ ሆኛለሁ ። እስከዚያች እለት ያለውን ስቃይና መከራ ማንም ሰብዓዊ ፍጡር አይችለውም ። በሌላ ጊዜም ሁለት ሶስቴ ምግብ ለማቆም ሞከርኩ ……ግን ያው ነው … ያንን ንዝረትና ህመም ተቋቁሜ ማለፍ ተሳንኝ ። ዛሬ ዛሬ እነዚህ ጅቦች እጅ ከገባሁ 4-5 ወራት እየሆነኝ ይመስለኛል … .. ከወደ መሃል አናቴ ጀምሮ ወደ ግምባሬ እየሳሳ የመጣው ፀጉሬ እንኳ ጐፍሯል ። በአየር ሀይል የረዥም ጊዜ ቆይታዬ ምክንያት ፀጉሬ ከአንድ ሳንቲም በላይ አሳድጌ አላውቅም …… .. የአሁኑ ግን ጉድ መስሎ ተሰማኝ ፤ የፊቴ ላይ ፀጉርም እንደነገሩ አድጓል ። በይበልጥ የአገጭ ፂሜ መተከዣ ከሆነኝ ሰንባብቷል ።በሰንሰለት የታሰሩ ሁለት እጆቼን ደረቴ ላይ በማሳረፍ በቀኝ እጄ ጣቶች የአገጬን ፂም ሳብ ሳብ እያደረግሁ በሃሳብ እርቄ እሄዳለሁ ። በየሰከንዱ ግን እናቴ ፊቴ ላይ ድቅን ትላልች … .. እየተቀጣሁ ያለሁት እኔ ብቻ እንዳልሆንኩ ይሰማኛል …… ምንም ወንጀል የሌለባት አዛውንቷ እናቴም በሰቀቀንና ስጋት እየተቀጣች መሆኑ ይሰማኛል…… በእኔ ምክንያት ህይወቷ ያልፍ ይሆን ? ወይኔ ጉዴ ! … .. ወንጀለኛነት ይሰማኝ ጀመር ፤ አልፎ አልፎም እጅግ የምወዳትን ፍቅረኛዬን አስባለሁ …… . ድንገት ነው እንደወጣሁ የቀረሁት ፤ ሊያሶሩብኝ የሚችሉትን የወንጀል መዓት ብትሰማ ታምናቸው ይሆን ? እላለሁ ።ላታምን የማትችልበት ምክንያት አይኖርም … ፍቅረኛዬ እንጂ እናቴ አይደለች ፤ … . ? በእልህ ጥርሴን እነክሳለሁ … ..እየሞተ ባለው አካሌና መንፈሴ ቂም እቋጥራለሁ ። እዚያችው ጉድጓድ ውስጥ እንደምሞት እርግጠኛ እየሆንኩ እንኩዋ እናቴን ያለውንጀሏ እየቀጣብኝ ያለውንና ፣ የወደፊት ሚስቴን እየቀማኝ ኑሮዬን እያፈረሰ ያለውን ወያኔ ቂም እንደቋጠርኩበት ነው ። ውሃ ለሰውነት መታጠቢያም እንደሚያገለግል አሳሪዎቼ ጋ የሚታወቅ አይመስለኝም … .. ግና ለሚሞት ሰው መታጠብ ምን ሊያደርግለት ? እውነቴን ነው የምላችሁ ሰውነቴን አይደለም ፊቴን ታጥቤ አላውቅም … . ጥርስ መቦረሽ ምናምን የሚባሉት እዚህ ያለሁበት ስፍራ በፍፁም አይታውቁም ። የለበስኳቸው የውስጥ ካናቴራና ፓንቴ እላዬ ላይ በመበታተናቸው ቀድጄ ካላዬ ላይ አውልቄ ከጣልኩ ሰንብቻለሁ … .. የበረራ ቱታዬ የቀንም የሌሊትም ልብሴ በመሆኑ ጉልበቴ ላይ ፣ ከኋላዬ ፣ ትከሻዬ ላይ ፣ በተጨማሪም እግሬና እጅጌዬ ጫፍ ጫፍ ላይ ተቀዳዷል ። እራሴን ማየት ባለመቻሌ እንጂ ጥሩ እብድ መምሰሌን እርገጠኛ ነኝ ። ቀስ በቀስ ግን አቅሜ በእጅጉ እየደከመ እየደከመ ህመም ይሰማኝ ጀመር …… . እንቅልፍ የሚባል ተኝቼም ስለማላውቅ ጭንቅላቴ ደንዝዞ ሰውነቴ ቅልል እያለኝ መጥቷል ፤ እንደቀድሞው ቆሞ ማደርና መዋል አቃተኝ … ሚዛኔን በፍፁም መጠበቅ የማይታሰብ ሆነ ። ከሁሉም በላይ ግን አንዳችም ድምፅ ስለማይሰማኝ .. የረዥም ጊዜው ዝምታ ጆሮዬ ላይ ኡኡኡኡ…… .የሚል ድምፅ ፈጠረብኝ ። ይህንን ድምፅ ከጆሮዬ ማስወገድ አቃተኝ … ቀጥሎም የልቤ ምት ቀየረ … . ይደክመኛል ። ብዙውን ጊዜም ትንፋሼ እየተቆራረጠ አስቸገረኝ ። መንገዴን እንደጀመርኩ እርገጠኛ ሆንኩ ። ሞትን ብመኘውና ብፈልገውም እንደዚህ ዓይኑን አፍጥጦ ልወስድህ ነው እያለኝ ሲመጣ ግን ጉልበት ከዳኝ … . እጅግም ፈራሁ … . አዘንኩም … .. ተስፋዬም ሙጥጥ ብሎ አለቀ ። በዳበሳ ያገኘሁትንም በር መደብደብ ጀመርኩ … ..ድምፄን ከፍ አድርጌም መጮህ ጀመርኩ ። የመጀመርያ ሁለትና ሶስት ቀን ምን እንደምፈልግ ጠየቁኝ … . ወደ ሰው እንዲቀላቅሉኝም ተማፀንኳቸው ። ከውጪ ሳቅ ተሰማኝ … . እየታዘቡኝ መሆኑ ነው ። በሩን ድብደባዬን በታሰርኩበት ሰንሰለት ማደረግ ጀመርኩ … . ብረቱ በር ከፍተኛ ድምፅ ያሰማል … . እኔም በምችለው መጠን ኡ ..ኡ… ብዬ እጮሃለሁ ። አንዳችም ለውጥ አጣሁ ።እንዲሁ ስጮህ ማደርና መዋልን ስራዬ አደረግሁት … እውነት ለመናገር ብዙሃኑን ምን እንደምል አሁን አላስታውሰውም ። እዚች ቀዝቃዛ ክፍል ውስጥ ከ 6 ወራት ያላነሰ ያሳለፍኩ ይመስለኛል ። አንድ ቀን ያለወትሮው በሬ ተከፈተ … . ቀዝቃዛ ላብ በጀርባዬ ሲወርድ ተሰማኝ ። ቁጥራቸውን ባላውቅም የእጅ ባትሪ የያዙ ሰዎች ወደ ውስጥ አበሩብኝ … .. ኩርምት በዬ ቁጭ እንዳልኩኝ ነው … . ቆጣ ባለ ድምፅ ና ! ውጣ የሚል ድምፅ ተሰማኝ … . ዛሬ የመጨረሻዬ መሆኑ ነው ። የተ